Content on this page requires a newer version of Adobe Flash Player.

Get Adobe Flash player

51. ታላቅ ስራ ታሪካዊ ስራ ተሰርቷል፡፡ የሞቱት ወገኖቻችን በህይወት ያሉ ያህል ያስቆጥራል፡፡ በግንቡ ላይኛው ቦታ ያሉት ፎቶዎች ለተመልካች እንዲመቹ ዝቅ ብለው ቢቀመጡ መልካም ነው፡፡
ሐዲስ ጸጋይ

52. baayee nalha gaddisiisa dhali nmi Ammaa Kana irra Brkkhuu gaba
Misomaf Kaka u faba

53. ሁልጊዜም ቢሆን የሚዘገንነኝ እልቂት ነው እግዚአብሔር አምላክ አይመልሰው መቼም፡፡
አበባ

54. መደገም አይደል መታሰብ የሌለበት እውነታ፡፡
ታረቀኝ

55. የሁላችሁንም ነፍስ በገነት ያኑርልኝ፡፡
ቤዛ

56. ባልኖርኩበት ዘመን አሁን እንደኖርኩ ተሰምቶኝ አዘንኩላቸው፡፡ አይደገምም፡፡

1/7/2002

1. እጅግ በጣም ዘግናኝ አሳዛኝ እንኳን በዜጋ ለማንም የማይደረግ ታሪክ፡፡

2. የሞቱትን እግዚአብሔር በሰማይ ገነት ይሁንላቸው ይህ ግፍ መቸም አይደገም፡፡

3. ከሞት በመለስ ሁሉንም ሰቃይ ቀምሻላሁ የድሮ ታሳሪ የአሁኑ ጎብኝ ፡፡ትውልድ ሆይ እንዳይደገም እግ/ር ነፍሳችሁን በገነት ያኑረው፡፡
Brook Belay

4. በጣም ጥሩ ነው ይበልጥ እይታ እንዲኖረው አድርጉ፡፡
አዳነ ገብሬ

5. እውነትም መደገም የለበትም፡፡ እግ/ሄር ሆይ ማስተዋልን አብዛልን፡፡

2/7/2002

1. የደርግ መንግስትና ባልደረቦች፤እግዚአብሔር ያረጋችሁትን ሁሉ ነፍሳችሁን ይማር፡፡ የሞቱትና የተሰውት እግዜር ያጽናችሁ፡፡ አጎቴም ነፍስህን ይማረው፡፡
Z. Lee LIYA           

2. Thanks for all u have saved as with Ur blood we are standing free እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በገነት ያኑረው፡፡

3. የደርግ መንግስት በሰራቸው ግፍ እና በቀይ ሽብር ሰለባ ለሆኑ ጀግኖች ቤተሰቦች መጽናናትን እየተመኘሁ፡፡ ይህንን ታሪክ ለተተኪው ትውልድ እንዲተላለፍ ላደረገው መንግስታችን ያለኝን ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡

4. ታሪክ በህዝባችን ደምና አጥንት ተቀይሯል፡፡
Hasan Aman

5. ኢትዮጵያዬ ለዘላለም በፍቅር ኑሪ! ጥፋታችን ታሪክ ብቻ ይሁን! ያለፈውን ይቅር ይበለን!! ሰላም ፍቅር ብቻ ይሁን ዘመናችን፡፡
Nardos Mersha

6. እግዚአብሔር አምላክ ለሞቱት መንግስተ ሰማያትን ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁ፡፡
ትዕግስት

7. ግን ለምን እስከዛሬ ድረስ የደርግ ባለስልጣናት ፍርድ አልተፈረደም አንድ ሞት ሳይሆን ሺህ ጊዜ እየተነሱ ይገደሉ፡፡

8. በጊዜ በኩሉ ………………….ሙዚቃው በጣም ጥሩ ነው፡፡ ይህ ጊዜ እንዳይደገም ምን ማረጋገጫ አለን? ድጋሚ እንደማይከሰት እርግጠኛ ነኝ፡፡

9. በአንድ መቶ አመት የማይገኝ የተማረ ትውልድ ያለቀበት ነው፡፡ ይህንን ለማየት ያበቃኝን አምላክ አመሰግናለሁ፡፡ እግዚአብሄር ነፍሳቸውን ይማር ስማችሁ ከመቃብር በላይ ውሏል፡፡
Abra

10. በዚያ ጊዜ የተፈጸመው አሳዛኝና አስከፊ ስራ፤ ድርጊት አሁን ላለነው ሁሉ መማሪያ ይሁነን ሁላችንም ጥንቃቄን፤ ማስተዋልን ብሎም አርቆ ማሰብን አንርሳ ዳግም ራሳችን
የታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን፡፡
M.M

11. በወንድሞቹ በእናቶቹ በአባቶቹ ደም የጨቀየ መንግስት አለፈ ዛሬስ? እንተሳሰብ ይሆን? እግዚአብሄር ነፍሳቸውን ይማር ለኛም ያስተምር !! የሆነውን አይተናል አንደግምም
እንበል ይበቃናል፡፡
ሐብታሙ ተፈራ

4/7/2002

1. አቶ ታደሰ ገብረእግዚአብሄር የማከብርህ መምህሬ የወደቅለት ዓላማ እንዲሁ በከንቱ አልቀረም ለዚህ ዓላማ የወደቃችሁትን ሁሉ እግዚአብሄር ነፍሳችሁን ይማር፡፡
M.S

2. ወንድሜ ቲቶ ገ/ሚካሌል የሞትክበት አላማ እውን ሆኖ ታይቷል፡፡
ከሰፈር ጔደኖችህ አንዱ

3. We all hope that it will never happen again. It’s really heartful

4. በጣም አሳዛኝ እና አስደንጋጭ ነው በተለይ ለአሁኑ ትውልድ አስተማሪና ጠቃሚ መረጃ ነው፡፡
ሀብታሙ ደጀኔ

5. የአ.አ የኒቨርስቲ ተማሪዎች ለዚህ የተከበረ አላማ ህይወታችሁን የሰዋችሁትን ነፍሳችሁን እግዚአብሄር በንግስ ያኑርልኝ፡፡
ተስፋአለም ሀጋዝ

6. በጣም የሚያሳዝን ድርጊትና ጭካኔ የተሞላበት ግፍና በደል በጭቁን ህዝብ ላይ ተሰርቷል አዝናለሁ፡፡ ከአሁን በኋላ ይህ ድርጊት እንዳይደገም ተተኪው ትውልድ ማወቅ አለበት
መማርም አለበት፡፡
በላይነህ አዲስ

7. የእናቴ ትልቅ ወንድም ከተረሸኑት ውስጥ አለ እና አጽማቸውን ባየሁ ጊዜ አለቀስኩ ነፍሳቸውን ይማረው እግዚአብሔር እንዲህ ከመሆን ያድነን ትግሉ በሰላም ይቀጥል፡፡

8. ሲወራ ታሪክ ይመስለኝ ነበር ዛሬ ግን አምኛለሁ እግዚአብሄር ያን ቀን አይመልሰው፡፡
ሀብቴ

9. ታሪካችን ነው፡፡ ባይደገም ---አላህ ይጠብቀን፡፡
Khalid

10. አላህ ይጠብቀን ጥሩውን ጊዜ ያምጣልን፡
ሰኢድ አወል

11. እንዲህ አይነት ነገር ከቶም ቢሆን መደገም የለበትም ሁላችንም በፍቅር በመቻቻል እንድንኖር እግዚብሔር ይርዳን፡፡
Dawit

12. ታሪኩ በእውነት ያሳዝናል ፈጣሪ ለእነዚህ ወጣቶች ነብሳቸውን በገነት ያኑራት፡፡
ዳንኤል ተሰማ

5/7/2002

1. ድርጊቱ እጅግ ያሳዝናል! ለኢትዮጵያ አንድነት የይቅርታ ልብ ይኑረን፡፡

2. በጣም አሳዛኝ ነገር ነው ግን እንዲህ አይነት ነገር ባይፈጸም መልካም ነው፡፡ አደራ በድጋሚ መልካም ነገር እመኛለሁ፡፡ ታሪክ ይሁን አላለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡
F.A

3. እረ ባካችሁ እንማር? እሺ በውነቱ በጣም አዝኛለሁ ልቤም ተሰብሯል፡፡በታሪክ ስሰማ እውነት አይመስለኝም ነበር አሁን ግን አምኛለሁ፡፡
ቢሻው

4. አእምሮ ማመን ከሚችለው በላይ ከባድ ጭፍጨፋ እንዲህ አይነት መሪዎች እንዳይደገም እንማር፡፡
አብዲራሂም ሱልጣን፡፡

5. ያልደረሰበት አያገባውም አባት ሳትቀብር መኖር መባድ ነው፡፡
S.M

8/7/2002

1. በዛ ጊዜ አለመፈጠሬ እግዚአብሔርን በጣም አመሰግነዋለሁ፡፡ በቀይ ሽብር የሞቱትን ቤተሰብ እግዚአብሔር ያፅናቸው፡፡

2. እንደሀገር ልናፍርበት እንደትውልድ ልንማርበት የሚገባ ጨለማ ታረካችን ነው፡፡
ቢኒያም ውብሸት

3. ታሪኩን ማወቅ እና መኖር በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ይህ ታሪክ ሁለተኛ መደገም የለበትም፡፡
ዩኒፊኸኤሉ

4. እይታውን ውድጀዋለሁ በጣም ጣሩበት፡፡

5. Nuawaelu Rexum Indicora. Lord Have Mercy

6. በተመለከትኩት በጣም አዝኛለሁ አሁንም መሪዎቻችን የዚህ አይነት ነገር እንዳይደገም አሳስባለሁ፡፡
ሐብታሙ ዓለሙ

7. አስደናቂ የሆነ ነገር ነው ያየሁት ጥሩ ነው፡፡

8. አለመፈጠሬ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፡፡ ከእንደዚህ አጋጣሚ እትዮጲያን ይጠብቃት፡፡

9. ከእንግዲነህ የዚህ ዓይነቱ ለማንም ኢት/ዊ ዜጋ አያድርገው፡፡
አምሳሉ

10. በጣም የሚያስደንቅ ስራ ነው፡፡

11. እግዚአብሔር የሞቱትን ወንድም፤እህት፤አባት፤ልጆች ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን የአሁኑም ትውልድ የፋሽሽት ደርግን ድርጊት በዚህ ሙዚየም ደግመህ ደጋግመህ መመልከት ይኖርብናል፡፡ መሪዎችችንም ይህ ድርጊት እንዳይደገም አደራ፡፡
ይድነቃቸው ባንተአይምሉ

9/7/2002

1. እንኳን ሊደገም ሊታሰብም አይገባም በሌሉበት ፍርድ የተበየነባቸው ሊታደኑ ይገባል፡፡ በተለይ መንግስቱ፡፡
ስዩም

2. ሙዚየሙን ተመልክቻለሁ በጣም ልብ የሚነካ ነው ያሳዝናል ይህ በውነቱ ለወደፊቱ ሊደገም የማይገባ በመሆኑ በተጨማሪ ደርግ በወቅቱ ያደረሰውን በጥቂቱ ብቻ በመሆኑ
ወደፊት በስፋት ቢቀርቡ ታሪክ በመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል፡፡
መልካሙ

3. አለም ከዚህ መማር ያለበት ነገር ቢኖር መብትና ዲሞክራሲ ሁሌም አይነጣጠሉም አሸናፊዎች ናቸው
ሚሊዮን አበራ

4. ወገኖቻችን አልሞቱም ታሪካቸው አለ፡፡ እኛም እንዘክርላቸዋለን ለዘላለም በህይወት እንዳሉ እናስታውሳቸዋለን፡፡
አለባቸው

5. በፍጹም አይደገምም በናታችሁ ያለፈው ዘመን ይበቃናል፡፡
ቶማስ

6. እጅግ በጣም ይደንቃል፡፡ እንደዚህ መሆኑን አላውቅም ነበር፡፡ የሆነውን ነገር በማየቴ እጅግ ደንቆኛል፡፡ የሄ ነገር እንደማይደገም አልጠራጠርም፡፡
ናትናኤል

9. የሰው ስጋ ለበስ አውሬዎች በኢትዮጲያውያን ዘመን መፈጠራቸውን አላውቅም ነበር ይገርማል ሰው አውሬ የሆነበት ዘመን አለፈ፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡
ቢኒያም

10. ከአንድ ኢትየጵያዊያን የማይጠበቅ ስራና ድርጊት ተመልክቻለሁ፤፤
ሀብታሙ በላይ

11. ትውልድ ያልፋል ታሪክ ግን ሰለማያልፍ ሁለተኛ እንዳይደገም በየዘመኑ ያለ ትውልድ የራሱን አስተዋጽኦ ለሰላም ማበርከት አለበት ምክንያቱም እንደዚህ ያለ ታሪክ ለትውልድ
ማውረስ ማለት የሀገርን ገጽታ ከማበላሸቱም በተጨማሪ ለሰው ልጅ ክብር አለመኖሩን
ያመለክታል፡፡

10/7/2002

1. እንዳየሁት እህታችን፤አባት፤እናት፤ ወንድሞቻችን ሞተዋልና እግዚአግሔር በገነት ያኑራችሁ እላለሁ፡፡

2. ነፍሳችሁን በገነት ያኑርልን፡፡

3. ብድሬን ስለመለስኩ ሀዘን አይሰማኝም፡፡

ረዘነ

4. እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በገነት ያኑርልን፡፡
የኒው ኤራ ተማሪዎች በሙሉ

5. መቼም መቼም እንዳይደገም አዜብ ሽፈራው አልሞትሽም፡፡

6. Its shocking

11/07/2002

1. ስቃያችሁ ብጋራ ምንኛ ደስተኛ በነበርኩ? አይዟችሁ ሁሉንም ፈጣሪ ያያል (God
Bless You All:
Getachew Muche

2. እግዚአብሔር በነፃነት ያኑራቸው ዳግም እ/ር በቀኝ አውላቸው፡፡
ሄኖክ

3. ልዑል እግዚአብሔር መንግስተ ሰማያትን ያውርሳችሁ፡፡ ለኛ በነፃነትና በሰላም መኖር የናንተ አስተዋጽኦ የሚያኮራ ነው፡፡ለመላ ቤተሰባችሁ መፅናናትን እመኛለሁ፡፡ይህንን ሰማዕታት ለሕዝብ እይታ ያቀረበውን እግዚአብሔር ዕድሜውን ያርዝመው፡፡
ማህደር

4. ደግሞ እንዳይደገም ትውልድ ይወቀው ለአባቴ ብ/ጄነራል ሙሉጌታ ወ/ዮሃንስ የምወደው

ሚሊዮን ሙሉጌታ

5. While exaturating the facts of our country we showing the world only the bad Side what happened to all the good they did???
Yohannes Henok

6. Avoid such Performance
Desta

7. መንግሰተ ሰማያትን ያውርሳችሁ! እኛ አሁን ለዚህ ላለንበት እናንተ ናችሁ መሰረታችን ለመላ ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡፡ይህ ኤግዚብሽን ላላወቁት እንዲያውቁ
ረድቷልና፡፡
ዊንታ

8. አሰቃቂ ነገር፡፡
ኃይሌ

9. እግዚአሄር በመንግስቱ ያስባችሁ!!! ይህንን ዳግመኛ አያሳየን!!!
Hanna Mersha

10. እ/ር ነፍሳችሁን በገነት ያኑረው ፈጽሞ እንዲደገም አንፈልግም፡፡

11. They did not know what they did?
Amanuel

12. እ/ር እንዲህ አይነት መአት አያምጣብን ፈጣሪን እንለምን፡፡
Long Lived Ethiopia

13. እ/ርበገነት ያኑራችሁ ለመላ ቤተሰቦቻችሁ መጽናናትን ተመኝቻለሁ፡፡The most shocking.
Haileyesusu Gizaw

14. እ/ር መንግሰተ ሰማያት ያውርሳችሁ፡፡ ይህንን ሰማዕታት ለተመለከተ ስለ ቀይ ሽብር ምንም እንደማያውቅ አወቅኩኝ፡፡ ብሁ ታሪክ ብሰማም እንድ ምርጥ ትውልድ እንዳጣን ምንግዜም ልናስበው ይገባል፡፡ ለልጅቻችን ፍቅርን ማስተማር እንዳለብን ያስገነዝበናል፡፡ ፍቅር መቻቻልን ይስጠን፡፡
ሲሳይ

15.የሰው በላው ስርዓት ዘር አጥፊዎች አሁንም በየስርቻው ይታደኑ!!

16. እ/ር የፈጠረውን ፍጡር አሰቃይቶ የገደሉትን ሁሉ ዋጋቸውን ከፈጣሪው እንዲያገኝ!!