Content on this page requires a newer version of Adobe Flash Player.

Get Adobe Flash player

የግል አስተያየት
                         
28/06//2002

1. ለዚህ ነፃነት ላደረሱን አምላክ ክብር ምስጋና ይድረሰው፡፡ ይህንን እንዲዘጋጅ የፈቀደ መንግስትና ያዘጋጁት ልጆቻችን እግዚአብሔር ይባርካቸው እንዲህ ያለው እንዳይደገም
ትውልዱ ልብ ይበል፡፡ እግዚአብሔር ሀገራችንና ሕዝባችንን በፍቅር በአንድነት በነፃነት ይጠብቅልን፡፡
አባ ጳውሎስ

2. ንግስት ሰለሞን እምወድሽ ዘላለም ከልባችን አትጠፊም፡፡
እነ መኩሪያ

3. የናንተ የሕይወት መስዋትነት ለኢትዮጲያ ብርሀን ሆኗል፡፡ ሰለዚህ ለእናንተ ክብር ይሁን
መሣይ

4. ሳሙኤል ብርሀኔ የምወድህ ወንድሜ ምንግዜም አስታውስሀለሁ፡፡
ሰለሞን ብርሀኔ

5. ሰለሞን አስፋው ሁሌም አስብሀለሁ፡፡
መሳይ

6. ውድ አበቴ አቶ አሰፋ ካሳ ወንድሜ ግርማቸው አሰፋ በደርግ ጥይት ሚታችሁ የትም ተጥላችሁ የነበረውን አፅም በተከበረ በዚህ ባማረ ቦታ ተቀምጣችኋል፡፡
አብርሀም አሰፋ

7. ለውድ ውንድሜና እህቴ በዲሞክራሲ ትግል በከፈላችሁት መስዋትነት ሁልጊዜ የማትረሱ ህያው የኢትዮጲያ ልጆች መሆናችሁን ሳውቅ እፅናናለሁ፡፡
ወንድማችሁ ዮሴፍ ጌታቸው

8. ለካሳ ወ/ማርያም፤ መኮንን ገ/አምላክ የሞታችሁት ለሕዝብ ነውና እግዚአብሔር ነፍ ሳችሁን ይማር፡፡
ብርቱካን ገ/እግዚአብሔር

9. ውድ ወንድሜ ጃፒ ወርቄ እግዚአብሔር ነፍስህን በገነት ያድርገው፡፡
ውድ ወንድምህ ሙሉጌታ ጽጌ

10. ውድ ወንድሜ ዳዊት ጀማነህ ነፍስህን መንግሰተ ሰማያት ያኑረው፡፡
ወንድምህ ሚሳ ጀማነህ

11. ለውድ ወንድሜ መኮንን ሁሉቃ እግዚአብሔር ነፍስህን በገነት ያኑረው፡፡ አባትህ አቶ ሁሉቃ ቡቃ የአንተን የመታሰቢያ ሀውልት ምርቃት ቀን ሰያዩህ ህዳር 1 ቀን 2002 በማለፉ አዘንን እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በገነት ያኑረው፡፡
ትዕስት ሁሉቃ

12. አሁንም እናከብርሀለን፡፡
ሚለን

13. ለውድ ማርቆስ ሐዋስ የከፈልከው መስዋትነት ከምንም ነገር በላይ መሆኑን ሳስበው እጽናናለሁ፡፡
ልጅህ ዘመነ ማርቆስ

14. ለውድ አባቴ አሰፋ ተወዳጅ ወንድሜ ግርማቸው እንዲሁም ውድ ወገኖቼ ይህንን ስትከፍሉ ለወገናችሁ ኩራት ለሀገራችሁ አለኝታነት በመሆኑ እስካለንና ለትወልድ አኩሪ በመሆኑ እስከዘላለም እንረሳችሁም፡፡
ሙሉዓለም አሰፋ

15. እግዚአብሔር ይህ አይነት እልቂት መቼም እንዳይደገም ይርዳን፡፡
አባ ብርሀነየሱስ

16. ሕያው አምላክ እንዲህ ካለ አስከፊ እልቂት ሕዛባችንን ይጠብቅ ሰላምና ፍቅር መቀባበልን ያብዛልን፡፡
ቄስ ዶ/ር ዋቅሥዩም አዲሳ

29/06/2002

1. ወንድሞቼ ተስፋዬ አሸናፊ፤ መሐተወርቅ ቅጣው እንዲሁም በዚህ ጉዳይ ያለቃችሁ ሁሉ አልረሳችሁም፡፡
ሐረገወይን አሸናፊ

2. ያን የግፍ ዘመን እግዚአብሔር አሳለፈልን፡፡ ለዚህ መብቃታችን እያመሰገንን ይህን የሰማዕታት ሐውልት ለመስራት ትልቅ ጥረት ላደረጉ ሁሉ ምስጋናዬን ትልቅ ነው፡፡
G/T

3. በትግል ሕይወት ውስጥ ያሳለፍን ብንሆንም ከዚህ የምንማረው መቻቻልን ነው፡፡ ይህ አይነት ነገር አይደገም፡፡

4. ይህንን ነገር በማየቴ በጣም ነው የማዝነው፡፡
ብሩክ

5. የትናንቱ መስዋትነት ለአሁኑ ትውልድ ኩራት ነው፡፡
ውብሸት መሀመድ
ከወጣት ማህበር

6. ውድ አባቴ በርሄ በላይ ነፍስህን በገነት ያኑርልኝ፡፡ የባሰ አታምጣ!!
ይስሀቅ

7. በዚህ ይብቃ!!
መታሰቢያ ኢሳያስ

8. ወንድሜ ጥላሁን ዛሬ ትንሳኤን እናት አባትህ ቢያዩህ ምን ነበር?
በዚህ ይብቃ                                                             

30/6/2002

ለእውነት በጣም የሚያሳዝንና ከአንድ ሠብአዊ ፍጡር የማይጠበቅ ኢ-ሠብአዊ ድርጊት ነው፤ ለነዚህ አረመኔ የደርግ ተባባሪዎች ላይ የሚፈጸመው የፍርድ አሠጣጥ ጠንካራ ያለመሆኑ ይጎለዋል ባይ ነኝ፡፡ “ ክብር በደርግ ወታደራዊ መንግስት ለተሰው ዜጎቻችን “

ይህ እልቂት የ1967 ዓ.ም ሐምሌ 27 ቀን የተገደሉትን 5ኛ ጦር ሜዳ መድፈኛ ሻለቃ ወ/ር መታሰቢያ ሆኖ ይህ እልቂት ደግሞ እንዳይደገም እላለሁ፡፡ በጣም ለሀገር ለወገን
የሚጠቅም ቅርጽ ነው የጊዜው ሰለባ፡፡

ዮሐንስ ገብሬ

ያለፈው አልፏል ዳግም እንዳይደገም እንፀልይ፡፡

ይህ አሰቃቂ እልቂት ደግሞ መነሳት የለበትም
ካሳሁን በቀለ

Hope it will never happen again.

ይህ የዛሬው ቀን የካትት 28/2002 ለኔና ለመላው ለቤተሰቦቼ ትልቅ ደስታ ነው፡፡ ያን የጨለማ ዘመን ያለፍንበት ነው፡፡ ባቢሌ አልሞተም በደሙ፤በአጥንቱ ሀውልት
አቌቁሟል፡፡

ድጋሚ ይህ ዓይነቱ እልቂት እንዳይከሰት ወደ ፈጣሪ መፀለይ አለብን፡፡ ለተሰውት ወገኖቻችን እግዚአብሔር በገነት ያኑራችሁ፡፡
ዳንኤል ንጉሤ

ሰማዕታት ክብር ይገባቸዋል፡፡

እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል፡፡ በዚህ ይብቃ

ብርቄ ከበደ

5.ባየሁት ነገር በጣም አዝኛለሁ፡፡ ሆኖም አሁን ባሉ የደርግ ባለሥልጣን ላይ ፍርድ በደንብ እንዲታይና አመርቂ ውጤት እንድናይ እፈልጋለሁ፡፡
መሀመድ

የከፈላችሁት መሰዋትነት በከንቱ አልቀረም

ሙዘይን

6. በደርግ ስርዓት በጣም አዝኛለሁ ለተጎዱት ቤተሰቦች እ/ር መፅናናቱን ይስጣችሁ፡፡
ሩት ሳህለ

7. በጣም አሳዛኝ ታሪክ እ/ብሄር ደግሞ እንደዚህ አይነት ታሪከ እንዳይኖራት ኢትዮጵያን ይጠብቅ፡፡

8. በጣም ያሳዝናሉ የዛን ጊዜ ሳላልነበርኩ ደስ ብሎኛል፡፡

9. እግዚአብሔር የፈጠራቸውን አየረሳም የሰው ልጅ ጊዜ ሰጠኝ ብለህ ግፍ ከመስራት ታቀብ ዋ!! ዛሬም ነገም፡፡
ዘውዱ ኃይሉ

10. አሁንም ያለው መንግስት ከባለፈው ተምሮ ይሄ እንዳይደገም፡፡ ሁሉም መንግስት ከላይ ጥሩ መስሎ ከበታች ያለ ሹም ሕዝቡን ሲበድል ባላይ ደስ ይለኛል፡፡ በጣም የሚያሳዝን አረመናዊ ድርጊት ነው፡፡ እ/ብሔር ነፍሳችሁን ይማረው፡፡
D.H

11. በደርግ ስርዓት ያየሁትን ማመን አልቻልኩም
ዳግም ዘውዴ

12. እ/ር አምላክ ሆይ ሁልግዜም ኢትዮጰያን ጠብቃት “እንዳይደገም “ለዘላለም ቁስል ነው፡፡

13. እውነትም ዜጎች እንደከብት ይታረዱ ነበርን……? እውነትም አይደገምም
ተክለብርሀን ሐይሉ

14. አይ ኢትዮጵያ የማትችለው ጉድ የለ፡፡ ሁሉም ያልፋል አሁን ግን የዛሬዋ ኢትዮጵያ ላይ ደርሰናል፡፡
B.B.F.Z
A.M.C

15. ስለምን እንደዚህ ሆነ እ/ር ሆይ ኢትዮጲያን ጠብቅ፡፡
ጸጋዪ

16. አንደግመውም!!! አይገባም
Rahel

17. ከአሁን በኋላ አይደገምም ይበቃል፡፡
F.W

18. እባክህ ፈጣሪ አምላክ ነፍሳቸውን በገነት አሳርፍልን፡፡ ኢትዮጵያን ከዚህ መከራ ጠብቅልን፡፡ ግን ለምን? በሰዎች ላይ አላስፈላጊ ድርጊት ለምን እናደርጋለን፡፡
ሙዘይን ሸምሱ

19. ድጋሚ የዚህ ዓይነት እልቂት እንዳይደገም እግዚአብሔር ይጠብቀን አሜን፡፡
ምናሴ መርዓዊ

20. ያ አሰቃቂ ዘመን አልፎ ይሄን መልካም ዘመን በማየቴ እ/ር የተመሰገነ ይሁን፡፡

21. መጪው ትውልድ መቻቻል ከዚህ አስከፊ ደርጊት ከበቂ በላይ መማር አለበት፡፡

22. በኢትዮጵያ የህዝብ ልጆች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ከዘር ማጥፋት አልፎ የተፈጥሮን ማጥፋት ነው፡፡ ይህ ጅምር ነው እንጂ ገና ብዙ ብዙ ያልታወቁ ያልተነገሩ የህዝብ ልጆች ታረክ አለ፡፡ ለዚህ መነሻ የሚሆን ነው፡፡ አሁን ያየነው የተመለከትነው ሁላችንም ይህ ጭፍጨፋ እንዳይደገም የበኩላችን እናበርክት፡፡
ይትባረክ ኃ/ማርያም

23. ነገሩ እንደዚህ ነው ለካ!!
ሔኖክ

24. በጊዜው እድሜዬ ባይደርስም ሙዚየሙን በመጎብኘቴ በተለይም የግርፋት ዘዴያቸውን አስተሳሰራቸው፤ ማፈኛ ካልሲው፤ የሟቾቹን ፎቶ ስመለከት ቁስሉ ተሰማኝ አይኔም እንባ አቀረረ….. አምላኬ ሆይ ዳግም ይህ እንዳይደገም ዘንድ እለምንሀለሁ፡፡
ሰለሞን ፈለቀ

25. እውነት ከሆነ እግዚአብሔር የሥራቸውን ይስጣቸው፡፡
አለማየሁ

26. አላህ ይዘንላችሁ፡፡
Anwar Temam

27. ምን እንደምል አላውቅም፡፡
ANTI

28. በዚያን ዘመን ነበርኩ ለድርጊቱም ህያው ምስክር ነኝ ያለ ባለወኔ ትውልድ ዛሬ ቢኖር ሀገራችን ከምን ትደርስ ነበር?

29. የፍርድ ሂደቱ የት አለ?

30. አባቶች በሰይፍ እና በጦር ያቆዩኝን ኢትዮጵያ ሀገሬን እወዳታለሁ፡፡ መንግስት ካለፈው ምን ይማራል?

31. ለውድ አባቴና እናቴ አቶ ጌትነት ገላውና ሐዳስ ገ/መድህን እንዲሁም ለሙታኖች ሁሉ የሁላችሁም ነፍስ በገነት ይሁንልኝ ( ያኑርልኝ)፡፡ደደቡ ድርግ እና ጠላቶቻ ችሁ እግዚአብሔር የስራቸውን ሰጥቶአቸዋል፡፡
ከውድ ልጆቻቸው ዘላለም ጌትነት እና ቤተሰቦቹ

32. ለሕዝብ ታማኝ ሰማዕታት ናችሁ፡፡
T.Z

33. በጣም አሳኝና ዘግናኝ እልቂት ነበር፤ እዲሱ ትውልድ ይህን ዓይነት ድርጊት ማየት አይሻም፡፡

34. Never ever again, ለእናንተ ሞት እኛ እኖርን ነው፡፡ its hope.
Yeneharge Bekele

35. የንጹሀን ደም በከንቱ አይቀርም፡፡
ቃልኪዳን ኢሳያስ

36. እግዚአብሔር ለሁሉም አለ ወንድሜ እኔ አልረሳህም እንደተነገረኝ አንተ ትወደኝና ታዝንልኝ ነበር ፡፡
ወንድምህ ሳሙኤል

37. መንግስቱ የሰይጣን ታናሽ ወንድም ነው፡፡
ብሩክ

38. የንጹሐንን ደም ያፈሰሰውን እግ/ር ይፍረደው፡፡
ጥበቡ

39. ለትውልድ ተምሳሌነት ለትግል ወሳኝ ናችሁ፡፡
ዳዊት መኮንን

40. እግዚአብሔር ነፍሳችሁን ያሳርፍላችሁ፡፡
በረከት አብርሀም

41. በጣም ያሳዝናል፡፡
ቤካ አበራ

42. በግፍና በጭካኔ የፈሰሰው ደማችሁ በከንቱ አልቀረም ክብር ለንጹሀን ሰማዕታት ወገኖቼ ይሁን!! አሜን
Tiruken

43. የንጹሀን ደም ያፈሰሰውን እግ/ር ይፍረደው፡፡

ሜሮን

44. የፈሰሰ ደም በከንቱ አልቀረም ዋናው ነገር እንዳይደገም ነው፡፡

45. ስማችሁ በመነሳቱ ይህን የክብር ተንሳኤ በማግኘታችሁ እንግዲህ ለእግዚአብሄር ምን ይከፈለው ይህች ቀን የትንሳኤ ቀን ለቤተሰቦቻችሁ ለወገናችሁ አልሞታች ችሁም፡፡

46. ለሁሉም ጌዚ አለው በእውነት ከሆነ ዝግረ 70 መጽሐፍ እንብቤው ዘግንኖኝ ነበር ይበልጥ በፎቶግራፍ ሳየው በቦታው ላይ ያለሁ መሰለኝ እግ/ር ፍርዱን ይስጥ፡፡

47. ደርግ ለካ ግፈኛ ነበር፡፡
እዮብ ቶሎሳ

48. ይህ ክስተት ባለፈ አይነት ሁኔታ የሚታይ ሳይሆን ነገር ግን ዜጎች በሰከነ አእምሮ አቸው ሁሌ አስታውሰውት አኑረውት ዳግመኛ እንዳይከሰት ሲባል ለልጅ ልጅ ሊያ ወርሱት የሚገባ ትልቅ ቅርስ ይህ ነው፡፡ ስለሆነም እጅግ አሳዛኝ ክስተትም ነበር
ነውም እንጂ፡፡

ጌታቸው አደራ ገ/ስላሴ