Content on this page requires a newer version of Adobe Flash Player.

Get Adobe Flash player

23/10/2002

1. ለካስ ኢትዮጲያ እንደዚም አይነት ጀግና ወልዳለች ቆራጥ፡፡
ኤደን

2. Rest in peace, you have contributed mightily to your country, May God Bless Your Soul. ሁሌም እናስታውሳችኋለን፡፡
ፌቨን፣ ሰላምእናለምለም

3. It is a very rhyme, but it will never be repeated again

27/10/2002

1. አባቴ በደርግ ተሰዶ ውትድርና ባይሄድና ትምህርቱን ቢጨርስ ህይወታችን ይቀየር ነበር፡፡
ይበልጣል ጥላሁን
ሄኖክ ባያብል ( ከጐጃም)

2. አረጋዊ ታረቀኝ
ጌቱ ሀጐስ
አሰፋ ይመኑ አድል ቀድር ሀምዛ ነፍሳችሁን ይማረው፡፡
ሁሴን መሀመድ ሀሰን

3. አያዛዝኑም??ለኛ ብለው!!!

4. የወንድሜ መኖር እኔ እንድኖር አድርጐኛል፡፡
አይን

5. በእናንተ መራር ትግል ዛሬ እና በነፃነት እንድንኖር አድርጐናል፡፡ ዘላለም ክብር
ለሰማዕታት!!!
M2

6. የሰማዕታት ሕይወት “ህያው “ነው፡፡ ነፍሳችሁን በገነት ያኑርልን፡፡
M.N (2002)

7. የግዛው ቤተሰቦች ተርፈዋል፡፡
ሳባ አለማየሁ

8. በእውነት መቼም አይደገም! ነፍሳችሁን ይማረው!!

29/10/2002

1. ንግስት ተፈራ (እምወድሽ) ክበር ላንች ይሁን!!!

2. ውድ ወንድሜ ገዛኸኝ ወልዴ ዘወትር ሁሌ አስታውስሀለሁ፡፡

3. እንደሻማ ቀልጠው ለዚህ ላበቁን ሰማዕታት እህት ወንድሞቻችን ነፍሳችሁን በገነት ያኑረው አሜን፡፡

4. ለሰማዕታት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እግዚአብሔር በመንግስቱ እንዲጠብቃቸው እንጸልያለን፤ ለሰሩትም ስታ እጅጉን እናከብራቸዋለን፡፡

5. የሰው ልጅ በወንድሙ ላይ እንዴት ይጨክናል???

6. ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ስራ ሰርታችኋል፡፡

7. ትውልዱን የሚወድና ቅን አስተሳሰብ ያለው መንግስት ይስጠን አሜን፡
God Bless Ethiopia

30/10/2002

1. ለዘላለሙ ኢትዮጲያን ቂም በቀል ጥሩ አይደለም፡፡
ደማሙ ብርሀኑ

2. ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በከፈሉት መስዋት መቼም አንረሳቸውም፤ በደምና
በአጥንታቸው ለውጥ አምጥተዋልእና!!!
በአውቀቱ

3. ሰማዕታት በደማቸው ወለዱን እኛ በትግላችን የኢትዮጲያ ህዳሴ እውን እናደርጋለን፡፡
ጉራሾ ለሚታ

4. በጣም የሚገርም ነው በዓለም ታይቶ የማይታወቅ ጭፍጨፋ የታየበት ነውና በምንም
ተአምር ሊደገም የማይችል ነው፡፡

5. ለወንድሜ ደረጀ ፍስሀ ምንም በማታውቀው ነገር ከአሜሪካ ቤተሰብህን ለመርዳት መጥተህ ለተሰዋኸው ደምህ እንደ አቤል ደም ይጮሀል ሁሉንም ሰማዕታት ታሪክ አይረሳቸውም፡፡

6. በደርግ የነበረ አገዛዝ በጣም ያሳዝናል! የሞቱት ወንድሞቻችን መንግሥተ ሰማያት
ያውርሳቸው፡፡
ወ/ኤል

7. አንድ አጐቴን ያጣሁት በዚህ የጭካኔ አገዛዝ ነው፡፡

8. ከጥሩ ነገር በፊት መጥፎ ማየትን ለትምህርት ነው፡፡

9. ክብር ለሰማዕታት ጨካኞችን ከገቡበት ታድነው ለፍርድ ይቅረቡ፡፡
ሳሚ

10. ምንም ምንም ሰብአዊነት ያልታየበት ንፁሕ ጭካኔ!! 2/11/2002 እንኳን ከአውሬው መንግሥት እግዚአብሔር ገላገለን!! Never again!!! 2. seems like we people won’t learn form the history...first Jewish people, the Derg powering in Ethiopia, the USA-KKK just imagine what will be the next... We will never let it happen again. May the deceased souls rest in peace.
መደገም የሌለበት ነገር!! We will never permit to happen again!! Never!!

4/11/2002

1. እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በገነት ያኑርልን፡፡

2. እንዳይደገም!!
ይዲዲያ ከበደ

3. ተክሉ ወንድሜ ብትሞትም ምንግዜም አስታውስሀለሁ፡፡
ወንድምህ መኳንንት

4. ይኸው ሁሉም አለፈ ወንድሜ ዳንኤል አሰፋ ነፍስህን በገነት ያኑረው፡፡
ወንድምህ ዳምሶን አሰፋ

5. በጣም ተሰምቶኛል በዚህ ይብቃን፡፡
ሲሳይ

6. የሰላምን ትርጉም ልናውቅ የምንቅለው በዛን ጌዜ ስንኖር ብቻ ነው፡፡
ሄኖክ ፀጋዬ

7. በእነርሱ ደም እኛ ድነናል እግዚአብሔር ይባርክ፡፡
ቢኒያም ዘላለም

8. I am glad that this museum have so many Ethiopian, will not forget the past!!!

9. Where does this great evil come from? For the sake us all pray, we learn the mistakes of the past. Congratulations on a truly moving memorial...
Sam

5/11/2002

1. ያለፈ አልፏል አሁን እንዳይደገም እግዚአብሔር ይርዳን ነው፡፡
ትህትና ግርማ

2. ይሄን እድል በማግኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል ግን ከእኔ ምን ይጠበቃል?

3. በዛን ግዜ ባለመኖሬ አምላኬን አመሰግናለሁ ለዛ መንግሥት አምላክ ምህረት ያድርግበት፡፡
ሜሮን

4. እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይባርክ ፊቷን ወደ እግዚአብሔር ትመልስ፡፡
ሸዋለም

5. ሰላም ውዷ!! ሰው በሰው ላይ ይህን ያህል ይጨክናል? ዩሳቤ አውሬ ዘመን፡፡ ለዘመነኛው ሰው ሁሉ ቆም ብሎ የራሱን አስተሳሰብ የሚሰልልበት ብሎም የሚመዘንበት ቦታ ይሁን!!ከታሪክ ይማሩዋል እንጂ አይደግሙትም፡፡
ነብዩ

6. በዚህ ይብቃ!!
እዮብ

7. ለሰው ልጆች በሙሉ ሁሉን የሰጠ እግዚብሔር ነውና ባለን እንደሰት ዳግም ወደ ጥፋት አንሂድ፡፡
አ/ሀኪም

6/11/2002

1. በእውነት ደርግ እኛን ያደረገን ነገር መቼም አይረሳም፡፡
አብርሀም ግርማ

2. ደርግ እጅግ ጠባብና ጭፍን አስተሳሰብ እንዳለው ተረድቻለሁ፡፡

3. እግዚአብሔር ከመዓት ይጠብቀን ይሰውረን!!!

4. ይህ ዓይነት ነገር እንዳይደገም የዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡
ናትናኤል ፍስሐ

5. ልብ እንበል!! የምናየው የሆሊውድ ድራማ አለመሆኑን ለወጣቱ ማስገንዘብ እፈልጋለሁ፡፡ የማይጠፋ እሳት ማቀጣጠል ለራስም ሆን ለወገን አስጊ ነው፡፡ በመሆኑም ለሚቀጥለው
ትውልድ ጥሩ ነገር እናስተምር እናስቀምጥ አደራ፡፡ ለሞቱትም ቤተሰብ መፅናናትን
እመኛለሁ!!
H.S

7/11/2002

1. ይህ ትውልድ ከዚህ ብዙ ነገር መማር አለበት፡፡ እነዚህ ሰማዕታት ያደረጉትን ተጋድሎ መጠበቅ ይገባል፡፡
ተስፋዬ

2. May always God Bless Ethiopia!!

3. R.I P. our martyrs! We can’t be here without your death. Thanks a lot.
Selam

4. ያለፈው አሰቃቂ ዘግናኝ ግዜ ነበር፡፡ አሁን ግን ከዚህ በመማር አገራችን ለእድገት እንጂ ጦርነት አንመኛት ግን እናንተስ ምን እየሰራችሁ ነው?

5. እውነት መቸም ተቀብራ አትቀርም!!!
MZKR.A

6. RIP ለገሠ በዙ እግዚአብሔር እንደሚጠብቅህ ተስፋ አደርጋለሁ!! የልጅ ልጅህ
ፌቨን ፀሐዬ

10/11/2002

1. በደል በበደል ሲጨመር የኢትዮጲያ ፈተና መቼ የሆን የሚቆመው!!!

2. ልብን ሰርስሮ የሚገባ ሀዘን አሰቃቂ ድርጊት ምንኛ የሰውን ህይወት እንደሚጎዳ ዛሬተ ረድቻለሁ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ያስባችሁ ዘንድ ዘወትር አጸልያለሁ፡፡
ሰላማዊት ሞሲሳ

3. እንደዚህ ዓይነት አሰቃቂ በደል እንዳይደገም ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማድረር አለብን፡፡
ቤዛ

4. መጪው ትውልድ ከዚህ አሳዛኝ ታሪክ ተምሮ ዳግም ማንም ኢትዮጲያዊ በግፍ እንዳይገደል መወሰንና ለልማት ተግቶ መስራት አለበት፡፡
ታምራት

5. እነዚህ ሰማዕታት ለነፃነት ሲሉ ሞተው የዛሬዋን ቀን አስገኝተዋል፡፡ ስለዚህ ሁሌም ከልባችን አይጠፋም፡፡
ወንድወሰን አረጋ

6. እንዲህም ነበር እንዴ? ያሁሉ ጉድ አልፎ አሁን ንፁህ አየር እንድንተነፍስ ላደረጉን ሰማዕታት ክብር ይግባቸው፡፡
ክብር ለአሞራው!!

7. ግሩም የልዩነት መስታወት!!!

11/11/2002
1. ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፍ የሚገባውና በጣም ጥሩ ነው ስለዚህ ያልተገኙ መረጃዎችን በማሰባሰብ የበለጠ ቢሠራ ጥቱ መሆኑን እገልጻለሁ፡፡

2. የሰው ልጅ በጣም ጨካኝ መሆኑን ያየሁበት ቦታ አቤቱ አምላኬ ይህንን በኢትዮጲያ አይደገም አሜን!! ኢትየጲያን እግዚአብሔር ይርዳት!!!
ሲሳይ

3. በጣም አሳዛኝ ድርጊት ነው በዚህ ይብቃ!!

4. የሰው ልጅ በሰው ሲጨክን በጣም ይሳዝናል!!!

5. እንዲህ አይነት አሳዛኝ ድርጊት መቼም እንዳይደገም እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይባርክ!!
ቅድስት

13/11/2002

1. የሚገርም የታሪክ አሻራ ነው!! ሞት ይብቃ!!!

2. አየሁት ሁሉንም ዛሬ ግን በፍጹም አይደገምም!!!

3. “ሁሉም ነገር ለበጐ ነው”

4. Its Amazing!!!

14/11/2002

1. አምላክ የሙታንን ነብስ በገነት ያኑራት አባቴም ነብስህን በገነት ያኑራት አባቴ ታደሰ ህንድያ፡፡
ከልጁ ነብዩ ታደሰ

2. በህወታቸው የሀገራችንን ነፃነት ያስገኙ ወንድሞቻችንን እህቶቻችን፤ ጓዶቻችን፤ ሥራ ከመቃብር በላይ ነው፡፡ እብዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር!!
ኃይሉ ሐጐስ

3. ከዚህ ሁሉ ስቃይና መከራ በኋላ አላህ ለዚህ አሁን ላለንበት ስላደረሰን ከፍ ያል ምስጋና ይግባው አልሃምዱሊላህ፡፡ የተጀመረውን ሰላምና ዲሞክራሲ በእኩልነት አለምን ልኖርና ገለግል ቃል እገባለሁ!!!
አህመድ ትጃን አህበቲ ( ከአጋሮ)

16/11/2002

1. ይህ ሁሉ አልፎ የቀን ጸሐይ ወጥቶልናል፡፡ ይህችን ጸሐይ አጥብቀን እንጥቀማት እንጠብቃት!!!

2. አሁንም ደርግን የሚናፍቁ ሰዎች ይኖራሉ እነዚህን በንቃት መከታተል ያስፈልጋል፡፡
ብርሀኑ ጥላሁን ተ/ማርያም ሁሌም እናስባችኋል፡፡መሠረት በላይነህ

3. በነሱ የደረሰ በኛ አይድረስ፡፡ መንግሥተ ሰማያት ያዋርሳችሁ፡፡
አስቴር

4. እግዚአብሔር ለዘላለሙ ኢትዮጲያን በመሀል እጁ አድርጐ ይጠብቃት፡፡

17/11/2002

1. እግዚአብሔር ኢትዮጲያ ከንደዚህ አይነት አደጋ ይጠብቃት!!
ናትናኤል ( ከአዳማ)

2. ይህ ለመጪው ትውልድ ትልቅ ትምህርት ነው፡፡

3. የልባቸው ፍላጐት ልቤን ተፈታተነው!!!
አለምሰገድ

4. ለዛሬዋ ነፃነት የታገሉትን መቼም አንረሳም!! ለጉብኝቴ የምለው አጠረኝ፡፡
ዋረሶ አዲ

5. ፈጣሪ ሆይ ዳግም ኢትዮጲያችንን ለዚህ አሳልፈህ አታስገባት!!
ሰላም

6. Congratulation for EPRDF for bringing this freedom. By MOHA

19/11/2002

1. ሰው ሆይ አላማህን እንዲሳካ በሰው ህይወት ሳይሆን ለሰው ጥሩ በመስራት መሆኑን ነው፡፡
ደ/ር ኃይሉ

2. ካየውና ከሰማነው አሰቃቂና ዘግናኝ ታሪክ ተምረን የአሁኑ ሰላምና ዴሞክራሲ ዋጋ እንስጠው እና እንጠቀምበት፡፡
አንገሶም

3. አላህ በሰላሙ ጊዜ ስለፈጠረኝ አመሰግነዋለሁ “may they rest in peace “

4. እግዚቸብሔር ከዚህ ይጠብቀን!!
መላኩ

5. ዳግም እንዳይደገም!!!

6. እግዚአብሔር ለሰው ዘር ሁሉ እንዳይደርስ እለምናለሁ!!

7. እግዚአብሔር የሞቱትን እህቶቻችንን እና ወንድሞቻችንን በገነት ያኑርልን!!!
እስጢፋኖስ፤ ሮቤል፤ ቢኒያም

8. ከአሁን በኋላ ላለው ጌዜ እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ባርኮ ህዝቡ ሁሉ ጥሩ አስተሳሰብ እንዲኖረው መልካም ምኞቴ ነው ካጠፋን ዳግም ይቅርታ ስለመጠየቅ፡፡
እዮብ

9. More than anything I wish and want peace for my Ethiopia!!

10. Thanks to God! Today we are in peace!!

11. It will never happen again! God bless Ethiopia!!

20/11/2002

1. Are they human? I have nothing to say!!
Beza

2. አሁንም ምክንያት እየፈለግን ከምንቦጫጨቅ ምክንያት ፈልገን እንቀራረብ!!!

3. እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በገነት ያውለው!!!

4. እውነት ያሳዝናል! ህይወት ትርጉሟን ስታጣ መፈጠር ያስጠላል፡፡ እናንተንማ ማን ይረሳል!! “ ከቃላት በላይ ናችሁ”
አላዛር ፈለቀ

5. የምናገረውን አላውቅም በጣም በጣም ያሳዝናል፡፡ ታሪካችሁን አልረሳውም፡፡
ማቲ

6. ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ እስካለሁ ሁሌም አስታውሳችኋሁ፡፡
አሸናፊ ሙሉጌታ

7. እውነት እነዚህን ንጹሀን ወገኖቻችንን ለማጣታችን ከልብ ሀዘን ይሰማኛል፡፡ ዳግም ይህ ታሪክ በሀገራችን እንዳይደገም ምኞቴ ነው፡፡
ኢዛድ አብዱራህማን እና በሀይሉ ሀይሌ

21/11/2002

1. እርስ በርሳችን እንዋደድ የተደረገው ሁሉ በጣም አሰቃቂ ነው ለዘላለም እንዳይደገም!!!

2. ዳግም አያሳየን እግዚአብሔር ይርዳን ጠንክረን እንስራ፡፡

3. በመጀመሪያ ለዚህ ያበቃንን እግዚአብሔር እናመሰግናለን፡፡ፀሎቴ ግን ይህን መሰል አሰቃቂና አረመኔ መሪዎች በኢትየጲያ እንዳይነሱ ነው፡፡

4. በጣም ተፀፅቻለሁ፡፡

5. ያለፈውን ጠባሳ በመርሳት እባካችሁ የሀገሬ ህዝቦች እንዋደድ፤ እንፋቀር!! ሲያልፍ እንደተረት------

6. ይህን ነገር ዳግም ስለማናየው እግዚአብሔር ይመስገን!! ተበብረን በመስራት አገራችንን እናሳድግ! የናንተ ሞት ለኛ ህይወት ሆኗል፡፡ እናመሰግናለን፡፡

23/11/2002

1. ለትውልድ ራሳቸውን የሰጡ ኢትዮጲያዊያን እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በመንግሥቱ ያሳርፍ!!!

2. Never ever again!!! JN- ( ከሚዛን ተፈሪ)

3. Remember and learn about the past, but forgive reconciliation on justice.
Jemal

4. ዳግም ይህ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በተቀደሰች አገራችን እንዳይደገም እኛ አዲሶቹ ትውልዶች ቃል እንገባለን!!!
አስገዶም

5. አለም ሁሉ ከንቱ ናት ከንቱነትም በደርግ ጭፍጨፋ ይብቃን፤ አሁን ትውልዳችን ዘግናኝ ግፍንና መከራን አይፈልግም፡፡ በገርግ ዘመነ መንግስት ያየሁት ሁሉ እራሴን ብቻ ሳይሆን ወደ ኋላ የነበሩትን ወገኖቻችንን የግፍን ስቃይና መከራ እንዳሳለፉ አሳስቦኛል ›››በዚህ ይብቃን !!!
ገረመው

24/11/2002

1. ለመላው የኢትዮጲያ ሕዝብ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው የሰጡ ሰማዕታት መከበር አለባቸው!!

2. አሁን ያለንበት ዘመን የለውጥ ነው ያለፈው ጌዜ በሀዘን አለፈ አሁን ግን ዳግም ላይደገም ጉዞ ጀምረናል፡፡ ግን ያኔ ምን አይነት ዘመን ነበር? እግዚዘብሔር ነፍሳቸውን ይማራቸው፡፡

3. እንደማይደገም እርግጠኛ ነኝ፡፡

4. Learn from the past correct the present!!

25/11/2002

1. ይህ አሳዛኝ ታሪክ ድጋሚ እንዳይፈጸም ድዋ እናድርግ፡፡
ከታጁ

27/11/2002

1. እባካችሁ የዚህ ሙዚየም ዓላማ በሀይማኖታዊም ሆነ በአለማዊ ይቅርታን መስበክ ሲሆንም አሁንም በማይታወቅ ሁኔታ ይህን አስከፊ ታሪክ መድገም የሚፈልጉ አውሬዎች
እንዳይበቅሉ ህዝቡ ነገሮችን በእርጋታ ይመልከት፡፡

2. ፀጋዬ መሐሪ ስዩም ሁሌም እናስብሃለን!! ቤተሰቦችህ

28/11/2002

1. አይ የዛ ትውልድ ሰቆቃ እባካችሁ ይህ ታሪክ በዚህች ምድር እንዳይደገም እሻለሁ፡፡

2. ይህን ድርጊት ሁሉም ሊያወግዘው ይገባል!!!

3. ዮሐንስ ገ/ክርሰቶስ ካሣ ሁሉም ህያው ነህ!!!
ያንተው ቢንጐ ዲዲ

30/11/2002

1. ያለፈው አልፏል ዳግም እንዳይደገም እንጸልይ!!

2. ልቤ በሀዘን ተነካ እባካችሁ! ይህ ሰቆቃ አይደገም! እንቻቻል፤ እንግባባ፤ እግዚአብሔር እትዮጲያን ይባርክ!!

3. ይህን ድርጊት ወጣቱ በዚህ ዘመን እንዳይደግሙት አስተውሉ ፋፅሞ በሰላም መፍታት አለባቸው ትውልድ ጌታ ይርዳችሁ፡፡
ቅድስት ታደሰ

4. አሳፋሪ ሌላ ይባላል!!

5. አቤት እንዴት አሰቃቂ ነበር፡፡ መቼም በአሁኑ ጊዜ ይህ ሁሉ ጥፋት አይደገምም!!!

1/12/2002

1. ለፍርድ መቅረብ ብቻ መፍትሔ አይሆንም የሚገባቸውን ፍትሃዊ እርምጃ መወሰድ አለበት፡፡

2. ክብር ለሰማዕታት!!
ሀና

3. በእውነት ደርግ ኢትዮጲያን አይወክልም አባት ልጅን እንዲህ እያደረገ!!
ያሬድ

4. ነፍሳችሁን አምላክ ይቀበል!!!

2/12/2002

1. ያየሁት ነገር በቃላት ለመግለጽ ባልችልም ከዚህ መረዳት የሚቻለው ኢትዮጲያ ብዙ የጨለማ ዘመን እንዳሳለፈች ነው፡፡ ለወደፊት እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች እንዳይደገሙ የመቻል ፖለቲካ እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ማስፈን ያስፈልጋል፡፡

2. ያየሁት ነገር እጅግ ያሳዝናል፡፡ በወቅቱ ያልነበረው ትውልድ አሁን ያገኘውን ነፃነት እንዲያጣጥም ይረዳዋል፡፡

3. ባለፈው ያላየሁትን አሁን በማየቴ በጣም ደስ ብሎኛልም፤ አሳዝኖኛልም ኢትዮጲያ ያለፉ ብዙ ታሪኮችን እንዳሳለፈች አይቼበታለሁ፡፡

4. ያየሁት ነገር እጅግ በጣም አሳዛኝ እና ለወደፊቱ መደገም የሌለበት ነገር ነው፡፡
ሙባረክ ሹክሬ

9. ባየሁት ነገር እጅግ በጣም ተሰምቶኛል፡፡ የሞቱትን ነፍስ ይማር፡፡
ፈለቀ

4/12/2002

1. ያየሁት ነገር በጣም አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ በቃላት ለመግለጽ ባልችልም በጣም አሳዝኖኛል ለመጪው የኢትዮጲያ ህዝብ ጥሩ ትምህርት የሚሰጥ ስለሆነ ወድጄዋለሁ፡፡

2. እጅግ በጣም ያሳዝናል!!

3. ይህ የሚያሳየን አሁን ያሉት መሪዎቻችን ካለፈው ተምረው ለሰብአዊ መብት መከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለባቸው ነው፡፡

4. በጣም የሚያሳዝንና የሚያስተምር ያለፈ ታሪክ ነው፡፡

5/12/2002

1. “SENCOFA” ያለውን እይ ያለህበትን እይ የወደፊቱን አሻግረህ እይ!! ነስረዲን

2. ዳግመኛ እንደዚህ አይነት ደም መፋሰስ እንዳይመጣ ለፈጣሪ ብለን ይቅር በይ መሆን አለብን፡፡
ናሆም እና ካሚል

3. መደገም የለበትም በጣም የሳዝናል ሕይወት ምደር ላይ ብቻ አይደለም እግዚአብሐር ነፍሳቸውን በነገት ያኑር ነፍስ ገዳዮችን እንደስራቸው በሲኦል ያስገባቸው፡፡

4. አምላክ ሰዚህ ዘመን ስላደረሰን የተመሰገነ ይሁን፡፡ የተሰው ወገኖቻችንን ነፍስ ይባረክ፡፡ ከዶማ ራስ አመራርና ፈጻሚ ይሰውረን!!
አንበሴ ወንደሙ

5. ሞትህ ቢያሳዝነኝም የተነበይካት ጊዜ የደረሰች ስለሆን መንፈስህ እንኳን ደስ ያላት!!
መ/ር አወል ለመካ ኸለል
በቀይ ሽብር ላጣሁህ በሳሉ ተንቢ

5/12/2002

1. መቼም ቢሆን በማንኛውም ቦታ ልባዊ ያገር ፍቅር ይኑራችሁ!! ልቦና ይስጠን፡፡

2. በአገራችን እንደዚህ ያለ ጭካኔ ዳግም አይታይም፡፡

3. የነዚህ ጀግኖች ህልፈት ለዛሬዋ መጐልት ጉልበር ነው፡፡

7/12/2002

1. እኛ ከቤተሰብ መሀል ነው የወጣነው እናም ሰውን እንእንስሳ ሳይሆን እንደ ሰው ልጅ እንምራ!! ኢትየጶያ ለዘላለም ትኑር!!!

2. መሪዎች እባካችሁ መሪነትን ከእግዚአብሔር ተማሩ፡፡

3. በነሱ ደም እኛ ለመለምን፡፡

4. ጌታ ሆይ አገዛዝህ የሰላም ነው፡፡ ሰላም ለስ ልጆች ባይበሉም ጥጋብ ነው እግዚአብሔር ስለፈሰሰው ደም ምህረት ያድርግልን ይህ ለእኛ ትምህርት ነው፡፡ ሰላም

5. እኔ የማስተላልፈው መልክት ይህን ያህል አሰቃቂ መስዋትነት ተከፍሎበት የመጣውን ሰላም ዲሞክራሲና ልማት ለማኮላሸትም ሆነ ሰላም የሚያውክና ያለፈውንፋሽስታዊስርዓትለመመለስ ጥረት የሚያደርጉትነ ሁሉ ይህን ያህል መስዋትነት ተከፍሎበት ይህ ሰላምና ሁለንተናዊ ጥቅም በምን ዓይነት መስዋትበት እንደተገኘ ማሳወቅአለብን፡፡

6. ይህ ትውልድ ከዚህ ብዙ ነገር መማር አለበት እነዚህ ሰማዕታት ያደረጉትን ተጋድሎ መጠበቅ አለብን፡፡ ተስፋዬ ይርዳ

8/12/2002

1. በዚያን ጌዜ ባለመወለዴ ተደሰትኩኘ ዳግም እንደዚህ አይነቱን ነገር አታሳዩን አደራ!! ጎራ

2. ያን ጊዜ ባለማየቴ እግዚአብሔርን አመሰገንኩት በጣም ያሳዝናል ይህ ነገር በኢትዮጲያ ምድር እንዳይደገም ተባብረን እንጸልይ ሰዎች አደራ በየእመታችሁ ጸልዩ አደራ አደራ!!
ሄርሞን

3. አባቴ ከዚህ ተርፎ አብሯትን በመሆኑ እድለኛ ነን፡፡

4. ያለፈው አሰቃቂ ዘግናኝ ጊዜ ነበር ነው አሁን ግን ከዚህ በመማር አገራችን ለእድገት እንጂ ለጦርነት አንመኛት ግን እናንተስ ምን እየሰራችሁ ነው?

5. እውነት መቼም ተቀብራ አትኖርም፡፡
መዘክር

6. RIP Legesse bezu, እግዚአብሔር እንደሚጠብቅህ ተስፋ አደርጋለሁ!!
የልጅ ልጅህ ፌቨን ጸሐዬ

7. RIP our martyrs! We can’t be here without your death. Thank a lot!
Selam

8. May almighty God Bless Ethiopia!!

9/12/2002

1. ሰላም ውዷ!! ሰው በሰው ላይ ይህን ያህል ይጨክናል? የሀሳበ አውሬ ዘመን፡፡ ለዘመነኛው ሰው ሁሉ ቆም ብሎ የራሱን አስተሳሰብ የሚመልስበት ብሎም የሚመዝንበት ቦታ ይሁን!! ከታሪክ ይማሯል እንጂ አይደግሙትም፡፡ ነብዩ

2. እጅግ ዘግናኝ የሆነውን የአገዛዝ ዘመን በሙዚየሙ ለትውልድ ላስተላለፉ ሁሉ ክብር ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
ሙሉጌታ አስራት ካሣ

3. በረሰው ዜጎቻችን ክቡራን በሰማዕታት ያገኘነው ሰላምና ዲሞክራሲ ከእጃችን እንዳይወጣ አብረን እንጠብቅ፡፡ ገ/እግዚአብሔር በርሀ

4. ኢትዮጲያን ለዘመናት ወደኋላ የመለሰ እልቂት!!

11/12/2002

1. በጣም ነው ያዘንኩት መቼም የትም እንዳይደገም!!

2. በደርግ መንግስት የተደረገው ኢ.ሰብአዊ ተግባር የትም መቼም እንዳይደገም!!
ነብዩ አህመድ

3. በጣም ተሰምቶኛል!! በዚህ ይብቃን!!
ሲሳይ

4. የሰላምን ትርጉም ልናውቅ የምንችለው በዛን ጊዜ ስንኖር ብቻ ነው፡፡
ሄኖክ ጸጋዬ

5. በእነርሱ ደም እኛ ድነናል እግዚሰብሔር ኢትዮጲያን ይባርክቐቐ
ቢንያም ዘላለም

6. Where dies this great evil come from? For the sake of us all pray we learn from the mistakes of the past. Congratulations on atrulymovingmemorial......
Sam

12/12/2002

1. በዛን ወቅት ለከፈሉት መስዋትነት ልንኮራባቸው ይገባል፡፡ ነብሳቸውን ይማር!!
ሰላምወሰን ናይዝጊ

2. Let us not forget history does repeat itself! So I hope we all learn form this
Great still image “ of terror!
Bethelhem Tsegaiye

3. A great representation of a sad part of history that all should know abord.
Estifanos Tsegaye Kemisi

4. A real sad story but truly it will never happen!!

5. ክብር ለታጋይ ቤተሰቦች ይህንን አጽማቸውን በክብት እንዲያርፍ ላደረጋችሁ ሁሉ!! እግዚአብሔር የሞቱትን ወንድሞቻችንን እህቶቻችንን ለዘላለም በገነት ያኑርልን፡፡

6. ይህ ትውልድ ዳግም ይህን ዓይነት ነገር ማየት መስማት አይፈልግልም፡፡ ትውልድ ከዚህ ምን ይማራል፡፡ አገራችንን እግዚአብሔር በቸርነቱ፤ በምህረቱ ይባርካት!!
ኢዩኤልና ጓደኞቹ ( ድሬደዋ)

7. በውነት ትልቅ ትምህርት ነው ሰላም ወዳድ ለሆነ ሁሉ፡፡
አበበ ጌታቸው

8. አሁን ላለንበት ሰላም ለከፈሉት ለህይወታቸው ትልቅ ክብር ይገባቸዋል፡፡
ይድነቃቸው ገ/ስላሴ

14/12/2002

1. በጣም አሳዛኝ ጊዜ ነበር ቢሆንም ታሪክ ነው፡፡ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ስቃያችንን አይቶ የድል ዘመን አምጥቷል፡፡

2. ሁሉም ነገር ያሳዝናል፡፡ ነገር ግን አሁንም እጥንታቸውን እና አካላቸውን በሰላም እንዲያርፍ ፍቀዱለት ልብሳቸውን ካለ ይበቃል፡፡

3. ለሰከንዳት እንኳን ማሰብ የሚከብድ አሳዛኝ የታሪክ አጋጣሚ!!
ሀብታሙ አለሙ

4. God have Mercy on everyone!!

14/12/2002

1. ለሞቱት ጀግኖቻችን ይህን ዓይነት ማስታወሻ መዘጋጀት ደስ ብሎኛል፡፡ ለአጐቴ በላይነህ ገ/ማርያም፡፡
ናሆሚ አየለ

2. የሰማዕታት ጀግኖቻችን ምንግዜም አንረሳቸውም፡፡
ሚካኤል ሰለሞን

3. ለሞቱባቸው ቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁ፡፡ ጥሩም ሆነ መጥፎ የሰራነው ለትውልድ ይተላለፋል ይህ ትውልድ መዚህ መማር ይኖርበታል፡፡ ከደርግ ጭካኔ ያድነን እላለሁ፡፡
ተስፋዬ

4. ባየሁት ልቤ በጣም አዝኗል፡፡ እግዚአብሔር እንዲያስባቸው እጸልያለሁ ይህ መደገም የሌለበት ቀይ ስህተት ነው፡፡
ታምራት

5. እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከእነሱ ጋር ነው፡፡
ግርማ ሽፈራው

6. I felll a Horable thing ever!!
Heruy

17/12/2002

1. እውነት ይህ ሄሉ በሀገሬ ሰው ላይ ተፈጽሟል!!!

2. እነሱ ላገራቸው ይህን ተቀበሉ እናስ?
ሙሉጌታ

3. አሁን ላለንበት እኛነታችን ሰማዕታት ላደረጉት ተጋድሎ በእውነት የማይረሳ ከ ጄኔሬሽን ወደ ጄኔሬሽን የሚተላለፍ ትልቅ ታሪክ ነው!! Long Live to Ethiopia
Nure

4. They did everything they could for their country!! The rest jobs is ours!!
Yonas Tesfaye

5. Rest and Peace!!
Abel Bahre

6. ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን ሙዚየም ስመለከት የተሰማኝን በቃላት ለመግለጽ አቅቶኛል ይርግ መንግሥት በቃላት ሊገለጽ የማይችል አረመኔ መንግሥት ነበር፡፡ ዘመን መጥቶበት
እግዚአብሔር ገለበጠው እንጂ ከዚህም የበለጠ ህዝብ ያል ነበር፡፡

7. ወንድሞቼና አባቴ ከዚህ መአት ነበር የተረፋችሁት!!!
ዮሴፍ አባተ

8. ንጹሐን ወንድሞቼ ደማችሁ ፈሶ አልቀረም እኛም የደርግ መቃብር ረግጠን ልማት፤ ሰላም፤ ዲሞክራሲ ተጐናጽፈናል፡፡

9. በጣም ያሳዝናል!!

10. ይህ አሳዛኝና አስነዋሪ ድርጊት እንዳይደገም!!

19/12/2002

1. ይህንን ለሰሩ ስራውንም ላሳወቁ ታላቅ ምስጋና አለኝ፡፡

2. ይህ አስከፊ ስርዓት እንዳይመለስ ቀጣይነት ያለው ትግል ማካሄድ እንዳለብን አልዘነጋውም!

3. ወገኖቼ ሆይ! እናንተ እንደ ሻማ ቀለጣችሁ ለኛ ብርሀን ሁናችኋል እና ስራችሁና ስማችሁ ለዘላለም ይኖራል፡፡

4. ታሪኩ እንዳይደገም ህዝብ መረባረብ አለበት፡፡ ይህን ታሪክ ላሳወቁን ትልቅ ምስጋና ይድረሳችሁ፡፡

5. አሁን ላለመፈጠሩ ማስረጃ አለ? የለም፡፡

21/12/2002

1. ያኔ አለመወለዴ ደስተኛ ነኝ፡፡ አባዬ እንዴት ያንን ጌዜ አለፍክ?

2. እየፈራሁ ነው ያየሁት መቼም እንዳይደገም እመኛለሁ፡፡

3. ያ ጊዜ ታሪክ ሆኖ አልፏል መቸም አይደገምም!!

4. እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይጠብቅ!! እባካችሁ እንዋደድ!!

5. እዚህ ያየሁት ሁሉ በጊዜው የተከሰቱ እውነት ነው፡፡ የ56 አመቱ ጐልማሳ፡፡

6. የሰላም ትርጉሙ ገብቶኛል፡፡

7. ያ ጊዜ ተመልሶ እንዲመጣ አልፈልግም፡፡
ሳሚ

8. እንዳይደገም ጥንቃቄ ይደረግ፡፡

9. መቼም እንዳይደገም የበኩሌን እጥራለሁኝ!!

10. በምድራችን ላይ እንዲህ ያለ ግፍ እንኳን መደገም አንስማ!!

22/12/2002

1. የትውልድን ክፍተት የፈጠረ፤ የሀገራችንን እድገት ወደኋላ የጐተተ የዜጐችን ሀሳብ በነጻነት የመግለጽ መብት የነፈገ ጨካኝ ስርዓት ያደረሰውን በደል ፍንትው አድርጐ ያሳየን
ስለሆነ የአሁኑ ትውልድም ይ መሰል ስርዓት አይሻም!! ሰላም፤ ብልጽግናን እንሻለን፡፡

2. እንደዚህ ዓይነት አሰቃቂ ነገር ዳግም እንደማይከት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ አሁን እኛ እምንፈልገው ነገር ነጻነታችንን ባስከበሩልን ሰማዕታት አማካኝነት የምንፈልገው ነገር
ልማት እና ልማት፤ አንድነት!!!

3. በአረመኔው ደርግ የተዋጣችሁ ምንግዜም ስራችሁ ህያው ነው፡፡ ሁሌም በህሊናዬ ውስጥ አላችሁ፡፡ እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በገነት ያኑርልን፡፡

4. እንፋቀር ሁላችንም!! ውበት

5. ይህ አይነት አገዳደል ዘግናኝ ስለሆነ፤ ከዚህ በኋላ በአገራችን እንዳይደም ምኞቴ ነው፡፡

23/12/2002

1. በእውነቱ በታሪክ ከማውቀው ይልቅ ዛሬ በአይኔ ሳየው አዘንኩ፡፡

2. ታሪካችንን ለሕዝብ በማሳየታችሁ እናመሰግናለን፡፡
ዳንኤል ጌጡ

3. ታሪክን ካለፈ በኋላ መመልከት ለመጪው ትውልድ ትምህርት ነው፡፡
W.T

4. አረመኔያዊ አገዛዝን ለሚያስቡ መማሪያ ይሆናል!!

5. ክፉ አውሬ እንኳን ይራራል የሰው ልድ እንደዚህ አይት ስራ ይሰራል? ባለጌ !!
ለምለም በለጠ

6. ዳግም የማናየው ግፍ!!
A.K

7. እኔ ላየሁት የፈራሁ እናንተ እንዴት አስገባችሁት?
ሚኪ

8. Very sorry for all the families that suffered through this!
Betty

9. ዘግናኝ! በሰው ልጆች ቀርቶ በእንስሳ ላይ ሊፈጸም ያልተገባ የሰይጣን ስራ እግዚአብሔር ሀገራችንን ይጠብቃት!!

10. በሁሉም ነገር ልቤ በጣም አዝንዋል!!

11. ያለፈው እንዳይደገም ለመጭው ብሩህ ተስፋ እንመኛለን፡፡

24/12/2002

1. ታሪክ ሆኖ ይቀር ዘንድ እንመኛለን፡፡

2. ለዘለዓለም መደግ የሌለበት ታሪክ ነው፡፡

3. እስከዛሬ በፊልም ነበር አጽም ያየሁት ዛሬ ግን በአይኔ ሳይ ያስፈራል፡፡

4. እነዚህ ባይኖሩልን እኛ የት ነበርን፡፡

5. እውነት ነው ግን?

26/12/2002

1. ታሪኩ እጅግ አሳዛኝ ነው አይካድም፡፡ ዳግም እንዳይሆን እንጣር!!

2. በጣም አሳዛኝ ነገር ነው መንግሥቱ ኃ/ማርያም የሰራው ስራ በጣም ያሚያስቀይም ነገር ለወደፊቱ ቢሆንም ትምህርት ይሰጣል፡፡ በጣም ተሰምቶኛል፡፡ ኢህአዴግ ግን ሰውን አይገልም እሱ በእስር ቤቱ ነው የሚገለው አመሰግናለሁ፡፡
ደርባባው ኃ/ማርያም

27/12/2002

1. እጅግ አሰቃቂ ተግባር ነው ለአሁኑ መንግስታችን ምስጋና ይግባው፡፡

2. እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ከእንደዚህ አይነት ግፍ ይጠብቃት!! በረከት

3. እንደዚህ አይነት ነገር ለመጪው ትውልድ ጠቃሚ ተግባር ነው

4. መቼም ቢሆን እንደዚህ ያለ ግፍ በኢትዮጲያ አይደገም፡፡ ጌታመሳይ ካሣ

5. ህይወት ተወሳስባ ሆኖብን አበሳ ቅጣቱ ሆኖብን በዝቶብን ስንፈልግ ካሳ ልክ በሌለው ፍቅር እራሱ ወዶናል
ሰላም ከላይ እንጂ ከዚህ መች ይበኛል!!

6. ይህን ቦታ በማየቴ እድለኛ ነኝ! ኢትየጲያን እግዚአብሔር ይባርክ!!
ሚኪአን፣ አበል እናዱአም

7. ኢትዮጲያ መች ይሆን ከዚህ የምትድነው!! ጥሩ ቀን ያምጣልን፡፡ ደስ የሚል ታሪክ!!

2/13/2002

1. ኢትዮጲያ ሀገራችንን እግዚአብሔር ይጠብቅልን ይባርክልን! አሜን

2. ህልውናችን በቀድሞ ሰማዕታት ህይወትና ደም የተገኘ ነው እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ከዘር እልቂት ይታደግ!!
አይናለም ታደሰ

3. ከዚህ አሰቃቂ ስርዓት ክብር ይገባቸዋል፡፡
ኤፍሬም

4. ሞት ለማንም የማይቀር ዕጣ ፈንታ ቢሆንም በናንተ ሞት ግን አዘንን!!

5. መጪው ትውልድ ሁሉ ይህንን ያውግዝ!!

3/13/2002

1. መጪውን ዘመን ከእንደዚህ አይነት ጠባሳ እናድናት እንጠብቃት፡፡
ብሩክ

2. በዛን ዘመን ወጣት ባለመሆኔ እድለኛ ነኝ!! ዳግመኛ ይህን አይነት ክስተት ትውልድ እንዳያይ የዘወትር ጸሎቴ ነው!! ኢትየጲያ በልጆቿ ትበለጽጋለች!!
ደስታ ፈንታ

3. May this be remembered not to happen again!!
Lonise (Belgium)