Content on this page requires a newer version of Adobe Flash Player.

Get Adobe Flash player

1/9/2002

1. አምላኬ ሆይ! ዘግናኝ ድርጊት ነው የተሻለች ኢትዮጲያን ለመገንባት እርዳን፡፡ ለመጪውም ትውልድ ቅን ልቦናን ስጥልን አሜን፡፡ መቼም መቼም እንዳይደገም!!!
መለሰ

2. እግዚአብሔር ሆይ! ዳግም እንደዚህ አይነት ድርጊት እንዳይደገም ኢትየጲያን ጠብቃት መሪዎችንም ባርክ፡፡
M.H

3. ከዚህ ጉድ ያመለጣችሁ ወይም በድርጊቱ የተሳተፋችሁ የዚያ ትውልድ አባላት ዛሬም አላችሁና ለልጆቻችሁ እንዳይደገም አስተምሩ!! ኢትዪጲያ ለዘላለም ትኑር!!

4. በዚያን ዘመን ብፈጠር ኖሮ ደርግን መታገሌ እርግጠኛ ነበረ፡፡

5. ሰዎች እንዲያደርጉብህ የማትፈልገውን አንተም አታድርግ፡፡

6. አሁን የሆነው ሁሉ በሀገራችን የነበረውን አረመኔያዊ አስተዳደር ያስወገደ በመሆኑ በጣም የሚያስደስት ነው፡፡ ያ ጊዜ በእውነት ጨለማ ነበር፡፡ ወንድማገኝ ሰለሞን

7. ይህ ነገር መቼም እንዳይደገም እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር፡፡ ይሄ ነገር መቼም ቢሆን በምድሬ ላይ እኛ እስካለን ድረስ አይደገምም፡፡ ህይወት እንዲ ሞት አይሆንም፡፡
T.A

8. እንደዚህ አይነት ጨካኝ መንግስት መጥፋቱና ለዛ ዕድል ተጋላጭ ለመሆን በዛ ዘመን ባለመ ወለዴ እድለኛ ነኝ፡፡ የደርግ መንግስት የሰው አስተዳደር ሳይሆን ከሰማይ የተጣለ ሰይጣን ነው፡፡ ሰማዕታቱ አልሞቱም ስራቸው ለዘላለም ይኖራል፡፡ አሁን ያለ መንግስት ለዘላለም ይኑር፡፡

9. እግዚአብሔር ከእንደዚህ አይነት ነገር ይሰውረን፡፡ በኛ አይደለም በሌላውም እንደዚህ አይነት ግፍ እንዳይደገም፡፡ God bless their life for their scarifications.
Q.M

2/9/2002

1. አባቴ ፅዋውን ቀምሷል፡፡ ግን እሱ አሁን አለ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡

2. ዛሬም ለኢትዮጲያ ትውልድን የሚተካ ትውልድ ያስፈልጋል!!!

3. ዳግመኛ እንዳይደገም!!!!
K.T
M.B
M.T
S.T

4. ይህ ሁላ ወጣት ባይቀጠፍ ኖሮ!!! እንዳይደገም፡፡

5. በእርግጥ ባየሁት ነገር በጣም ባዝንም፡፡ የተከፈለው መስዋትነት ፍሬ ማፍራቱ ለቤተሰ
ቦቻቸውና ለወገናቸው ያኮራሉ!!

6. ገና ያልተነገረለት ነው፡፡ ሌላ ሙዙየም ከማሰራታችን በፊት ለወደፊቱ ቆም ብለን
እናስብ፡፡

7. ነፍሳቸውን ሰውተው ነፃነት ለሰጡን እናመሰግናለን፡፡

8. እንደዚህ አይነት ግፍ ይዘገንናል ኢህአዴግን እግዚአብሔር ያንግሰው፡፡

3/9/2002

1. ቀደምት አባቶች የበኩላቸውን መስዋትነት ከፍለዋል መቸም የሚረሳ አይደለም፡፡ እኛ አዲሱ ትውልድ ደግሞ ለዚች ሀገር የራሳችን ደህንነት ታሪክየሚደረግሀላፊነትይጠበቅብናል፡፡ዘላለማዊ ክብር ለተሰው ጀግኖች ሰማዕታት

2. Bullshit, Bullshit, Bullshit derg regime!!

3. ዛሬ የሚፈለገው በፍቅር ሁሉን ነገር የሚያሸጋግር መንግሥታዊ አገዛዝ ያስፈልጋል ጦርነት አንፈልግም፡፡

4. እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይግዛት!!!

5. የባሰ አታምጣ ከዚህ በላይ አሳልፈናል ብዙ ስቃይ በዚህኛው ትውልድ እንዳይደገም ኢትዮጲያን ጠብቅ አምላክ ዘለዓለም!!

6. I am sorry about what I see inside the room, may god help Ethiopia not to appear such things again.
From A.A.U.

5/9/2002

1. የአገራችን ታሪክ ሁሌም የችግር እንዳይሆን እንድደማመጥ፡፡ ባለፈው ታሪክ ላይ አዲስ ታሪክ እንስራ መወቃቀስ ይቅር፡፡ ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር
ብርሀኑ

2. ኢህአዴግ በጣም አደንቃችኋለሁ፤ ደግሞም እወዳችኋለሁ ከዚህ የበለጠ እንደምትሰሩ ተስፋ አለን፡፡ እወነትም አይደገምም                                      
አብርሀም ሸፈራው

3. ስንጎበኝ ከነበርነው ውስጥ በአብዛኛችን ሳናውቀው በሐዘን ተውጠን በመሐል በሰፊው እንተነፍሳለን፡፡ ይህ አልፏል ከአሁን በኋላ ይህን የመሰለ ታሪክ እንዳይደገምየሁላችንምሀላፊነት ነው፡፡
ከእ/መንግሥት

4. ያለንን መንግሥት በፀጋ ተቀብለን ተሳስበን በፍቅር፤ ባንድነት በመተሳሰብ ካለፈው ታሪክ ዳግመኛ በኛ ላይ እንዳይደገም ስል በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ፡፡
አልጋነሽ

6/9/2002

1. ያለፈው አልፏል ይቅር እንባባል፤ አሁን እንኳን ከታሪክ እንማር፡፡

2. Even though we people seen a change, it should through peaceful way. I am so very feel about it,
A.A.U

3. አደራ የኢትዮጲያ ህዝብ ሆይ መቼም መቼም እንዳይደገም ሁሉም ያልፋል!!

4. የሰላም ታሪክ አውሪ ያድርገን፡፡

5. Show us that you are better than “those “
A.A.U

6. አስቸጋሪ ወቅት ነበር አለፈ፡፡ የማያልፍ የለም ከዚህ በኋላ ጥሩ ወቅት መጥቷል እንጠ ቀምበት፡፡

7. መቼም መቼም መቼም እንዳይደገም፡፡

8. ካለፈው እልቂት ትምህርት በመውሰድ የአሁኒ ትውልድ ነገሮችን በውይይት በፍቅር መፍታት ባህሉ ያድርግ፡፡
ሄቨን ግርማ

7/9/2002

1. ከዚህ በኋላ በኢትዮጲያ ምድር እንደዚህ አይነቱ ነገር እንዳይደገም እግዚአብሔር ኢትዮጲ ያውያንን በፍቅር ይባርክ፡፡ ያየነውን እንዳላየን ሆነን ይብቃ፡፡
B.M

2. ሰላምን የመሰለ ምን አለ?

3. በእግዚአብሔር ፍቅር ምድራችን ትባረክ ዘንድ እንዲሁም ያየነው እንዳይደገም ምኞቴ ነው፡፡

4. አልምዱሊላህ; It’s all over!!!

5. እጅግ በጣም ክቡት በሆነው የሰው ልጅ ላይ እንዲህ አይነት ግፍ መፈጸሙ የሚያሳዝን ቢሆንም ከአሁን በኋላ እንዲህ አይነት ግፍ እንዳይደገም እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ያግዝእላለሁ፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይባርክ ሰላም ለሁሉም

6. መቼም እንዲደገም አያስፈልግም አሁንም በቀል አይኑር ዛሬም ይቅር አንባባል ምህረት ማድረግ ይገባል እላለሁ!!

7. ይህ በኢትዮጲያ ተደረገ ብዬ ለማመን ከበደኝ ለካስ እንደዚህ አይነት ታሪክ አልፏል፡፡ መቼም እና የትም አይደገም፡፡

8. ሌላ ፍጥረት “ዘርህ “ሊሆን አይችልና ሁልጊዜ ለሰው ዘር ተጠንቀቅ!! ሳሙኤል ብርሀኔ ዛሬም አስታውስሀለሁ

9. ሁሌም ከአዕምሮዬ የማይጠፋ ክስተት፡፡ ከተመሪ ፍሬዘር አምሳሉ

9. አባታችን ለሞቱለት ሀገር እኛ ደግሞ ሰርተን እንለውጣት፡፡ ከተማሪ አይናቸው

9. ለዲሞክራሲ ሰማዕታት ለሆንከው ሰተስፋዬ ተፈሪ፤ ይህንን ሁሉ ስቃይህን አየሁ እጅግ ውስጤ ቢያዝንም አንተ ባታየውም እኔ በአንተ መስዋዕትነት ኮራሁ፡፡ አባቴ ባነተ ሀዘንእንደሞተ ሳስታውስ ግን ሁሌም ያመኛል፡፡
ወንድምህ ሰይፈ ተፈሪ

10. ይህ አይነት ታሪክ በህልምም ቢሆን አይደገም!! እግዜር ነፍሳችሁን በገነት ያኑራት፡፡ ልጅ ቃልኪዳን ወርቅነህ

11. ሁሌም ታሪክ ሰማዕታቱን ሲያስብ ይኖራል፡፡ የምዕታአመቱ ጀግኖች እውነትም ሁሉም የትም እንዳይደገም አደራ!!
ተኮላ ወርቁ

12. በሰማእታቱ ትግል የዲሞክራሲያችን መሰረት ተጣለ ክብር ለሰማእታት፡፡
ልጃችሁ ሞሮን ሀ/ልኡል

13. የሰዎች ሰብአዊ መብቶች አሁንም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ከመንግስት ጎን እንቆማለን፡፡ ህገመንግስቱንም እንጠብቃለን፡፡
ከተማሪ አስቻለው ተሰፋዬ

9/9/2002

1. ደርግ እንደዚህ ጨካኝ ነበር ለካስ?

2. ሰላም ለሁላችን ይሁን!! Peace be forever!!

3. እግዚአብሔር ኢትዮጲያን እንደሚወዳት በእውነት አይቻለሁ፡፡ ምክንያቱም ይሄን ከመሰለ ጨካኝና አረመኔአዊ አገዛዝ ነፃ ማውጣቱ “ እግዚአብሔር እጆቿን ወደ እግዚአብሔር
ትዘረጋለች” ሰላም ለኢትየጲያ ይሁን አሜን

4. በእውነቱ በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡
ትዕግስቱ ደሳለኝ

5. ይህ ትውልድ ያለፈውን ጭካኔ አይቶ ዘር፤ቀለም፤ ሐይማኖት ሳይል አንድ ኢትዮጲያ ብሎ እንዲኖር በድርጅት ማመን ሳይሆን ፈራኽ እግዚአብሔር እንዲኖር ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር፡፡
ዘውዱ እና አማረ

6. ደርግ እንደዚህ ነበር፡፡ ከነበረ ዳግም በሰው ነፍስ ይጠየቅ፡፡

7. እግዚአብሔር አምላክ መጭውን ጊዜያት የሰላም ጦርነት የማናይበትና በሰላም የምንኖርበት ለኢትዮጲያ ሕዝብ ሁሉ ያድርግልን፡፡ አሜን፡፡
ሒሩት እና ታናሼ

8. በጣም የሚያሳዝን ዘመን አለፈ የሞቱትን እግዚአብሔር ነፍሳቸውን የቀበልልን፡፡

9. እኔና ባለቤቴ አይተነው በጣም ነው ያዘንነው ግን ለሚመጣው ትውልድ ትልቅ ትምህርት ነው፡፡ በዘህ ጊዜ በእግዚአብሔር አምነን መኖር አለብን፡፡ ድንግል ነፍሳቸውን
ታስምርላቸው፡፡ አሜን፡፡

11/9/2002

1. ታሪኩን ላየው በጣም ያሳዝናል ከእንግዲህ እኛ ተማሪዎች ለመዋጋት ሳይሆን አገራችን ከድህነት ለማውጣት በርትተን እንማራለን እንለውጣታለን፡፡

2. በየሁት ነገር በጣ አዝኛለሁ ከንግዲህ የዘህ አይነት ነገር ለማየት አልፈልግም፡፡

3. “በሰማአም ለካ አልቀዋል” ይህን እናወግዛለን!!! ክብር ለናንተ ይህ የተፈጸም ግፍ አሳኝና አሰቃቂ ስለሆነ ወደፊት እንዳይደገም መግለጽ እወዳለሁ፡፡

4. በጣም አዝኛለሁ ሰው መሆኔን እስክጠላ ድረስ፡፡

5. ይህ የማንክደው ታሪካችን ነው፡፡ በዚህ ድርጊት ማንኛችንም (ድርጊቱን የፈጸሙት ቢሆንም) ልናዝንና ልናፍር ልንሸማቀቅ ይገባል፡፡ መቸም ዳግም የትም ይህንን ድርጊት ሳይሆን ሀሳቡን ልናስበው አይገባም፡፡ ይህ ከሆነ ነው የሰማዕታቱ ክብርና ምስጋና፡፡ ኢትዮጲያ መቼም ታስባችኋለች

6. እንባዬን የሚያፈስ ታሪክ አይቻለሁ በጊዜው ህፃን ስለነበርኩ ምን ማለት መሆኑን መገንዘብ አስችሎኛል፡፡

7. በጥም የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ የድሮ አባቶቻችንና ወንድም እህቶቻችን የተሰውት ለኛ ብለው ነፃነታችንን አገኘን፡፡ ስለዚህ ያለፈው ታሪክ እንዳይደገም እላለሁ፡፡

8. “No Violence”!!!

12/9/2002

1. ይህ ለዘላለም የማይሳ የፋሽስት ስቃይና ጭከና ነው፡፡ ቢሆንም ግን እነሱ ታግለው ያመጡትን ሰላም እኛ በልማት እናከብረዋለን፡፡አገራችን ከማንም ጠላት እንከላከላለን፡፡

2. ፍቅር ያሸንፋል!!
ቴዲ

3. ይህ ትልቅ መማሪያና ማስታወሻ ነው፡፡ በዚህች ሀገር ታሪክ ዛሬም ሆነ ወደፊት መደገም የለበትም፡፡
ተስፋዬ ዘመድኩን

4. እናንተ መብራቶች ለኢትዮጲያ የቀለጣችሁ ሻማዎች ዛሬ የብርሀናችሁን ጨፍጫፊ መታየት ጀምሯል፡፡ መብራታችሁ እስከዓለም ፍጻሜ ያበራል፡: thank you ለመኖርስላበቃችሁኝ
ቶብስታ ግዛው

5. አጎቴ አማሀ ሁሌም በኛ ትኖራለህ!!!

ልጅ ሃሊማ ኢድሪስ

6. We all love you and remember your good deeds to this great nation.
R.I.P, you finally can

7. Their should not be no more peace to Africa!!!
My uncle Yelema Abebe U will always be in our heart!!
Zion Mulugeta

8. ባየሁት በጣም ተደስቻለሁ በዚሁ ቀጥሉበት
አሮንሸት ተፈሪ
ሙሉጌታ ሱልጣን
ይትባረክ
ስዩም ከበደ
ተወልደ ስዩም

9. “የሰው ልጅ ሆይ የሰው ልጅን እንደዚህ ስትገድል ህሊናይ ምን ይሰማው ይሆን!! መቼም ቢሆን እግዚአብሔር ይሄን ታሪክ አያሳየን ኢትዮጲያ ይባረክ፡፡

10. ይህንን በማየቴ የተነሳ ለደርግ የነበረኝን አመለካከት ዘላለሜን እንድጠላውና እንደዚህ አይነት አገዛዝ በአገራችን ደግም እንዳይፈጠር እያልኩኝ ለሟቾቹም እግዚአብሔር
ነፍሳቸውን ይማር፡፡

11. ታሪክ ምንጊዜም አየረሳችሁም፡፡
በፍቃዱ ተረፈ ረታ (Chicago)

12. አውነት ተቀበሮ አይኖርም ምንም ቢሆን ታሪክ ሠርታችኋል፡፡በዚሁ ቀጥሉበት
መላኩ

13/9/2002

1. የናንተ ሞት ለሌላው ነፃነት ነው፡፡

2. መሪዎቻችንን እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው፡፡

3. ባየሁት በጣም ተገርሜአለሁ ይህ ነገር መቼም ቢሆን በኛ ዘመን ሊደገም አይችልም፡፡

4. ንምንታይ ንቃተል! ታሪክ ያብቃ፡፡

5. ትውልድ አለፈ ትውልድ ይተካል ግን ጥሩ ሥራ መሥራት ጥሩ ነው እናመሰግናለን፡፡

16/9/2002

1. እግዚአብሔር ማስተዋልን ለመሪዎቻችን ይስጥ ይህ መደገም የሌለበት አሳፋሪ ታሪክ ነውና!!! ቤተሰባችሁን ላጣችሁ እግዚአብሔር መፅናናት ይሁናችሁ----- በተለይ 4 ልጆቾን ላጡ እናት፡፡

2. ውድ ወንድሜ ገዛኸኝ ወልዱ ነፍስህን ገነት ያስገባልን፡፡ውድ ወንድሜ ደምህ ውጤት አግኝቷል፡፡
ወንድምህ ኤርሚያስ ወልዱ

3. እነዚህን በማጣታችን ያጣነውን ሳስብ አዘንኩ፡፡

4. በደማችሁ ፀዳች ኢትዮጲያ፤ ድል ለኢህአዲግ!!

5. የባሰ አታምጣ!! ነፍሳችሁን ይማር፡፡

6. መቼም ቢሆን አይደገምም!!! ልናየው የማንፈልግ ወጣቶች በሰማዕታት ስም ለአገራችን ለውጥ እና እድገት መትጋት ይኖርብናል፡፡ነፍሳችሁን ይማር፡፡
ቅዱስ ገ/ኪዳን

17/9/2002

1. የሀገራችን መሪዎች ካለፉት ስርአቶች ተምረው ይህ ምን ያህል የታሪክ ጠባሳ እንደሆነብን አይተው ሰላምን ለዘላለም እመኛለሁ፡፡ ለመሪዎቻችንም ጥንካሬ፡፡

2. This is history and history must never repeat itself! Never!!

3. We have lost so many things in the path to freedom and civilized Ethiopia.
Sure we will change this one love!!!

18/9/2002

1. ለከፈላችሁት መስዋትነት ዛሬ ላይ ቆሜ ስመለከተው ውጤቱን በከፊልም ብታደልም ለመጪው ጊዜ መላ የሀገሪቱ ዜጋ ለመምት ደርሳ የነበረችውን አገራቸውን በደማችሁ
ዝርህ ነፍስ የፈጠሪለትን ደም ዘር አፍርቶ ወደ ፍሬ እንዲበቃ አደራ እላለሁ፡፡
መስፍን (ክፋያችሁ)

2. ላለፉት መልካም እረፍት ፣ሀገራችው በታማኝነት መስዋዕት ሊሆኑን ታላቅ የሆነ ክብር ይገባቸዋልለለ ኢትጲያዬ ወደፊት ካለፈው እንማር ሰው እንሁን፡፡

3. ኦ! እጅግ በጣም ሰው መሆኔን ጠላሁ ሌላ ፍጥረት ሆኜ ብሆን ኑሮ! ነፃ ሆኜ መኖር እንደምችል አስብ ነበር፡፡

4. Our mothers, our fathers our sisters, our aunts, our friends, we will love You till the end through hard times & easy times your havefought day & night even though you are not here, in our hearts you are near. We love you!!!
R.I.P
Dedicated to my uncle Amaha Tsege

5. ባየሁት ነገር በጣም አዝኛለሁ ለመግደል ተፈልገው የተረፉ አሁን ያሉበትን ሁኔታ የሚዳስስ ፕሮግራም ቢዘጋጅ፡፡ አሳዛኝ ታሪክ ነው በዚህ ይብቃ!!! እንኳንም በዚያን ዘምን
እድሜዬ አልደረሰ፡፡እረጅም እድሜ ለመለስ!!!

20/9/2002

1. ኢህአዴግ ከደርግ በምን ይለያል!!!

2. ደርግ በኢሀፓ ስም በግፍ የጨፈጨፋቸውን ሰማዕታት ያረፉበትን መረቅን…ደግሞ ኢህአዴግ በሽብርተኝነት መቼ ነው የጨፈጨፋቸውን ነው የምንመርቀው?????

3. By my Generation, I wish to kill poverty, illutracy and…
Samuel

4. ኃ/ስላሴ የፊተኞቹን አወገዙ ደርግ በተራው ኃ/ስላሴን አወገዘ ኢህአዴግ በተራው ደርግን ኮነነ እግዚአብሔር በቃችሁ ይበለን አሜን!!!

22/9/2002

1. ይህንን የግፍ ታሪክ እንዳውቅና ትምህርት እንድንወስድበት ስላደረጋችሁ በወጣቶች ስም አመሰግናለሁ፡፡
ለዘላለም እንዳይደገም

2. እግ/ር ይቅር ባለን ማንነት ይህን ግፍ የሰሩትን ይቅር እንበል!!
God Bless you

3. Its very interesting, I will never forget forever, Thank you!!!

4. በጣም የሚያሳዝን ድርጊት ነው፡፡ መቸም እንዳይደገም!!

5. ወንጀለኞች ለፍርድ መብቃታቸው ያስደስታል!!!

6. መስዋትነት በከፈሉ ጀግኖችና ዜጐቻቸን እኛ እና ሀገራችን ሕያው ሆነናል፡፡በቂ ገለፃ ለሰጡን አስተናጋጅ እናመሰግናለን፡፡

23/9/2002

1. ከእንግዲህ በቃ ይብቃ ላይደገም ቃል እንግባ በጣም ነው የሚያሳዝነው፡፡

2. ኧረ በቃችሁ እርስ በእርስ ተባልታችሁ ሰላማዊ ሰው አይለቅ!! እባካችሁ እባከችሁ በዚህ ይብቃ!!! እልቂ ለልማት አይደለም፡፡

3. በጣም ያሳዝናል ይሄ ሁሉ ንፁህ ዜጋ አለቀ እግዚአብሔር በሰማይ ቤት በገነት ያኑራቸው፡፡

4. ባየሁት ነገር በጣም አዝኛለሁ ነገር ግን ያሁኑ ትውልዶች እድለኞች ነን ስለዚህ ካለፈው ስህተት በመማር ለሰላም እና ልለማት መታገል አለብን፡፡
አትክልት

25/9/2002

1. ለርሱ ሲል ተሟግቶ የሞተ የታደለ ነው፡፡ ስሙ ለዘላለም ሲወሳ የሚኖር ነው፡፡
ፍቅር ማህተቤ

2. ሰልሀምዱሊላህ ይህን ማየት በራሱ ትልቅ እድል ነው፡፡
አብደላ ሁሴን

3. ያለፈው ሁሉ አልፏል የፈሰሰ ደም ፈሷል ካሁን በኋላ ግን የፈሰሰውን ደም በልማት እያደስን ለዘላለም ሰማዕታችን እንዘክራለን!!
Jimmy

4. ከፍተኛ ሐዘን ለወገኖቼ ተሰምቶኛል፡፡ ዳግም እንደዚህ ዓይነት የዘር የማጥፋት ወንጀል እንዳይፈጸም ባገኘሁነት አጋጣሚ አስተምራለሁ፡፡
Demisse

5. “ሰው ያልፋል ታሪከ ግን ከተጠበቀ ለዘላለም ይኖራል”፡፡
Mintesinot Degefu

6. እነሆ ጥቁር ጠባሳ ራሱን እንዳይደግም ለሰማዕታቱ ክብር ለዘላለም፡፡
Abrham

7. በጣም ያሳዝናል እግዚአብሔር ምህረት ነው ያደረገልን፡፡
ዳዊት ንጉሤ

8. በእርግጥ ይህ ነገር በሀገራችን ተፈፅሟል? ከዚህ በኋላ ለሚፈጸመው ክብር የሰው ደም ተጠያቂ ላለመሆን እውነትንና ነፃነትን ይዘን ልንጓዝ ይገባናል!!!
ዘካሪያስ ሀ/ሚካሌል

9. ወንድሜ አምሣሉ ማሞ ምንግዜም አልረሳህም፡፡
አጥናፉ ማሞ

26/9/2002

1. ደ = ደብድበህ
ር = ርግጥ አርገህ
ግ = ግዛቸው
ደደብ ነው አይደል?
አላዛር መኰንን

2. በእርግጠኝነት በደርግ ዘመን ለክብር የሰው ልጅ ነፍስ ይልቅ ጥፋት የከበረ እንደነበር ተገነዘብኩ፡፡ ግን ታጋዮ ሞተ እንጂ አላማው አልሞተም፡፡
እዮብ ካሣሁን

3. በእናንተ መስዋዕት እኛ ኖረናል ታላቅ ክብርና ምሰጋና፡፡
( HUP)

4. በርግጠኝነት ሀገሬ ብዙ ችግር አሣልፋለች ካሁን ወዲህ ግን አትቸገርም!!
አላዛር መኰንን

5. ያሳዝናል!! ሰሚቀጥለውም ትውልድ ጥሩ ትምህርት ይሠጣል፡፡ Never Repeat!!

6. ካየሁትና ከሰማሁት ተጋነነ!

7. ኬር ይሁን አገሩ!

8. ከመ/አ ደረጀ ተመስጌን እሸቴ /ታጋይ/ ለአለፉትም ለአሉትም የአትዮጵያ ሕዝብ፤ እንደሆነ ለችግርና ለስቃይ ኑሮ አለለት፤ ለሞት ከሆነ ደግሞ እያንዳንዱ የራሱ ቀን አለው ስለዚህ ባለማወቅ የምትፈጽሙት ሁሉ ነገር የማይቀር ቢሆንም ያለሠዓቱና ያለአግባብ መሆኑ ኢትዮጲያ ሀረጌን እንድጠላት አርጎኛል፡፡

9. Never Again! History must be changed forever! ከማሽቃበጥ መተግበር

10. We must look forward! ለሞቱት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፤ አባቶቻችን ፤ እናቶቻችን ነብስ ይማር!! እባካችሁ ከእንግዲህ ይብቃን! ይህን አሰቃቂ ነገር ተመልክተናልናየተዳፈነ እሳት ይጥፋ፡፡

28/9/2002

1. ለወንድሜ ለከበረ ሀይሌ አባዲ የግፍ ዘመን ሰቆቃ ዘመን እ/ር አሳልፎልናል፡፡ አሁንም እ/ር ነፍስህን ይማረው፡፡ በገነት ያኑረው አንተ ጥሩ አስተማሪ ጥሩ ወንድም ነበርክ አሁንምደግሜ ደጋግሜ ነፍስህን በገነት ያኑረው፡፡
እህትህ ቲቲ ሀይሌ

2. ለአጎቴ ለኤፍሬም ፋንታዬ እ/ር ነፍስህን በገነት ያኑረው!!

3. እ/ር ሆይ ስለምታስባቸው ከእነሱ ጋር ስለሆንክ አመሰግንሀለሁ፡፡
ዮርዳኖስ ገ/ማርያም

4. ወንድሜ ግርማ ሲማ እናታችን በአንተ ሀዘን እንደደቀቀች መቃብር ወረደች እ/ር ነፍስህን ይማር!!
ወሰኔ ሲማ

5. ካጠገቤ ተነስተህ ለተሰዋኸው ለአጎቴ ሳሙኤል ህለተወርቅ፤ በቀል የእ/ር መሆኑን አወቅሁ፡፡ ልዑል እ/ር በገነት ያኑርህ፡፡
ሽመልስ ወንድሙ ሕለተወርቅ

6. የናንተ ሰማዕታትነት ለእኛ ዘላለማዊ ህይወት እረድቶኛልና አመሰግናለሁ!!

28/9/2002

1. ይህን ታሪክ የዛሬው ትውልድ አይቶ አኑን ያለውን የሰላም ጊዜ እንዲያመሰግን ይገባዋል፡፡
ሳሙኤል ታደሰ

2. መቼም ዘላለማዊ ናችሁ፡፡ ለእናንተ እኛ ዛሬ ሰላም ነን!! እናመሰግናለን፡፡
ሞገስ

3. ቃል የለኝም!! አመሰግናለሁ፡፡
ብርሀነመስቀል

4. ይህ ታሪክ እንዳይደገም በጣም ሀሳብ አለኝ ፡፡ ነገር ግን ሁሉም መንግሥትና አስተዳደር የየራሱ ድርጊት አለው ስለዚህ እባካችሁ ይህ ያፈና ጊዜ መብቃት አለበት አሁንም
ይኖራል ብለን እናምናለን፡፡

5. ለሰማዕታት ለወንድሜ ባይራይ አሰፋ አልሞትክም ታሪክህ ዘወትር ይዘከራል እኛ ወጣቶች እንደዚህ ዓይነት አምባገነንነት ስርዓት እንዳይኖር ለዘለዓለም እንታገለዋለን፡፡
ኪዳኔ

1/10/2002

1. በጆሮዩ የሰማሁት ዛሬ በአይኔ አይቼ በውስጤ ከአይኔ ትልቅ እንባ አፈሰስኩ፡፡
ከበደ (ከወላይታ)

2. እግዚአብሔር ይመስገን ዛሬ ሁሉም አልፏል፡፡
ዮሴፍ

3. አየነው ሰማነው በጣምም አዘንን በኛ ይብቃ!!!!

4. ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን፡፡
ፀጋዬ

5. ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር የመቻቻል ትርጉም ዛሬም አልገባንም፡፡
ዘሪሁን

6. ሳያዩ የሚያምኑት ብፁአን ናቸው፡፡
ብሩክ

7. ቆም ለሚያየው ላል ይመስላል፡፡ማየት ማመን ነው፡፡

8. ለዚህ አላፊ አለም ይህን ትልቅ ታሪክ ማስተላለፍ ታላቅ ፅናት ነው!!!
ማህደር

9. እግዚአብሔር እንዲህ ዓይነት አሰቃቂ ድርጊት ለፈጸሙት እንዲፋረዳቸው እንጸልያለን፡፡never happen again!! ለሰራው ስራ እግዚአብሔር የእጁን ይስጠው፡፡ ዳግም
እንዳይመጣ ሁሉም ነገር ያሳዝናል!!

4/10/2002

1. በአባታችንና በወንድማችን የመጣ ሰላምና ዲሞክራሲ ለዘላለም ይኑር/ምን ግዜም/

2. ያለፈው አልፏል ምነግዜም ተመልሶ አይመጣም እግዚአብሔር እውን ታደረገው ዘንድ እንጸልያለን፡፡
M.zewdie

3. ለጊዜውና ለነበረው ሥርዓት እድጉን አትብቀን እንቃወማለን በርካታ የሕዝብ ልጆች መስዋት ሆነዋል፡፡ ግን አሁንም በኢትዮጲያ ውስጥ ጥቂት ነገር አለና ይታሰብበት፡፡
Esayas (Canada)

4. I learned from this picture Derg was not Human Bieng!!

5. ሁለተኛ በእትዮጲያ አይደገምም መቸም!!
ኪሮስ ገ/መድህን

6. NEVER, EVER AGAIN IN ETHIOPIA.
Dalayana Kiros

7. እትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!
China mlekamy

8. መቸም እንዳይደገም!! አንፈልግም
መሀመድ ሬድዋን

9. ያለፈው ሁለተኛ አይደገምም ከእግዚአብሔር ጋር!!
ፍሬሕይወት ማዘንጊያ

10. ኢትዮጲያ ሕዝብ ለቀጣዩ ትውልድ እንዳይደገም መጸለይ አለበት
ተሰማ

11. እግዚአብሔር አምላክ ዳግም እንደዚህ አይነት ነገር አያሳየን አሜን!!!

12. ይህ ለመጪው ትውልድ ትምህርት ሰጭና አስተማሪ ስለሆነ በጣም ጥሩ ነው፡፡
ዳዊት

13. በደርግ ጊዜ የነበረው የመንግስት ስርዓት ከአሁኑ ጋር ሲነፃፀር የሰማይና የምድር ልዩነት አለው፡፡

13. ለስልጣን ተብሎ ሰውን የሚያጠፋ መንግስት በኢትዮጲያ እንዳይፈጠር አምላክን እንለምን፡፡

14. አምላክ እንዲህ ያለውን ነገር በዘመናችን መቼም አይደግመውም፡፡
አስማረ ፍቃዱ ( ከሙሉ ወንጌል ቤ/ክ)

15. በሰማዕታት ስም የተሰማኝን ሐዘን ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡
ታሪኩ ሙሴ ( ከአ.አ. ዩኒቨርስቲ)

6/10/2002

1. ለዛሬ እኔነት ላበቃችሁኝ ውድ ኢትዮጲያውያን በሙሉ አላህ ውለታችሁ ይክፈላችሁ

2. እናንተ ናችሁ ሰዚህ ያደረሳችሁንና ዘላለማዊ ክብር ለሰማዕታት ይሁን!!!
ስንታየሁ

3. ይህ ሁሉ ሰእኔ ሚስጥር ነበር እግዚአብሔር ይህንን አስጨናቂ ጊዜ በቃ ስላለ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ እናንተን አርበኞች እግዚአብሔር ይባርካችሁ፡፡
አስራት

4. ከታገሱት ሁሉም ያልፋል በአሁን ዘመን የሚኖር እያንዳንዱ ዜጋ ለሰላም ዋጋ መክፈል አለበት ስልጣን ላይ ካለው መንግሥት ጭምር!!! ሁሌም አስባችኋለሁ!!

5. በጣም ያሳዝናል ያየሁት!!

7/10/2002

1. የሠራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ነብሳችሁን በገነት ያውለው!! ከልብ በሆነ ስሜት!!
ኢትዮጲያዊ

2. መጪው ጊዜ ከእናንተ ድል ጋር ብሩህ ነው እግዚብሔር ኢትዮጲያን ይባርክ!! አባታችን አልሞትክም ሀ/ስላሴ፡፡
መታሰቢያ

3. የሞቱትን ነብሳቸውን ይማርልን ለኛ ላለነውም አስተዋይ ልቦና ይስጠን፡፡
ሀይሌ

4. ይህ እልቂት እንዳይደገም የበኩሌን ቃል አገባለሁ!!! እግዚአብሔር እትዮጲያን ይጠብቃት፡፡
ሚኪያስ ተክሌ

5. ይህን የመኖር ዕድል ያገኘነው በናንተ ደም ነው!! መድሀኒዓለም ነፍሳችሁን በገነት ያኑር ላችሁ፡፡
ሚስጥረ

6. በደማችሁ እኔነቴን በምድር ላኖራችሁ ነፃነቴን ላወጃችሁ ሁሉ ፈጣሪ ነብሳችሁን በገነት ያኑረው!!
በሕይወት ካለው ውንድማችሁ አህመድ አ/ቃድር (ከአፋር)

7. ይህን ያየ ቀጣይ በኢትዮጲያ ውስጥ ይፈጸማል ብሎ ማሰብ የለበትም ምክንያቱም ይህ ኤግዚብሽን እስተምሮናልና ለአዘጋጅዎችም ምስጋና አቀርባለሁ፡፡

8. ይህንን አሰቃቂ በደል ሀገር በሚረከብ ወጣት ላይ ያደረሱ ሰዎችን ሰላህ ይፋረዳቸዋል፡፡
ሳሊህ

9. እግዚአብሔር ያንን ክፉ ዘመን እንደገና አያምጣው፡፡
አብነት (ደብረዘይት)

11/10/2002

1. አጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው!! እንዲህ አይነቱ ድርጊት በኢትዮጲያ ምድር አይደገም፡፡

2. በምንም አይነት መንገድ እናምልክ በኢትየጶያ አገራችን እንዲህ አይነት ጭካኔ እና አረመኔነት አይደገም፡፡ እጅግ ዘግናኝ ድርጊት ነው፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ይስጠን
አሜን!!! ለሰማዕታት ቤተሰብ መፅናናት ይስጥ፡፡

3. የሞቱትን ይማር ሁለተኛ በኢትዮጲያ ችድር እንደዚህ አይነት ስቃይ ምንጊዜም የአከተመ ሆኖ ይቅር አሜን!!!

4. A time of great cruelty Never again, Please.

5. እኛ በደህና ጊዜ ተወልደናል፡፡

6. ያለፈው ዘመን ለኛ ለአሁኖቹ ትምህርት ነው፡፡ ምህረትና ሰላም ለኢትዮጰያ

12/10/2002

1. ይህ ታሪክ ያለፈው ትውልድ የፈፀመው መጥፎ ድርጊት ነው፡፡ የዛሬው ትውልድ ደግሞ ከመሰል መጥፎ ድርጊት ተቆጥቦ ለሀገሪቱ አልሚ ተግባር እንዲፈፅም አደራ እላለሁ፡፡
ፍቅረስላሴ አድማሴ

2. ይህ የሰማእታት መታሰቢያ ቂም በቀል ጥላቻ ለአገር ምንም ፋይዳ እንደማይሰጥ፡፡ አሁንም ያሉት መሪዎች ከዚህ ቂም፤በቀል፤ተንኮል ዘረኝነት እንዲወጡ ትልቅ አስተማሪ
ነው፡፡
አማኑኤል

3. በራስህ እንዲደረግ የማትፈልገውን በሌሎች ላይ አታድርግ!!!
ራሄል ሀጐስ

4. ይህ የሰማዕታት መታሰቢያ ቂም በቀል ጥላቻ ባገራችን መቼም እንዳይደገም እኛ ታዳጊዎች ሀላፊነት አለብን፡፡
እስጢፋኖስ እንየው
ሔኖክ ሰለሞን

14/10/2002

1. በደማችሁ ጸዳች ኢትዮጲያ!!!
ዮሐንስ

2. Long Live Ethiopia!! ሕያው ናችሁ!!!

3. በጣም ያሳዝናል ይህ መሆኑን አላውቅም ነበር!!! የኢትዮጲያ ጀግኖች አንበሶች!!

4. ከዚህ አሳዛኝ ታሪክ ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን፡፡ ልዩነታችን በሰላም እንፍታ እንግለጽ!!!

5. ለሰማዕታት እግዚአብሔር ገነትን ያውርሳችሁ አሜን!!!

6. እጅግ በጣም ያሚያሳዝን ነበር በየትኛውም አለም ተደርጐ የማይታወቅ አሰቃቂ ድርጊት ነበር፡፡

7. ግዜ ደጉ!! ትናንት በከፈላችሁ መስዋትነት ዛሬ ላለነው ወጣቶች ትልቅ የአላማ ፅናት ተምረናል፡፡

8. ይህንን በየመስሪያ ቤቱ እና በየትምህርት ቤቱ እየሄዳችሁ ብትጋብዟቸው በጣም በቂ እውቀት ያገኛሉ ይህንን ያላዩ ብዙ አሉና፡፡

9. God Bless you Jerry!!

16/10/2002

1. ከዚህ በኋላ በምንም አይነት መልኩ የዜጐች መብት መጣስ የለበትም!!

ደረጀ

2. አሁን ግን የነፃነት፤ የእኩልነት ዘመን ነው!!!

ተሾመ

3. ለኛ ኢትዮጲያ ትልቅ ማስታወሻ ነው፡፡

በሱፈቃድ ጌታነህ

4. በጣም አዝኛለሁ ሁለተኛ እንዳይከሰት ፈራሁ፡፡
ብሩክ

5. ኢትየጶያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች፡፡
B.I (A.A.U.)

6. አምላክ የሞቱትን በገነት ያኑርልን መቼም የትም አንዲህ ዓይነት ግፍ አይፈጸም!!!
ሜሮን

7. ያለ ሀጥያታቸው የተጨፈጨፉትን ንፁህ ሕዝቦች አግዚአብሔር ያስባቸው የሞቱትን ነፍስ ይማርልን በገነት ያኑራቸው!!
ቲዮቢስታ ሳህሌ

8. ያላየሁትን አይቻለሁ ዳግመኛ አይደገምም!!! እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን እግዚአብሔር ሀገራችንን ይጠብቃት ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!!
ሰላም

9. This is a reminder of an almost lost generation, we shall never forget!!!
Ayda

17/10/2002

1. የሰማዕታት “ደም” አሁን እየበለጸገች ለምትገኘው ኢትዮጲያ ጉልህ የሆነ ድርሻ አለው!!
አሸብር

2. እንደገና ባይፈጠር እላለሁ፡፡
ሚኪ

3. ለአላማቸው የታገሉ ሁሉ ባይኖሩም ስራቸው ይኖራል!!!
ወንድወሰን

18/10/2002

1. በእነሱ ሞት እኛ ኖረናል፡፡ ሁሌም ክብር ይገባቸዋል!!!!
ማማ ሩሀማ

2. የንፁሃን ደም ከንቱ አልቀረም ያለፉት ናቸው ፡፡ በሕይወት ያለን ከዚህ መጥፎ ነገር መማር አለብን የሰላም አገር እንድትሆን ሁላችንም መጣር አለብን፡፡
ሲሳይ

3. እርስ በእርስ ተባልታችሁ ሰላማዊ ሰው አይለቅ መቼም እንዳይደገም!!!!

19/10/2002

1. ያን መጥሮ ጊዜ አሁን አየሁት፡፡
አትክልት ለማ

2. መደገም የሌለበት ታሪክ ነው ተመልክቻሰሁ!!
ዳንኤል

3. በሕይወቴ በጣም ያዘንኩበት ቀን ይህንን አሰቃቂ ድርጊት በማየቴ ነው፡፡ ከጥፋት ምን ግዜም ኪሳራ እንጅ ትርፍ አይገኝም፡፡
ፀሐይ

4. ያለፉት ጊዜያቶች ይበቁናል ነገን የተሻለ እናድርግ::

5. የኋላውን እየረሳን ወደፊት እንራመድ፡፡

6. ይህንን ነገር ሳይ አሁን ያለሁበትን መንግሥት አመሰገንኩ በጣም ያሳዝናል፡፡
ኤልሳ

7. የትላንትናው ገድል ለዛሬ ክብራችን መሠረት ነው፡፡

8. በጣም ያሳዝናል የሰው ልጅ እንደማይረባ ነገር የተወገረበት ስለሆነ ነገር ግን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ እንደዚህ ዓይነት ነገር ስለማይደገም በምድራችን፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይባርክ፡፡
ህሊና ግርማ

9. ባየሁት ነገር አዝኛለሁ፤ ተደስቻለሁ በቀጣዩ ትውልድ ይህ አይደገምም፡፡
ኪሩቤል ወልዴ

21/10/2002

1. በናንተው መስዋአት ይን ሁሉ ነፃነት ሰላም ዲሞክራሲ አግኝተናል፡፡ አደራችሁን እንቀጥልበታለን፡፡

2. ክብርና ሞገስ ለናንተ ይሁን፡፡

3. አሁን ህያው ሆናችኋል፤ አልሞታችሁም በአይኔ አይቻለሁ፡፡
ዳንኤል ጌታቸው

4. እንደዚህ አይነት ነገር ለዘላለም መደገም የለበትም፡፡

5. አምባገነን ስርዓት ስትፋለሙ የነበራችሁ ውድ ዜጐች በእናንተ መስዋትነት ዛሬ ሰላም ልማት ዲምክራሲ አግኝተናል ክብርና ሞገስ ለእናንተ፡፡
ተኪኤ ( መቀሌ)

6. You are the cause what we are here, never again!!

22/10/2002

1. ሁሉም ያልፋል ታሪክ ግን ለዘላለሙ ተፅፎ ይኖራል፡፡ ክብርና ሞገስ ለቀይ ሽብር ሰማዕታት ይሁን፡፡

2. ጌታን ይቅር እንዳለን እነሱን ይቅር ይበላቸው ሰማዕታት ለትምህርታችን ነው ያለፉትና አይደገም ይብቃን፡፡
እዮብ

3. አድራጊዎችን ይቅር ብለናቸው ለወደፊቱ እንዳይደገም ብናገር መልካም ነው፡፡ ሀገሬ ኢት ዮጲያን እና አጽሙን በሙሉ እግዚአብሔር ይባርክ፤ መልካም ግን ልቦናን ይሰጠን፡፡ ግን
ይቅርታን እየተማርን እናስተምር፡፡

4. ይህ ያለፈው መጥፎ ታሪካችን ነው፡፡ እንዳይደገም ምኞቴ ነው፡፡

5. ያለፈውን እንርሳ ግን ያለፈውን ይቅር እንባባል፡፡
ተስፉ ረፌ