Content on this page requires a newer version of Adobe Flash Player.

Get Adobe Flash player

16/8/2002

1. የእህቴን የውብሳሽን ነፍስ ይማርልኝ የሁሉንም ሰማዕታት ነፍሳቸውን ይማረው፡፡ ይህን መታሰቢያ ላቌቌሙ ለኢትዮጲያ ሕዝቦች አመሰግናለሁ፡፡ የሞቱት ሰዎች ግን ስማቸው ይጻፍበት እላለሁ፡፡
ባዩሽ እንዳላማው

2. እናንተ ብታልፉም ታሪካችሁ ዘላለማዊ ፤ሞታችሁም ህያውነት ነው፡፡ ለዚህች ሀገርና ህዝብ የከፈላችሁት መስዋትነት በአሁኑ ትውልድ አይን ሲታይ ሚዛኑ ላቅ ያለ ነው፡፡ ሞትንም ግፍና ጭቆናን የሚጠላ ትውልድና መንግስት እንዲሰጠን እ/ር ይርዳን፡፡ ያለፈው ዘመን አይደገም አዎ አይደገም!!
ወሰን

3. የደርግ ግፍ በዚህ ሙዚየም ብቻ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ በየዋና ከተሞቹ ሌላ ሙዚየም ለመገንባት መረጃ ለማስቀመጥ ያበርታችሁ፡፡
ዳዊት ፀሐዬ

4. በዚህ ትውልድ ላይ ሆነን ስለ እናንተ ስናስብ እናዝናለን እንደነቃለንም፡፡ ለሀገር ክብርና ፍቅር መስዋት በመሆን ያለፈ ድንቅ ትውልድ፡፡
ሳምሶን ፀጋዬ

5. ደርግን ስለጣልክልን እጅግ በጣም እናመሰግናለን፡፡
ወጣቶች

6. የንጹሀን ደም ዛሬ ለኛ ነፃነት ሆኖናል፡፡ ክብር ለንጹሀን ሰማዕታት እና በናንተ ኮራን የናንተ ለኛ ዋጋ አለው፡፡
ሀብታሙ መላክ

7. በትንሹም ቢሆን የናቴን ሰቀቀን ተሳቅቄዋለሁለለ
ሰለሞን ገ/ክርቶስ

8. ይህ የማይደገምባትን ኢትዮጲያ እንሻለን፡፡
በረከት ካሌብ

9. ምን ብዬ እንደምጽፍ ቃላት ያጥረኛል! ግን በቃ!!!
Benti

10. ያየሁት ነገር ሁሉ ያለፈው ታሪክ በዚህን ቀን ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡ ለሰማዕታቱም ከልብ አዝኛለሁ፡፡ ይህንን ሙዚየም ላዘጋጁትም አመሰግናለሁ፡፡
ጎበና በሪ

17/8/2002

1. በደርግ ዘመን ወጥቶ የጠፋው ወንድሜን ሀዘን በዚህ ሙዚየም ጽናት እግኝቻለሁ፡፡
H.T
Never, ever again

2. ያንጊዜ የነበረውን ቁልጭ ባለ መልኩ አኑን ስላየሁት ያለሁበትን ጊዜ አመሰገንኩ፡፡እጅግ በጣም የሚያሳዝን ታሪክ ነው፡፡ አይደገምም!!!

3. አጎቴን በአካል አላውቀውም ታሪኩ ግን ሕያው መሆኑን በዚህ ሙዚየም ተረድቻለሁ፡፡
Fidel Hagos

4. የእልቂት ዘመኑ ይዘጋ!!

5. የሙዚየሙ መገንባት በጣም ይደነቃል፡፡ አሁን ሰማን፤ አየን፤ አነበብን፤ ግን ይህ ሁሉ እንዳይደገም ምን እናድርግ? እባካችሁ እንስማማ እንፋቀር ያለው ዕድል ሰልጆቼ ማሳወቅ
ብቻ ነው!!

18/8/2002

1. በሀገራችን ተከስቶ የነበረውን ግፍ ወጣቱ ትውልድ ሁሉ ሊጎበኘው እንደሚገባ እና ይህ ድርጊትም እንዳይደገም ወጣቱ ሀላፊነት እንዳለበት ተሰምቶኛል!!
TLT.

2. እኛ በዚህ ትውልድ ላይ ሆነን የእናንተን ጥንካሬ ተምረንበታል፡፡
ወንድወሰን አበበ

3. ወጣት ሆይ! ይህ የግፍና አፈና አገዛዝ እንዳይደገም ከፈለግህ/ሽ ሀገርህን/ሽ በነቃት ጠብቃት፡፡

4. ያንን አሳዛኝና አስከፊ ዘመን በሀገራችን አይመልሰው የተሰውትንም ነፍስ ይማር፡፡
አስረስ

5. የተሰውትን ሰማእታት ነፍሳቸውን እ/ረ ይማርልን እርስ በርስ የመተሳሰብ ፍቅር ይስጠን፡፡
ያኔት፣ገሊላ እና እስከዳር

6. አምላክ ይህንን አስከፊ ግዜ አይመልሰው፡፡
Hanival

7. እውነትም መቼም አይደገም
Emy

8. Never and Ever Again.
A.M

9. ይህንን ላደረገልን ኢህአዴግ ዛሬም ነገም ሁሌም ከጎኑ ነኝ ያንን አምባገነን መንግስት አሸንፎ ከመጣበት ቀን ጀምሮ ከፍተኛ ልማት የሰራውን ኢህአዴግ ነው፡፡

ምርጫዬ

10. ይህ እንዳይደገም ምን አስበዋል?

11. የአሁን ወጣት በጣም እድለኛ ነን!!

12. እ/ር ሰዚች ቀን ስላደረስከን እናመስግናለን፡፡

13. ይህ ነገር እንዲደገም አልፈልግም በጣም እዛኛለሁ፡፡
ሄኖከ ዘሪሁን

14. ዛሬ ወጣቱ ምንም ችግር የለበትም የቀድሞ ወጣቶች በደማቸው ችግራችንን ቀርፎልናል፡፡

21/8/2002

1. ይህ በጣም ጥሩ ማስታወሻ ነው፡፡አሁን ካለው ትውልድ ጥሩ ትምህርት ይሆነዋል ምክንያቱም ይህንን አሰቃቂ ድርጊት በወገኑ ላይ ለመፈጸም ህሊናው አይፈቅድለትም፡፡
Helen G/Egziabeher
Hiwot Nigusse

2. ይሄንን ድርጊት የፈጸማችሁ የሰው ፍርድ ብቻ ሳይሆን የእ/ር ፍርድ እየጠበቃችሁ ነው፡፡ ለቀሪዎች ወጣቶ ከባለፈው ድርጊት ተምረን ፍቅር ይኑረን፡፡
God Bless You!!
Kebrom M.

3. ግን ለምን?
C.A

4. ይህን ድርጊት ፈፅማችሁ በህይወት ያላችሁም ያለፋችሁም ታሪክም፤ትውልድም፤ ነፍሳችሁም በሰማይ አይድላት፡፡ በምድርም ዋጋችሁን ተቀበሉ፡፡ የረገፈው የወጣት አፅም
ይፋረዳችሁ! እትዮጲያ ግን ያልጣለሽን አምላክ አመስግኚ፡፡ ያተረፍከን መንግስት ሆይ እድሜህን ያርዝመው፡፡ ክብር ለተሰው ሰማዕታት
Rahel Ade

5. ያለፈው ዘመን ይበቃል ነፍሳችሁን በመንግስተ ሰማያት እ/ር ያሳርፈው፡፡
ያለው ይብቃ

6. ባየሁት ነገር በጣም አሳዝኖኛል ዳግመኛ በኢትዮጲያ ታሪክ ውስጥ የማይደገም ሆኖ ይለፍማ…..
ይርጋለም ዋናው
እና
ኤልሳቤጥ ንጋቴ

7. በእውነት! ይህን ወንጀል በአገራችን ህዝብ ላይ እንዳይደገም ለራሳችን ቃል መግባት አለብን ብዬ አስባለሁ!! በበኩሌ ቃል እገባለሁ፡፡
ፍሰሐዬ ገብራይ

8. እ/ር ሆይ ይህ የተፈጸመው ኢ.ሰብአዊ ጭፍጨፋ ዳግም በሰው ልጆች ዘንድ እንዳይደገም በቸርነትህ እርዳን፡
ገ/ሔር አረጋዊ

9. እወነትም በአገራችን ተፈጽሟል? በጣም ያሳዝናል እንዳይደገም፡፡
ንጉሴ ተካ

10. የቀረቡት መረጃዎች ጥሩ ግንዛቤ የሚሰጡ ቢሆንም ገና ብዙ በጣም ብዙ የተፈጸሙ ግፎች ይቀራሉ፡፡ በርትታችሁ በቅርቡ ለእይታ በሚቀርብ መልኩ እዘጋጁት፡፡ ይህም ትውልድ
ተምሮበት ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይሄድ ይጠንቀቅ፡፡
T.A.K

22/8/2002

1. የርሱ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን እነዚህን በግፍ የተጨፈጨፉት እ/ር ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን፡፡

2. እግዚአብሔር ሆይ እባክህ ከዚህሰውረን ጌታ አዋቂ ነው ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡

3. በአየሁት ነገር በጣም ተሰማኝ አልቅሽ አልቅሽ አለኝ ግን አላለቀስኩም እነዚህ ሰማዕታት ህያው ናቸው፡፡ መቸም መቸም እንዳይደገም፡፡
L.W

4. እማማ እንደወጣ የቀረውን ዮሴፍ ሀዘን ልብሶትን ሳይቀይሩ በሕይወት ላለፉት የምስራቅ እናት ይህንን ቢያዩ ምን ያህል ሀዘኑ ይቀሎት ይሆን?
አበራ ተመስገን

5. የደርግ መንግስት በጣም ጨካኝና አረመኔ መንግስት ነው፡፡ መቼም የትም እንዴትም እንዳይደገም እባካችሁ፡፡
አቤል ለማ( ኪያ)

6. የተማሩ መሪዎች ለአሁኗና ለወደፊቷ ኢትዮጲያ እመኛለሁ፡፡ እስካሁን ድረስ ለተደረገውና እየተደረገ ላለው አዝናለሁ፡፡

7. ባየነው ነገር ልባችን ተነካ፡፡
F.M

8. በደርግ የነበረው ጭርጨፋ ልቤን ነክቶታል፡፡

9. በልጅነት አእምሮዬ ጠባሳ ትቶ የሔደውን ዘመን ደግሞ አስታወስኩት፡፡ ብርግጥም ያ ድርጊት ፈጽሞ እንዳይደገም፡፡
ሣሚኤል

10. ለቤተሰቦቻቸውና ለመላ ጔደኖቻቸው መጽናናትን ይስጣቸው፡፡
C.Z

11. መቼም የትም እንዳይደገም ሁሉም የበኩሉን ያድርግ፡፡
ገኒ

23/8/2002

1. ስለዛ ስላለፈው አሳዛኝና አሰቃቂ ጊዜ በልጅነት አይምሮዬ ሳስበው ሁልጊዜ ሀዘን ይጭርብኛል ምክኒያቱም ቤተሰቦቻችንና ብዙ ወገኖቻችንን አጥተናል፡፡ አሁን ደግሞ በዚህ ዘመን ያለን ኢትዮጲያውያን ወገኖቼ የአለፈውን ዘመን እየረሳን አሁን ይበልጥ እየተግባባንና እየተፋቀርን የሰለጠነችና ለኢትዮጲያውያን ወገኖቻችን የምትጠቅምና የበለፅገች ኢትዮጲያን ማየት ነው ሁልጊዜ ምኞቴና ህልሜ እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይባርክ፡፡
ሚኪ

2. የትኛውም መንግስት ዘለዓለማዊ አይደለም በሚያልፍ ሕይወት የማያልፈውን ታሪክ ሰርተው ይሙቱ፡፡ መቸም የትም አይደገም
ሳሊሀ

3. በነበረው ስራ እኔ በጣም አዝኛለሁ፡፡
መዲ

4. ይህን ታሪክ በመጽሐፍ ብቻ ለሚያውቀው ትውልድ እንዲህ በግልጽ የነበረውን አስከፊ ስርዓት በማየቴ ደስተኛ ነኝ ግን ከዚህ በተሻለ ያለው መንግስት ይህ እንዳይደገም መስራት
አለበት፡፡

5. መቸም ሁሉም አልፏል፡፡ መቸም መቸም አይደገም ብቻ ሳይሆን መቸም አይታሰብ በእመቤታችን ማርያም ብላችሁ፡፡
አለም

6. ባለማወቃቸው የማያውቁ አጥፍተውናል፡፡ ለወደፊቱስ? አይደገምም!! የማያውቅን ለማሳወቅ ተግተህ ስራ! ዘግናኝ ነው!! ታሪክ እራሱን አንዳይደግም ለወደፈቱ ከዚህ እንማር!! እውቱን ጌታ ያውቃል ፡፡ የዛሬስ?

7. እጅግ አሳዝኝና አስነዋሪ ተግባር ነው፡፡ በተሰራው በጣም አዝኛለሁ፡፡ ግን ከዚህ ምን እንማራለን ያለፈውን ትተን አሁን ያለንበትን ማሰብ ተገቢ ነው የዚህ አይነት ድርጊት አሁን እንዳይደረግ መጠንቀቅ አለብን፡፡

8. ለሁሉም ጊዜ አለው አሁንስ? ምን እየተደረገ ነው ዋ!!

9. ጀግኖች የትግራይ ልጆች ለዚህ ሰላም ተዋግታችሁ ይሁንን የጔደኞቻችሁ ሐውልት ሳታዩ በረሀ ላይ በመቅረታችሁ በጣም ያሳዝናል፡፡ መጨው ትውልድ ከዚ የተሻለ ሊያስተምረው
የሚችል ለነር ያለ አይመስለኘም፡፡
ፍጹም

10. ምን ተማርን አሁንስ? ወንድሞቻችን በተሰውት ሰላምን እግኝተናል፡፡

11. እግ/ርን የማይፈራ ህዝብ ይጠፋል፡፡
H.B

12. ሁሉም በግዜው ያለውን ነው የሚያመሰግነው፡፡ So No. Difference B/N the elder and now!

13. አብዲ ጀማል በጣም አሳዝኖኛል፡፡ መቼም እንዳይደገም፡፡

14. የተሰራው ስራ እጅግ አሰደሳች ነው፡፡ ግን አንዳንድ ጉድለቶች አሉበት ለምሳሴ በዚ በር
ያለው አፈር አልገባኝም፡፡

24/8/2002

1. እነሱ ለአገራችው ነፃነት ተሰው! እኛስ ለሀገራችን ምን ሰራን?

2. ባየሁት ነገር እጅግ በጣም አዝኛለሁ እስካሁን በወሬ ብቻ ነበር የምሰማው በአይኔ በማየቴ ተደስቻለሁ፡፡
አማኑኤል አሰግድ

3. በግዜው የተደረገው አሳዛኝ ግድያ እጅግ በጣም በጣም ያሳዝናል፡፡

4. የሰው ልጅ ጨካኝ ነው፡፡ እግዚአብሔር ነፍሳችሁን ያኑራት እነሱንም ይቅር ይበላቸው፡፡ ሀዘኔ ግን ………….

5. መሪዎቻችን ስልጣን በመውደዳቸውና አንለቅም በማለታቸው ይህ ሁሉ ግፍ ተፈፀመ ወደፊት እግዜር ይጠብቀን!!

6. ላለመደገሙ እርግጣኛ መሆን አይቻልም፡፡

7. እ/ር ይህንን ነገር በምድራችን ዳግመኛ አያመጣውም እትዮጲያን እ/ር እጆቿን ታነሳለችና፡፡
ኤፍሬም

8. እዚች ምድር ላይ ስንት አመት ነው የምንኖረው? አናውቀውም ምናለ በዚህች ምድር ስንኖር መልካም ነገር ሰርተን ብናልፍ!!!
M.A

9. Hope it will never happen again.

10. Never, Ever Again.
Alex & Filli

27/8/2002

1. መቼም አይደገም እሺ?
TS.

2. ባየነው ነገር እጅግ በጣም አዘንን በሆንም ልፋታችን ከንቱ አልቀረም በአገራችን ዲሞክራሲ እንዲመጣ ትልቁን ድርሻ ተወጥተዋል፡፡ ሁሌም አንረሳቸውም!
ከአፍረካ የጤና ኮሌጅ ተማሪዎች

3. እኔ በጣም ነው ያዘንኩት እኔ ከዚህ በፊት ብዙም ኢንፎርሜሽን የለኝም እና ይሄን ታሪክ የቀየረውን ኢህአዴግ አደንቀዋለሁ ይሄ ታሪክ እንዳይደገም፡፡

4. የዚህ አይነቱ ዳግም አይከሰት!!
ተማሪ A.

5. ሰማዕታት ለሀገራችው ሕይወትን እንደገደሉ ሁሉ እኛም ለልማት እንትጋ!!

6. ማሽኑ በመገኘቱ በጣም ደስ ብሎኛል ያገኘው ጎበዝ ሰው ነው፡፡

7. ዛሬ ባየነው ነገር እጅግ ከማዘናችን በላይ በተሰራላቸው ሐውልት ተደስተናል፡፡
ፌቨን

8. እግዚአብሔር የወደደውን አደረገ፡፡ የኔ ጓደኖችና ወንድሚቼ በ 1997 ውንጌት ት/ቤት በስቃይ ሞተውብኛልና የነሱስ አፅም የት ይሆን??

29/8/2002

1. ያየሁት ነገር በጣም አሳዛኝ ነው ጭካኔ የተሞላበትን አገዛዝ የጣለልንን እ/ር የተመሰገነ ይሁን፡፡
አዳነች ግርማ

2. ያለፈው አለፈ ዋናው ነገን የተሻለ ለማድረግ መጣር ነው፡፡ የተሻለች ኢትዮጲያ እንድትኖረን እ/ር ይርዳን፡፡
አብይ ሐይሉ

3. ሁሉም ነገር ያልፋል፡፡ ባየሁት ነገር አዝኛለሁ፡ በዛ ጊዜ ነፍስ ባላውቅም በዛ አገዛዝ ምክንያት ባጣነው አባታችን እና በዚህም እናታችን የደረሰባትን ትንሽም ቢሆን ስቃይ
የሚባለውን ነገር እንዳስብ አድርጎኛል፡፡ ሁሌም እናስብሀለን፡፡
ሻምበል ግርማ ወ/አገኘሁ
ፌቨን ግርማ

4. እንባችንም ፈሰሰ ወገኖቻችንም ሞቱ እመታቱም አለፈ ያ ክፉ ጊዜ ሄደ፡፡ አሁን ግን ያ አስከፊ ጊዜ እንዳይደገም ለአምላካችን በጾም በጸሎት ኢትዮጲያ መልካም ብልፅግና
እንዲገጥማት ዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡
R.G

5. ባየሁት ነገር በጣም ልቤ ተነክቷል ለካ ወገን በወገኑም እንዲህ ይጨክናል፡፡ በጣም ያሳዝናል፡፡ ግን ለምን?? ነፍሳችሁን እ/ር ይማረው፡፡
አብይ ( ከጅማ )

6. ሰማዕትነታችሁ በሰማይ ጥቱ ዋጋ ይሁንላችሁ፡፡ ለእኛም በምድር ሁሌም ሰላም!!!!
ሳሙኤል ለማ

7. ባየሁት ነገር ልቤ የተነካ መሆኑን እየተናገርኩ ወጣቱ ትውልድ የዚህ አይነቱ እኩይ ተግባር ሰለባ እንዳይሆን ከስሜታዊነት ማስተዋልን መምረጥ አለበት እላለሁ፡፡
አዲሱ በዛብህ

8. ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ነው፡፡ መጥፎ ታሪክ አይደገም!! ያሳዝናል!!

9. ባየሁት ነገር በጣም ተደናግጫለሁ ለሞቱት መፅናናትን እመኛለሁ፡፡ ለውድ ቤተሰቦች ለሙቱባቸው መፅናናት እመኛለሁ፡፡
ደርባባው ሀ/ማርያም

30/8/2002

1. በምንም ምክንያት የአንድም ሰው ሕይወት መቼም ቢሆን አያልፍም፡፡
ሙሉ

2. መጥፎ ድርጊት አልፏል፡፡ እንዳይደገም እላለሁ፡፡
እስራኤል

3. በጊዜው ምንም ስለማላስታውስ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡
ሜሮን ወ/ሰማያት

4. Thank your for showing me the horror of this dictatorship Never forget. Let It happens again. You are beautiful People.
Ronan Downs
(Ireland) USA

5. በጣም የሚያሳዝን ድርጊት ነው፡፡ ሰው ላይ እንዲህ አይነት አሰቃቂ ድርጊት!! ይህ ሁኔታ ዳግም መደገም የለበትም፡፡

6. ያለፈው አልፏል ዳግም እንዳይደገም፡፡
ዮናታን መርጊያ እና ብዙአየሁ

7. መችም ሊደገም የማይገባው አስነዋሪ ድርጊት!!
አስራት

8. ባየሁት ነገር በጣም ነው ያዘንኩት እ/ር ሰተሰውት ወንድሞቼና እህቶቼ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልኝ፡፡
E.C

9. ባየሁት ነገር እጅግ በጣም አዝኛለሁ፡፡ ለሞቱት ወገኖቻችን እ/ር ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን፡፡
Alemeshet

10. ካለፈው ለመማር መሞከር እንጅ መድገሙ አስተዋጽኦ የለውምና የአሁን መንግስታት ላለመድገም መጣር አለበት፡፡

11. የሞተ ወይም ሕይወት የሌለው ሰው ባለማየቴ ተደስቻለሁ፡፡
ሰናይት አበራ

12. Sorry በጣም ነው ያዘንኩት ለካስ በጣም ተጎድተናል ባለፉት ዘመናቶች፡፡ በእውነት የማላውቀው ስሜት ነው የተሰማኝ አዝኛለሁ፡፡ በውስጤ ለወደፊቷ ሀገሬ በጣም ጥሩ
የሆነ ሀላፊነት እንዲሰማኝ ነው በውስጤ የጫረብኝ!! ብቻ ስላለፉት ነገሮች ሁሉ በጣም አዝኛለሁ!!! ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!
ምህረቱ ረጋሳ ( ከሻሸመኔ )

13. ለትውልድ ሁሉ ብርሀን ሆናችኋል፡፡ ሁሌም አስባችኋለሁ፡፡
ተሜወርቅ

14. የእ/ያ ሕዝብ ሆይ! ከንደዚህ ዓይነቱ አሰቃቂ ድርጊት ይሰውረን፡፡ ደም መላሾቼ ናችሁ አከብራችኋለሁ፡፡

15. እ/ር ነፍሳችሁን በገነት ያኑረው፡፡
ምህረት ብርሀኑ

16. በእነሱ ምት እኛ ኖርን እ/ት ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን፡፡
ኤደን አብዱ

17. እ/ር ኢትዮጲያን ይባርክ!!

18. የሞተው ሰበጎ ነው፡፡

19. ሕፃናቱስ ለምን?

20. እ/ር የሞቱትን ነፍስ ይማርልን!!
Nardos.N

21. ትናንት ያለፈውን እውነታ አልፌ ዛሬ ይህን ማየቴ እ/ርን አመሰግናለሁ፡፡

22. ዛሬ ይህን ብለናል ነገስ?

23. እ/ር ኢትዮጲያን ይጠብቅ በጣም አስቀያሚ ነገር ነው! አይደገም እባካችሁ፡፡ እ/ር ነፍሳችሁን ይማረው፡፡

24. በቀይ ሽብር የተገደሉትን ሁሌም እናስባቸዋለ፡፡ ለእኛ ነፃነት ሲሉ ተጋድለው፤እውነት እውነት ይህ ታሪክ ዛሬም ነገም እንዳይደገም፡፡
B.H (ከአርሲ ነገሌ ከተማ ወጣቶች ማህበር)

25. በቀይ ሽብር የተገደሉትን ለዘላለም እናስባችኋለን፡፡ ዳግም ይሄን ነገር ማየት አንፈልግም
ጌታቸው ንጉሴ

26. ድህነትን ማሸነፍ ለምን መደርግ ግፍ በላይ ይከብደናል?

27. በቀይ ሽብር ያለቁትን ወገኖቻችንን ሁሌም እናስባቸዋለን ምክንያቱም ለእኛ መልካም ነገር አርገውልናልና፡፡ ከዚህ በኋላ አይደገምም፡፡ አላማችሁ ሁሌም ዘላለማዊ ይሆናል
ቲቲ ሐማዶ
ከአርሲ ነገሌ ( ነጋት ሁለገብ ወ.ማ)

28. በቀይ ሽብር የሞቱትን ዘለዓለም እናስባችዋለን፡፡ የደርግ ስርዓት የመጨረሻ አሳፋሪ ስርዓት ለመሆኑ ይህ ትውልድ በሚገባ ሊገነዘበው ይችል ዘንድ ይህ ሐውልት አስተማሪ ነው፡፡
ሰለሞን ወርቁ

29. እኔ ሙዚየም ውስጥ ከተመለከትኳቸው ነገሮች እጅግ በጣም የተገነዘብኳቸው ነገሮች አሉ ስለዚህም እስተያየቴን በአጭሩ ገልጫለሁ፡፡

30. አምባገነኖች ዳግም እድዳይስፋፋ የሁላችንም ጥረት ይቀጥላል፡፡
ግርማ ፈይሳ

31. ለካ ለዚህች አገር እንዲህ አይነት መስዋዕት ተከፍሏል፡፡
ሙሉብርሀን

32. Must be one and for All!

33. በጣም ያሳዝናል፡፡
ሳሚ

34. ከአሁን በኋላስ በምን እርግጠኛ መሆን እንችላለን?

35. ደርግ በኢትዮጲያዊያን ላይ ያደረሰውን በደል ግፍ እግዚአብሔር አምላክ በቃችሁ በማለቱ ስሙ የተመሰገነ ይሁን፡፡
ዘነበ ዓለሙ

36. እዚህ ቦታ ያየሁት ነገር እቺን ሀገር ለማዳን የተደረገ መስዋትነት ነው፡፡ የተሰዋችሁ ታሪክ ያስታውሳችሁ!!
አብዲሳ

37. ይሄ እዚ ያየነው በእውነቱ ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም በዚህ አጋጣሚ አባቴን በፎቶ ሰላየሁት ደስ ብሎኛል፡፡ የሰባቴ ስም ጌታቸው ገ/ጊዮርጊስ ነበር እግዚአብሔር ነፍሱን ይባርክ፡፡
ሚኪያስ ጌታቸው

38. ኧረ በስመአብ በጣም የሚገርም ጭፍጨፋ ነው፡፡ ወጣት አልቆ የለ እንዴ፡፡ ሁለተኛ እንዳይደገም፡፡ይበቃል !!!
GIRUM

39. በዚህ አጋጣሚ ባለቤቴን የ 4 ልጆቼ አባት የልጆቼን አባት አቶ ጌታቸው ገ/ጊዮርጊስ ፎቶ በማየቴ ደስ ብሎኛል፡፡ እርሜንም አውጥቻለሁ፤አልቅሻለሁ፡፡ ይሄን መንግስት እግዚአብሄር ይባርከው ያቆየው ይሄን አሳይቶናልና፡፡ እናት የትነበርክ እንግዲህ እንደገና አይደገምም

40. ይህ ሙዚየም በጣም አስተማሪ የሆነና ትምህርት ሰጪ መሆኑ ጠቅሞናል፡፡ በተለይ በአሁኑ ትውልድ በጣም ጠቃሚና አስፈላጊ ነው፡፡ከዚህ የበለጠ ለማጠናከር ተጨማሪ
የሆኑ መረጃዎች እንዲገቡ እንላለን፡፡ እናመሰግናለን፡፡

41. Will never happen again!
Biruk

42. በጣም ያሳዝናል፡፡ ይህ በነሱ የተደረገው ግፍ ይብቃ! ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልኝ አዝኛለሁ በጣም፡፡ ድጋሚ እንዳይደገም፡፡
አቤኔዘር ሰለሞን

43. They are a hero in Ethiopia history for all of us!

44. We can learn from this museum to this generation!

45. እንኳንም አለፈ!

46. ዳግም እንዳይደገም፡፡ በጣም ያሳዝናል ይህ መንግስት ይህን የአሰቃቂ ነገር ተዋግቶ በዚህ ትውልድ ይህንን እንድናውቅ ስለረዳን እናመሰግናለን፡፡ዳግም እንዳይደገም በጣም
የሚያሳዝን ወቅት ነበር፡፡ ሙዚየሙ መዘጋት የለበትም ክፍት መሆን አለበት፡፡

47. ነፍሳቸው በገነት ያስቀምጥልን፡፡

48. በውነቱ በፊት ከነበረኝ ግንዛቤ የበለጠ በመረዳቴ የነበረው የጊዜው አስከፊነትና የግንዛቤ ማነስ አሳዝኖኛል፡፡ ሕይወታቸውን መስዋት ላረጉ ሁሉ እግዚአብሔር ያስባቸው ነፍሳቸውን በገነት ያኑረው፡፡
W.Z.A.A

49. እግዚአብሔር የሞቱትን ነፍሳቸውን ይማር፡፡ ይህ አስቀያሚና አሳዛኝ ድርጊት ዳግም እንዳይደገም፡፡

50. ይህ አስቀያሚና አሳዛኝ ድርጊት ዳግም እንዳይደገም፡፡

51. በጣም አስተማሪ ሙዚየም ነው ለቀሪው ትውልድ ይህንን ድርጊት የፈጸሙትን እግዜር ይፍረድባቸው፡፡

52. በጣም አሳዛኝ ታሪክ ነው! አላህ ይህን ታሪክ ወደ ሀገራችን እንዳይመልስ አሜን!

53. ደግሞም ለኛ ለሕፃናት ፈጽሞ አይደገምም፡፡ እንዳይደገም እግዚአብሔር ይርዳን! አሜን አብርሀም ጥላሁን

54. If there is a will, there is a way.

55. We all hope this “Bloody” history will never repeat itself in this country. “God Bless Ethiopia”
H. RAJA (INDIA)

56. እጅግ በጣም ያሳዝናል፡፡ እ/ር አምላክ የሞቱትን ነፍስ ይማርልን አቤቱ አምላኬ ሆይ ዳግመኛ የዚሕን አይነት እልቂት አታምጣብን፡፡
Yohannes

57. አሳዛኝ ነው! አሰቃቂ ነው!! ነገር ግን እንዳይደገም፡፡

58. History is never deleted! Never, ever again!
Mahari

59. Yes I have seen, but how do we know that the evidence are original and true? I don’t think that is true; please tried to have the original evidence.
S.A

60. ባየሁት ነገር በጣም አዝኛለሁ፡፡ አንድ ነገር ከዚህ የምንረዳው ነገር ቢኖር ታሪክ ታሪክ ሆኖ እሰማለሁን ነው፡፡
S.B.H

61. አይ! አይቻለሁ በጣም ማዘኔን በዕንባዬ አልገልጽም፡፡ ይህ እንዳይደገም ግን ሁልጊዜ በማሰብ እንደዚህ አይነት ሁኔታ እንዳይደገም ኢትዮጲያ እጆቿን ትዘረጋለች፡፡ ሰው ምን አቅም አለው፡፡
S.W

62. እኛ ኢትዮጲያውያን እርስ በርሳቸው መተራረድን ግን ለምን? ዛሬስ ?

63. መዋደድ ስንችል መጠፋፋት፤አብረን መኖር ስንችል መገዳደል ለምን? ትምህርት ይሁነን ጌታ ሆይ ነፍሳቸውን ማር እባክህ?

64. ዛሬ አኛ ምን ተማርን! ይቅርታ ታላቅ ነው፡፡ ዳግም አይደገምም፡፡ በሀገሬ ኢትዮጲያ!
ጎይቶም

65. እናንተ በተሰዋችሁበት ምድር ላይ እኔ መቆሜን ፈራሁት፡፡
ተሾመ

66. በእውነት ይህ አሳዛኝ ነው፡፡ ይገርማል፡፡እንዳይደገም፡፡
ሚሊዮን ፤ ሔኖክ

67. ለመጪው ትውልድ እንኳን ማየት መስማት አያስፈልግም፡፡

68. ሁሌም በልባችን ናችሁ፡፡

69. Glory for human being, human rights is universal & given form God must Not happen again.
F.H

70. ሰውን እንደዚህ መግደል ሀጢያት ነው ለነፃነት የሞቱ ሁልጊዜ ሲታወሱ ይኖራሉ፤፤
አብይ ፍርዱ

71. አይ ሰው!!! እንኳን አልተፈጠርኩ፡፡
አስመላሽ

72. በጣም ያሳዝናል ብዙ ጊዜ በዓለማችን ላይ የዚህ አይነት ክስተት ተመልክተናል፡፡ ሰው ከታሪክ ብዙም ስለማይማር እግዚአብሔር ያስተምረው፡፡
አበራ በየነ

73. የሰው ልጅ ክብር ነበርክ ታዲያ???

74. በጣም አስቸጋሪ ግዜ እንደታለፈ ነው የማስበው፡፡ ወደፊት ከእንደዚህ አይነት ጥፋት አንድ ነገር አስተምሮን ያለፈ ይመስለኛል፡፡

75. ምንም እንኳ ፈራሽ ብትሆኑም የብዕራችሁ እሙን ታሪከ ለተተኪው ትውልድ ይቀላል፡፡ እግዚአብሔር ነፍሳችሁን ይማር፡፡

76. እግዚአብሔር ነፍሳችሁን ይማረው የወንድሜን አፅም ያለማግኘታችን እስካሁን ድረስ ብንፀፀትም ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ነፍስ ላጠፉት እንፋረዳቸዋለን፡፡ ካሉበት ቦታ መጥተው ይፈረድባቸው፡፡መንግስቱ ይፈረድበት ይሙት፡፡
አበበ አለሙ

77. እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በገነት ያስገባው ወንድሞቼ፤ እህቶቼ ትግላችሁ በከንቱ አልቀረም ፍሬ አፍርቷል፡፡
ሙሉጌታ በየነ

78. እግዚአብሔር አምላክ በግፍ ለተሰው ነፍሳቸውን ይማርልን፡፡ ዘመኑ የአንድነትና የፍቅር የሰላም ይሁንልን፡፡
ስለሺ አያሌው

79. ሁሉም ነገር ሆነ እግዚአብሔር ታላቅ ነውና ነፍሳችሁን በገነት ያኑርልን፡፡ በኢትዮጲያ ታሪክ ግን ድጋሚ አይፈጸምም፡፡
ጌዲዮን ተዘራ
ዮናታን ሽብሬ
ዮሴፍ ወርቁ

80. ፎቶግራፋቸውንና አፅማቸውን በክብር ላኖራችሁ ኢትዮጲያውያን እ/ር ይስጣችሁ፡፡
Mekasha Zeru

81. ከእንደዚህ አይነቱ ግፍና በደል ወገን ብዙ ሊማርና ሊያስብ ይገባል፡፡
ከሊፋ ከድር

82. በእርግጥ እግዚአብሔር የእነዚህን ሰማዕታት ነፍስ በገነት እንዲያኖር መማፀን ሁሉም የበኩሉን ሊያርግ ይገባል፡፡ በሀገርና በወገን የተፈጸመ ይህ ግፍ ታላቅ ትምህርትም
ሆኖ፡፡ አዎ መቸም የትም መደገም አይኖርበትም፡፡
ክንፈ ገብርኤል

83. እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን ይማርልን፡፡ ይህ ድርጊት ዳግመኛ እንዳይደገም በነሱ ይብቃ፡፡ ውድ ወንድማችን ማሞ ሰይፉ እንወድሀለን ብትኖርልን ጥሩ ነበር፡፡፡
እህቶችህ አበሩ እና ድንቅነሽ

84. እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳችሁን ይማር፡፡
ታሪኩ ደበበ

85. እግዚአብሔር ነፍሳችሁን ይምረዋል!!

86. ኦ! አምላኬ በፍጹም እንዳይደገም አድራ!!
ዋሲሁን ታደሰ

87. በጣም ዘግናኝ ግን ለወገንና ለሀገር የተከፈለ መስዕዋትነት!!

88. ውይ አጎቴ አቶ ክበበ ወ/ጻድቅ ጅማ መምህራን ማህበር የ1967 ዓ.ም የወዝአደር ሰልፍ ተሳታፊ የነበረ እና አጠቃላይ ለቀይ ሽብር ሰለባዎች ነፍሳቸውን ይማር፡፡ ለሁሉም ታሳታፊ፡፡
ሙላቱ አስታርቄ