Content on this page requires a newer version of Adobe Flash Player.

Get Adobe Flash player

4/8/2002

1. ትግል ሁሌም አያልቅ የዘመኑ ትልቅ ትግል ከድህነት የመውጣትና የማሸነፍ ትግል ነው!!

2. እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቃት እንዳይደገም፡፡
ኤርሚያስ ተስፋዬ

3. እግዚአብሔር የሰማእታትን ነፍስ ይማር፡፡ ሁሉም ያልፋል፡፡

4. የሰው ልጅ በሰው ላይ እነዴት እንዲህ ይጨከናል፡፡
ቢቢ

5. ያ ክፉ ዘመን አባቴን ነጥቆኛል አሁን 26 አመቴ ነው፡፡ ግን አባቴ አሁንም ይናፍቀኛል፡፡ አባቴን ካጣሁ 22 ዓመታት ተቆጠሩ፡፡

6. የደርግ አገዛዝ በምንም አይነት ለሰው ስጅ አይበጅም አላህ በላይኛው ዓለምም ይፍረድባቸው፡፡

7. መንጌ የስራሕን ይስጥህ ከፈጣሪ አትጣ፡፡
Never again.
FA

8. እውነትም ደርግ ባለጌ ነው፡፡ በተለይ መንግስቱ፡፡

9. Hope it will never happen. ቅን ልቦና ይስጠን፡፡

10.ወይ እማማ አትዮጲያ ይህንን ሁሉ አሳልፈሻል ፡፡ ያኔ እኛ ም ነበርን፡፡ ለነገሩ አንኳን አልኖርን ይህንን ሁሉ ባለማየታችን እድለኛ ነን፡፡ በጣም አሰቃቂ ነገር ነው እንደገም መቸም አንፈልግም፡፡
ሀይልሽ

11. ወንድሜ ጌትነት ለዘላለም አልረሳህም፡፡ መኖር ደግ ብዙ ያሳያል! የማያልፍ የለ ሁሉ ያልፍና የተሻለ ይመጣል፡፡ እስኪመጣ ያልፋል፡፡
ሳሙኤል ተስፋዬ

7/8/2002

1. የሀገር አለኝታ የሆኑ ወጣቶችን በግፍና በጭካኔ የሚጨፈጭፍ አገዛዝ አልፏልና እግዚ አብሄር ይመስገን፡፡
እዮብ በላይ

2. ያሳዝናል መቼም እንዳይደገም፡፡

3. ያም አልፏል፡፡
H.M

4. I hope & pray that this kind of life don’t happen again in our life too.

5. ይህ አሰቃቂ ታሪክ በኢትዮጲያ የመጨረሻ ነው መቸም አይደገም፡፡
አማረ ጌታቸው

6. የኢትዮጲያ ሕዝብ ካለፈው ግፍና ሰቆቃ በመማር መጪው ትውልድ ለሰላምና አንድነት እንቅፋት የሆኑትን መናናቅና ጥላቻ አስወግዶ በመከባበርና በመግባባት እንዲኖር ሕያው ምስክር ነው፡፡
አርአያ ተስፋይ

7. ይህ ድርጊት ዳግመኛ እንዳይፈፀም ኢትዪጲያውያን ተስማምተን፤ተግባብተንና ተቻችለን እንኑር ኢትዮጲያ በነፃነትም ለዘላለም ትኑር!!

8. ትውልድ ይህን አሰቃቂ ድርጊት እንዲረዳው በራሱ ማድረግ ታላቅነት ነው፡፡
ሻ/አመረ የሺጥላ

9. ለትውልድ ሰሀገር ነፃነት ስትሉ ሰተሰዋችሁ የኢህአፓ አባላት በሙሉ አስታውሳችኋለሁ አልረሳችሁም በተለይም ውድ ጔደኛዬ ከበረ ኃይሌ አስታውስሃለሁ፡፡ ታሪክህን ምንግዜም
አወሳዋለሁ፡፡
አድማሱ አበራ

10. No more blood, no more suffering, no more death. What we got is more than enough. Let’s live together with unity and help our land to shine in the world.. ይህ አሰቃቂ ታሪካችን ነው እንዳይደገም! ፈጣሪ መከፋፈልን አርቆ ፍቅርን
ያብዛልን፡፡

11. it’s an unforgettable past!!

12. Of course its- is ridicule’s such a terrorize historical moment!!

13. Feel pity abut past historical political oppresses ion, Peace and love.
Ethiopia.

14. DEPUiS 1974… MA PRESENCE (ET MON COEIJR) EST AVEe VOIJS
VOTRE Ami.
JOSE-MARiE BEL
ESPACE REiNE DE SABA, PARIS

15. ባየነው ነገር በጣም አዝነናል፡፡
ከአፍሪካ የጤና ኮሌጅ

16. ሁሉም እንደየስራው ይፍረድበት በነጩ ዙፋን ፊት ይቀርባል!!!

17. የደርግ መንግስት ሲያገርገው የነበረው በጣም ያሳዝናል በእውነት በጣም አዝነናል ዳግም እንደዚህ አይነት ታሪክ እንደማናይ ተስፋ አለን፡፡ ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር
ፍጹም

18. ነፃነት እንድናገኝ ለረዱን ከልብ እናመሰግናለን እኛ ልጆቻችሁ የእናንተ አርአያ ሆነን በተግባር ላይ የተመሰረተ የኢትዮጲያ ድህነት ለማስወገድ ቃል እንበጋለን፡፡ ለኛ ሲሉ
ህይወታቸውን ለሰጡት ሰማዕታት ውለታቸውን ያገኙ ዘንድ እንፀልያለን፡፡
አያት

19. በተመለከትኩት ነገር በጣም አዝኛለሁ፡፡ ግን በአሁኑ መንግስታችን እንባችን ተጠርጓል፡፡

20. ይህንን በማየት ጭፍጨፋው እንዳይደገም ትምህርት ይሁነን እንፀልይ፡፡

9/8/2002

1. እጅግ በጣም አሳዛኝና አሰቃቂ ነገር መስራት ጥሩ ነው? በተለይም ለመንግስቱ ሀ/ማርያም ትምህርት ይሆን ዘንድ ተተኪው ትውልድ ከዚህ አይነት አሰቃቂ ነገር እንዲቆጠብና ለልማት መነሳት እንዳለበት አሳስባለሁ፡፡ ለሀገራችን መስዋት ለከፈሉት እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በገነት ያስቀምጥላቸው፡፡

2. እግዚአብሄር ገነትን ያውርሳችሁ ልፋታችሁ ሰምሯል፡፡ ዘላለማዊ መፅናናትን ለቤተሰቦች
እመኛለሁ፡፡

3. ወንድሞቻችን በደረሰባቸው ግፍ እጅግ አድርገን እናዝናለን፡፡

4. ለህዝብና ለወገን ብላችሁ መስዋት ለሆናችሁ ወገኖቼ እግዚአብሔር ከአብርሀምና ከይስሀቅ ጎን ያኑራችሁ፡፡ እግዚአብሄር ኢትዮጲያን ያስባት፡፡

5. እናከብራችኋለን፤እንወዳችኋለን እናደንቃችኋለን እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በገነት ታኑራችሁ፡፡ ለተሰውት ባጣም አዝኛለሁ፡፡

6. ውድ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ለደረሰባችሁ መራራ ግፍ እጅግ አዝነናል፡፡ ለቤተሰቦ ቻችሁ መፅናናትን ይሁን!
ፓስተር ካሳሁን ማሞ
ፓስተር አዲስኪዳን ሙሉጌታ
ፓስተር በርናባስ አለማየሁ

7. ይህ አሳዛኝና ትልቅ በደል የተፈጸመበትን ታሪክ ለቀጣይ ትውልድ እንዳይደገምና ትምህርት እንዲሆነው በማቆየታችሁ እናመሰግናለን፡፡ የሰማዕታትን ነፍስ እግዚሰብሔር በገነት ያኑርልን፡፡
ፈለቀ

8. ውድ ጓደኞች ስማችሁና አላማችሁ ህያው ነው፡፡

9. ለህዝብና ለወገን ስለ እራሳቸውን መስዋዕት ላደረጉ ሰማዕታቶች ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን፡፡ የሰማዕታት ኮሚቴን ያኑርልን፡፡

10. በሰማዕታት ምክኒያት ሕያወታቸውን ላጡ ፈጣሪ በገነት ያኑርልኝ፡፡

11. በጣም አስፈላጊ ቅርፅ ነው የተቀመጠው ግን በእያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ዜጋ ህሊና ውስጥ ስር ሰዶ መግባት አለበት፡፡ ምክኒያቱም ይህ አስቀያሚ ታሪክ እንዳይደገም፡፡

12. እንደ እድል ሆኖ ቨዛን ዘመን ልጅ አልነበርኩም ታላላቅ ወንዶሞቼና እና አህቶቼ ያንን ዘመን እንዴት እንዳሳለፉት ባሰብኩ ጊዜ ህሊናዬ እጅጉን በጣም ተነካ፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ዳግም ይህ ነገር በኢትዮጲያ እንዳይደገም አድርግ፡፡አምላክ ለተሰው ሰማዕታት መንግስቱን ያውርሳቸው፡፡
ዘውዱ በቀለ

13. እግዚአብሔር የአገራችን የተሰዉትን አባቶቻችንና እናቶቻችን ነፍስ ይማርልን፡፡

10/8/2002

1. እጅግ አሳዛኝ፤ አሰቃቂ የሰው ፍጡር እውነት ይህን ያደርጋል በሰው ላይ ብዬ አላምንም ነበር አሁን ግን አየሁ ዳግም መቼም ከአሁን በኋላ እንዳይፈጸም ትምህርት ነው ሰማዕታት በእዚአብሔር ዘንድ ትፅድቃላችሁ፡፡
አርአያ ተስፋዬ

2. ካለፈው አረመኔ አገዛዝ ብዙ ትምህርት መማር አለብን፡፡

3. ከዚህ ድርጊት ጊዜ ሳንወስድ እንማር በዚህ ይብቃ፡፡
ሙሉዓለም ግዛው

4. አይ መንግስቱ ሀ/ማርያም ስምን መላአክ ያወጣዋል ልትሉ ነው አረመኔ!

5. እጅግ በጣም አስከፊ ትእይንት ነው ያየሁት፡፡ ይህ እውነት በኢትዮጲያ ተፈፅሞ ከነበረ በጣም ያሳዝናል አሁን ግን ያለፈው አለፈ አሁን ያለነውን ትውልድ በጥሩ ጎኑ አሳድጉ፡፡
አንድነት ምናለ

6. እራሴን በእድለኛነት አስጋለሁኝ ምክንያቱም በእዛን ጊዜ አለመፈጠሬ፡፡ ነጣም አዝኛለሁ፡፡ እንደዚህ አይነት መጥፎ አስተሳሰብ እንዳይደገም፡፡
ሚካኤል ደጀኔ

7. በጣም ልቤ ተነካ! እንዲህ አይነት እልቂት ዳግም ወደ ኢትዮጲያ እንዳይመጣ ሁላችንም እንዴእምነታችን እንፅልይ !!!
ታሪኩ ፀጋዬ

8. ዳግም እንዳይመጣ እናስተውል
አብዲ አስገዶም

9. ያየሁት ዳግመኛ እንዳይደገም በወጣትነቴ የበኩሌን ለማበርከት እቆማለሁ፡፡
ዘመድኩን ጀምበሬ

10. ያ አስከፊ ዘመን አለፈ ዳግም እንዳይደገም ሁላችን እንፀልይ፡፡
ሳሙኤል ወርቁ

11/8/2009

11. በጣም ሰሀገር ለወገን የሚጠቅም ቅርፅ ነው በጣም ደስ ይላል በርቱ፡፡
E.T

12. ትላንት የከፈላችሁት መስዋትነት ዛሬ ላለነው ወጣቶች ትልቅ ሀገራዊ፤ ቤተሰባዊን አደራ ጥላችሁልናልና ፈጣሪ ውለታችሁን ይክፈላችሁ፡፡
E.C

13. It is good work for all Ethiopian people
Jerry

14. ይህ ሁሉ መስዋትነት ለሀገራችን የተከፈለ የሞት ካሳ ነው፤ ፈጣሪ ነፍሳቸውን ዘላለም በገነት ያኑረው፡፡ በስጋ ቢለዩንም ዘላለም ግን ሕይወታቸው አብሮን አለ በሰሩ የህይወት ገድል፡፡ ኢትዮጲያን እ/ረ ይባርካት፡፡

15. እነዚያ ቀኖች አልፈው ዛሬ አዲስ ቀን መጥቷል፡፡ ይህን ቀን የለወጠው ማንም ሳይሆን እ/ር ነው፡፡ ከአሁን በኋላ እንዳይደገም እ/ር ኢትዮጲያን ይጠብቅ፡፡ እትዮጲያ እጆቹን ወደ እ/ር ትዘርጋ ፡፡ እናንተንም እ/ር ይባርካችሁ፡፡
ሚኪያስ ካሳሁን

16. it’s the best work for the new generation.

17. እውነት ይህን ነገር ደርግ ነው የፈጸመው ወይ ሴጣን ነው? እውነትም የሰው ልጅ ሳይሆን ሴጣን ነው የፈጸመው፡፡
RUB

18. ዳግም አንጨካከን አንድ እንሁን፡፡
Amele

19. ከእንግዲህ እንደዚህ እንዳይፈጸም ለራሳችን ቃል እንግባ፡፡
Tamrat

20. Everybody should know the truth!
SW

21. ዳግም እንደዚህ አይነት ነገር ማየት እንፈልግም፡፡

22. እውን ደርግ ይህን አድርጔል? ካደረገ ሊደገም የማይገባው ስህተት ነው!

23. ለወጣቱ የሚጠቅም ቅርፅ ነው በጣም ደስ ይላል፡፡ እ/ር ይስጥልን ወጣትም ከዚህ አይተህ ለወደፊቱ ለሀገርህ ጥሩ ቅርፅ ጥለህ እንድቴድ እላለሁ አመሰግናለሁ፡፡

12/8/2002

1. አስከፊና አሳዛኝ ነገር ማየት ደስ አይልም፤ የሆነውን መረዳትና ለዳብም ስህተት አለመ
ጋለጥ ግን ወሳኝ ነው፡፡

2. እ/ር ነፍሳቸውን በክብር ታስቀምጣት አሜን!!

3. ሰው ጨካኝ ነው፤ ይህን የታገሰው ፈጣሪ ግን………..

4. This is the past but not again.

5. May you all rest in peace?
Edom

13/8/2002

1. ለካ ደርግ እብደዚህ ጨካኝ ነበር?
H.N

2. ማይታለፍ የለ ይህም ታልፏል፡፡ዛሬ በጣም አዝኛለሁ ነገር ግን ዛሬ ይህ ታሪክ በጭራሽ አይደገምም!!
F.F

3. በጣም አሳዛኝ ታሪክ ነው በየነው ነገር በጣም አዝነናል እንዳይደገም በጋራ እንስራ!!!

14/8/2002

1. ልዑል እግዚአብሔር ነፍሳችሁን ይማረው፡፡

2. በነበር መቅረት ያለበት፤መደገም የማይኖርበት፤ በአብዛኛው የወቅቱ ወጣት ቆራጥ ተጋድሎና ለዛሬው ሰላምና ዲሚክራሲ ድርሻውን ያበረከተ ድንቅ የሞት ሽረት ትግል ዘላለማዊ ክብር ለተሰው ሰማዕታት፡፡
ሰለሞን ግደይ

3. ይህ የታሪከ ማስታወሻ ለልጆቻችን መስታወት ማሳያ ነው፡፡

4. ትልቅ የታሪክ ስራ ለመታሰቢያ አሰሪዎች፡፡

5. በእውነተኛ ትግል የተሰውትን ሰማዕታት ነፍስ እ/ር ያስብ!!
T.G

6. ይህ አይነቱን የግፍ አገዛዝና ጨካኝ ስርአት ዳግም በሀገራችን እንዳይደገም ወጣቱ የበኩ ሉን ድርሻ ለመወጣት ይህን የዲሞክራሲ ስርአት ከመጠበቅና ከማጎልበት አንጻር ድር ሻውን መወጣትና ይህን ስርአት ለመድገም የሚቃትቱትን አጥብቆ መታገል ይጠበቅበታል ፡፡
አለምነሽ ወ/ማርያም

7. ብዙ ነገር ተምሬበታለሁ፡፡
E.T

8. በጭንቅላት ይገዛ የዚህ አይነቱ ጭካኔ ለምን አስፈለገ? በፍቅር በሰላም መግዛት እየተቻለ እንደ አሁኑ!!
ማርታ ሰይድ