Content on this page requires a newer version of Adobe Flash Player.

Get Adobe Flash player

12/7/2002

1. የሰው ልጅ ፈጣሪውን ከረሳ ምን ያህል ዘግናኝ እንሰሳዊ (የበላ) ስራ እንጅ ፡፡ ይህ ምስክር ነው፡፡ እነዚህ ሰማዕታት የዘለአለም ዕረፍት ለነሱ ይሁን፡፡
አባ ሐጎስ

2. እግዘአብሔር በሕይወቴ ይሄን ቀን እነደዳይ ሰለረዳኝ አመሰግነዋለሁ፡፡ ወንድሞችንም ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልኝ፡፡

3. እ/ር አትግደል ያለውን ትዕዛዝ አፍርሶ በመግደሉ በጣም ትልቅ ሐጠያት ሰርቶአል፡፡ በጣም አሳዛኝ ነው በሀገራችን ዳግመኛ እንዲህ ዓይነቱ እልቂት እንዳይፈጸም   እግዚአብሔር
ከኛ ጋር ይሁን፡፡

4. ሕዝባችን ያሳለፈው ሰቆቃ በጣም ዘግናኝ ነው፡፡ ለመጪው ትውልድ ይህ አስከፊ ነገር እንዳ ይደገም ትምህርት ነው ፈጣሪ ኢትያጲያን ይባርክ፡፡

5. No explanation in English or Amharic

6. በጣም ያሳዝናል እግዚሰብሔር መልሲ አያምጣው::
ወይ ወንድሞቼ
ወይ አባቶቼ
ወይ እናቶቼ
ወይ እህቶቼ
እኔ አዚህ ተኘቼ
ነፃቴን አግኝቼ
መቼ እከፍላችኋለሁ
መቼ?
Amin Mahommed

7. በጣም ነው የሚያሳዝነው ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይስጣቸው፡፡

8. መቼም እንዳይደገም!
ማክዳ ተሻለ

9. በጣም አሳዛኝና አሰቃቂ የትውልድ ውድሚያ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ በማናቸውም ቀጣይ ዘመነ መንግስት እንደማይደገም ተስፋ አለኝ፡፡
ሜሮን ጸጋ

10. በጣም አዝኛለሁ የሞቱትን ነፍስ እግዚአብሄር በገነት ያስቀምጣቸ! በድጋሚ በኢትዮጲያ ምድር ማየትና መስማት አልፈልግም፡፡

11. INPRESSIONATA DAL CORAGGIO DI CHI HA LOTTATO PER LA HIBERTA E CA DE NOCRAFIA QUESTI IBEACI SONO ANCORA VIVI
ANOMEWA

13/7/2002

12. ለኛ ለኢትዮጵያውያን ሲሉ ሰማዕት ለሆኑት ወገኖቻችን በሙሉ ክብርና ሞገስ ይገባቸዋልና ቃላቸውን ጠብቀን በልማት እንካሳቸው፡፡
ተመስገን

13. We will always remember. They did not die in Vain.
Mongo awabanki. E.O.M
Kenya

14. ለመጪው ትውልድ ጥሩ ነገር አስተላልፋችኋል፡፡ እኛም ለመጪው ትውልድ ተንከባክበን ለማሳለፍ ቃል እንገባለን፡፡
ተማሪ አወል

15. ይሄ መልዕክት ለኛ ለዚህ ትውልድ ነው፡፡
ለሙ

16. እኔ ለካ ያንድ ቤተሰብ ውጤት አይደለሁም የነዚህ ሁሉ ውጤት እንጂ፡፡
ቢኒያም መኩሪያ

17. የሞቱትን ነፍሳቸውን ይማርልን፡፡ ዳግም እንደዚህ እንዳይደገም፡፡
የሱፍ

18. ሕማቅ ታሪክ የሕሊፍና ግን አይደገም፡፡

19. በጣም አስጨናቂ ዘመን እንዳለፈ ተረድቻለሁ!! ማሪያም ነፍሳቸውን በገነት ታኑራቸው፡፡
ፍቅር እና ዌስ

20. በጣም አዝኛለሁ ነገር ግን ለኛ ለተማሪዎች ስላሳያችሁን እናመሰግናለን፡፡
ሙሉጌታ

21. እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር ያለፈው ግፍና በደል ፈፅሞ የማይደገም ከመሆኑ ሌላ ትምህርት ሰጭነቱ የጎላ ይሆናል፡፡የበደል አድራጎዎች ቤተሰብ ለቀሪ ልጆቻቸው የተፈ ጸመውን ድርጊት አስመልክተው ትምህርት ይስጡ፡፡
TMR

22. በአውኑ በዚያን ዘመን ባለመኖሬ እራሴን እንደ እድልኛ እቆጥራለሁ፡፡ ምክንያቱም በማ ንኛውም ሰዓት ማንም ሊያጠፋኝ ይችል ነበር!!

23. A Very Powerful + sad story that should not be forgotten. You’re new Museum will continue to inform all who visit.
Helen Wolfe
London UK.

24. In this era of terror Ethiopia wasted its youth and a great talent. Never Again.

25. What a memorable experience of Ethiopia story. What can we learn from? All this? Forward ever, backward never. God bless Ethiopia.
Malaki – Kenya

14/7/2002

1. በእውነት ይህ አስከፊ ድርጊት አይደገም የሞቱት ዜጎች ለዚህ ብሩህ ዕለት ያበቁን በመሆኑ ክብር ይገባቸዋል፡፡
ተክሌ ገ/ሕይወት

2. ታሪክ የማይረሳው ሀዘንና ሰቆቃ ነው ጉብኝቱ በክላሲካል ሙዚቃ ቢታገዝ መልካም ነው፡፡

3. በእውነት ይህ ሙዚየም የመላው አፍሪካ የአምባገነን መሪዎች ጭካኔ ይወክላልም ለወደፊቱ የአፍሪካ መፃኢ ትውልድም ትምህርት (Practical) ይሆናል፡፡
ፀጋ

4. ውስጤ በጣም ስላዘነ ምን ብዬ እንደምገልጽ አላውቅም ብቻ እግዚአብሄር መልካም ነገርን ያድለን፡፡
ሄለን

5. እባካችሁ በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ እንደ ታሪኩና እንደተፈጸመው ድርጊት ገና ብዙ የሚቀሩ መረጃዎችና ቅርሶች አሉ ብዬ አምናለሁ፡፡ ለማግኘት ጥረት ይደረግበት፡፡
አሰግድ

16/7/2002

6. ይህ ሥርዓት ተመልሶ እንዳይመጣ ያገኘነውን የዴሞክራሲ ጭላንጭል ሊቀሙን ከሚሯሯ ጡት ቀበኞች እንጠብቅ፡፡

7. አሁንም ነገም ሁሉም ሊያውቀውና ሊማርበት የሚችል ነው፡፡
Kalekidan Tafesse

8. Never Again
Kaleb

9. የዛሬ 34 አመት ተመልሼ እንዳስታውስ አደረገኝ ያ! ዘግናኝ ዘመን፡፡ እሁን ግን አበቃ፡፡
Jimmy Fekale

17/7/2002

1. ከዚህ ድርጊት መጭው ትውልድ ተምሮ ለወገኑ ተቆርቌሪና አለኝታነቱን ለገኑ ያሳይ እንጅ ለቀጣይ የወገናችንን አፅም ማየት ይቅርብን በዚህ ይብቃን ድለወ ለሰማዕታት ወገናችን፡፡

2. ይህ ታሪክ በምድር ላይ መተፈጸሙት ዘግናኝ ታሪካዊ እውነቶች ውስጥ እንዱ ነበር፡፡
አበቃ!!!

3. ቢገመርም ታሪክ ነው፡፡
ዮናስ

4. በጣም ያሳዝናል፡፡
Bini

5. በአካል እንጅ በመንፈስ አልተለያችሁም ታሪካችሁ እስከ ዘላለም ይወሳል፡፡
ግዛቸው ኃ/ማርያም ደሳለኝ

6. ትግላችሁ ለኛ መብራት ነው፡፡
ተክላይ ገ/መድህን

18/7/2002

1. እኔ ይሄንን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ያየሁት በሚዲያ ሲወራ አላምንም ነበር አሁን ግን አመንኩ አዘንኩ ከአሁን በኋላ ግን እንዲህ አይነቱ ነገር መደገም የለበትም፡፡ የሞቱትንምነፍሳችውን ይማረው ለነፃነት ነው የሞቱት እነሱም ቢሞቱ እኛ የነሱን ዓላማ ይዘን አገራችንን እንቀይራለን፡፡
ተስፋአለም ገብረየስ

2. አይደገምም! ይበቃል! እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያኑር፡፡
Fikru Fiseha

3. ቆሻሻ ታሪክ ነው!!

4. በጣም የሚገርመውና የሚደንቀው ይህን ሁሉ ስ ተገድሎ እያዩ የማይለወጡ እልቂትን የሚፈልጉ ሰዎች አይጠፉም እና እ/ር ልብ ይስጣቸው፡፡ እንዲህ ዓይነት ጭካኔ መታሰብም የለበትም ኢህአዴግ ለዘላለም ይኑር፡፡
ክምቸች ዘመድ

5. ታሪክ ሆኖ መቅረቱና ለኛ ብለው ያደረጉትን መስዋእት እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በሰማይ ያእቀምጥልን፡፡
በእምነት ላቀው

6. ታሪካችንን እንድንረዳ ስላደረጋችሁን በጣም እናመሰግናለን፡፡
ናትናኤል

7. ለሰማዕታት ነፍሳችሁን እ/ር በገነት ያኑር ኢትየጲያ ታላቅ ነበረች፡፡ በዚያን ዘመን ግን በእውነት በጣም ትንሽ ሀገር ነበረች ያለፈ ታሪክ ሁሉ አልፏል፡፡ እኛ ተተኪ ትውልድ
ሁሉ ትልቅ የቤት ስራ ከዚህ እንማር፡፡
ከተመልካች እንዷ ነኝ

8. ያለፈውን በደል ትተን ሁላችንም በአንድነት ሆነን በእግዚአብሔር ፍቅር ተያይዘን አገራችንን እንለውጣት፡፡
ሄኖክ

9. ውድ ተስፋዬ ሶሬስ፤ ውድ ካሳሁን በላይነህ፤ ውድ ተክሉ ወልዴ ሁሌም አልረሳችሁም፡፡

10. እነዚህ ሰማዕታት አሻራ ትተው አልፈዋል፡፡ ነገር ግን ደግሞ ይሁ ተቌም ታሪካቸውን ለትውልድ እንዲቆይ ማድረጉን እጅግ በጣም በአድንቆት አየዋለሁ፡፡

11. One day somebody should pay the price of all this young man and women life jousts should be serve.

12. ለመጀመሪያ ግዜ ተመልክቻሁ የትናንትናውን መጥፎ ገፅታ ፍንትው አድርጎ ያሳያል ሰነገ ምን መከተል እንዳለብንም የቨመለክታል፡፡ ክብር ለዚህ ላበቁን ሰማዕታት ይሁን፡፡

13. በጣም ጥሩ ነገር ነው የሰራችሁት ማለትም አሰተማሪ የሆነና ታሪካችንን እንድንረሳ ያደረገን ሙዚየም ነው፡፡ ታዲያ በደንብ ቀጥሉበት፡፡
ናትናኤልሳ

14. ለወደፊቱ ይህ እንደማይደገም ተስፋ አለኝ እግዚአብሔር ይጠብቀን፡፡
ልዑል አማኑኤል

15. በጣም ነው ያዘንኩት ይህ ሁሉ መከራ አልፈን ለዚህ መብቃታችን፡፡
ፀሐይ ዮሐንስ

16. ለኢትዮጵያ ሀገራችሁ ትልቅ ስራ ሰርታችሁ አልፋችኋል በዚህም የጀግና ሞት ሞታችኋል እግዚአብሔር በገነት ያኑራችሁ ለእምዬ ሀገራችንም ከእንዲህ አይነት ሰቆቃ ዳግም
ይጠብቃት፡፡ በዚህ በቃሽ ይበላት፡፡

17. ሁሉም ነገር ታሪክ ሆኖ መቅረቱና ማለፉ ጥሩ ነው ግን ሁሌም መስዋት የሆኑትን Sኢትዮጵያውያን ሁሌም እናስባቸዋለን፡፡

18. በእኛ እንዳይደርስ የምንመኘውን በልጅ እና እናት ሲሆን ያሳዝናል፡፡
Mehret Equbay

19. Oh my God. I can’t believe, it is very disgusting I feel bad. God Bless you.

20. I feel bad but I hope one day Ethiopia will become great.
Nebyat

21. ፍትህ ለዘላለም ይኑር!!!!
Dany

22. አላህን የሚፈራ እንደዚህ አያደርግም፡፡
Ibro-man

23. ለገዢው ተማሩበት

24. የህያው ስም ለዘላለም ይኖራል፡፡
ያሬድ

25. የታላቁን የእስጢፋኖስ ክብር ያውርሳችሁ፡፡
ከወሎ ሰፈር

19/7/2002

1. እንደዚህ አይነት እልቂት እንዳይደገም እላለሁ፡፡
አብደል ማሊክ

2. ሊደገም የማይገባው የሚገርም ትልቅ የጭካኔ ታሪክ ነው፡፡
ሚኒሊክ

3. ባያዩትም ሞተው አልቀሩም ዲሞክራሲው በማስፈን ላይ ነን፡፡ ክብርና ሞገስ ለሰማዕታት
ሲ/ር ገነት ያይኔ

4. እጅግ በጣም ያሳዝናል፡፡ ይህ እንዳይደገም ሁላችንም በድርጊት ማሳየት አለብን፡፡
ፈለቀች