Content on this page requires a newer version of Adobe Flash Player.

Get Adobe Flash player

1. ሁሌም እናስብሃለን!!

2. በጣም አዝኛለሁ እግዚአብሔር ነብሳችሁን ይጠብቅ!!

3. ሁሉም መልካም ይሆኛል!!

3/1/2003

1. Everything has its awn time!!
Dan

2. በጣም አዝኛለሁኝ ሁሌም አስብሀለሁ!! እግዚአብሔር ነብሳችሁን ይማር!!
ሳሙኤል ዳጨው

3. ይህን ነገር የኢትዮጲያ ህዝብ መቼም ሲረሳው የማይችል ነገር ነውና ዳግም እንዳይደገም ስል በአምላክ ስም እጠይቃለሁ፡፡ አመሰግናለሁ

4. ማንም ሰው ዳግም አለመፈጠሩን እንዲያስ ማድረግ ብቻ ነው ለእናት ሀገር ኢትየጲያ የሚጠቅማት ማሰብ እንደራስ ነው፡፡

5. የማይረሳ ትልቅ ታሪክ ነው አልረሳውም!!
እስጢፋኖስ ጀምበሬ

6. ለዛሬ ማንነታችን የተከፈለ መስዋትነት ነው፡በጣም ያሳዝናል!!

ዩሀንስ

7. ዳግም ያለፉት አሰቃቂ ሥርዓት መደገም የለበትም፡

ታምራት

8. ለሀገራችን ሲባል የተደረገ መስዋት ነው ያሳዝናል!!

9. ይህን ሥራ ለሠራችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!

10. መቼም እንዳይደገም!!
ሚኪያስ

11. የሰው ደም በከንቱ አይቀርም!!

12. I wish it won’t happen to all of you. Dear uncle I took place to make
Good.

13. ለትውልድ እግዚአብሔር ቀንን አመጣ!!

14. ሁሌ እናስባችኋለን ላረጋችሁትም ትግል እንወዳችኋለን፡፡

15. አሁንም የአንን አረመኔያዊ ስርዓት የሚደግፉና የሚመኙ በመኖራቸው በጣም እዝኛለሁ!
ሰማዕትነታችሁ በከንቱ አልቀረም!!

16. የመጨረሻ ያለመግባባት ጥግ ምን እንደሆነ ሳይ አዝኛለሁ!...ሌላ ሀገር ያለ ይመስል..

6/1/2003

1. ይህ ሙዚየም ለትውልድ ትልቅ ትምህርት ነው፡፡

2. በኢትዮጲያ ውስጥ ሰላምና ፍቅር ይስጠን!!         

7/1/2003

1. ለአጐቴ ለፋንታሁን ተፈራ ምንግዜም በገነት ያኑርህ!!
ጋሻው ሲሳይ ተፈራ ( የወንድም ልጅ)

2. በቃላት ለመግለጽ የሚያስቸግር ጉድ! የዚህ ዓይነት ጭፍጨፋ ለደርግ ፋስሽት ሞት ሲያንሰው ነው!!

3. ወንድሞቼና እህቶቼ በእናንተ ቁስል እኛ ድነናል እና እግዚአብሔር ይባርካችሁ እወዳችኋለሁ፡፡ ሁሌም ነብሳችሁ በቀኝ ትቀመጥ፡፡
ዴቭ

4. የዚህ ዓይነት ጭፍጨፋ እንዳይደገም የአሁኑ ትውልድ ከባለፈው ተምሮ አምባበነንና ጨፍጫፊዎችን ሊያወግዝ ይገባል፡፡

5. ይህ ሁሉ ግን ለምን? እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይባርክ ይጠብቅ ፍቅርንም ይስጠን!!

6. የሰማዕታት ዓላማ ዘላለማዊ ህያው ታሪክ ነው፡፡
ሰለሞን

7. ሁሌም ታሪክ ይፈርዳል፡፡
A.M

8. በእኔ ዘንድ ዘላለማዊ ናችሁ እግዚአብሔር ሕይወታችሁን በገነት ያኑረው፡፡

9. ስምኦን አይዞህ በገነት ያኑርህ!!

10. ምስኪን ወገኖች በጥቂት ፖለቲከኞች ፍላጐት ረገፋችሁ መስዋዕትነታችሁ ህይወታችን ነው፡፡

11. History will judge always!!

12. በደማችሁ እኔነቴን በምድር ላኖራችሁ ነፃነቴን ላወጃችሁ ሁሉ ፈጣሪ ነብሳችሁን በገነት ያኑረው!!
አህመድ አ/ቃድር ( ከአፋር)

13. የሠራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ነብሳችሁን በገነት ያውለው፡፡ ከልብ በሆነ ስሜት

14. መጪው ጊዜ ከእናንተ ድል ጋር ብሩህ ነው እ/ር ኢትዮጲያን ይባርክ!! አባታችን አልሞትክም

ሀ/ስላሴ                     

11/1/2003

1. እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው እንዲህ ዓይነት ድርጊት በኢትዮጲያ ምድር አይደገም!!

2. I have admiration for the Ethiopian spirit in the face & such cruelty. Humanity is good on the whole!!

12/1/2003

1. አላህ የሞቱትን በገነት ያኑርልን!!

2. በጣም ጥሩ ነገር ነው ያየሁት በተለይም ወጣት ከበደ ወርቁ እጅግ በጣም እንወደዋለን! እንደንቀዋለን፡
ብሩክታዊት፣እየሩስ እና ንፁህ

3 በምንም ዓይነት መንገድ እና መልክ በኦትዮጲያ አገራችን እንዲህ አይነት ጭካኔ እና አረመኔነት አይደገም፡፡ እጅግ ዘግናኝ ድርጊት ነው፡፡ እግዚአብሔር ፍቅርን ይስጠን!!
ለሰማዕታት ቤተሰብ መፅናናትን ይስጥ፡፡

4. እግዚአብሔር የሞቱትን ነብስ ይማር!! ሁለተኛ በኢትዮጲያ ምድር እንደዚህ አይነት ስቃይ ምንግዜም ያከተመ ሆኖ ይቅር!! በወቅቱ የነበርኩ ሰው ነው፡፡

5. እግዚአብሔር የሞቱትን በገነት ያኑርልን!!
ኤስሮም ገሰሰ

6. ካለፉት መማር ጥሩ ነው፡፡ ጥሩ ታሪክ ሰርተን እንለፍ! እግዚአብሔር አስተዋይ ልብ ይስጠን!!
ዘካሪያስ

7. መሞት የሚፈልግ ሰው የለም ለህዝቦች ልዕልና መሞት ግን ታላቅ ክብ ነው፡፡ ታሪክ እንደ ወራጅ ወንዝ ቢገሰግስም እናንተ ስራችሁ ህያው ነው፡፡ ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!
ዮሲያስ ገ/መስቀል

8. ሞት ያለ ነው! በዚህ መልኩ ሲሆን ግን፡፡
ኪሩቤል

9. በራስህ እንዲደረግ የማትፈልገውን በሌሎች ላይ አታድርግ!!!
ራሄል ሀጐስ

10. እኔ ባየሁት ነገር በጣም አዝናለሁ!!!

13/1/2003

1. ይህ የሰማዕታት መታሰቢያ ቂም በቀል ጥላቻ ለአገር ምንም ፋይዳ እንደማይገኝ አሁንም ያሉት መሪዎች

2. ላመንበት ነገር የምንሞት ያድርገን!!

3. ይህ የሰማዕታት መታሰቢያ ቂም በቀል ጥላቻ ለአገር ምንም ፋይዳ እንደማይሰጥ አሁንም ያሉት መሪዎች ከዚህ ቂም፤ በቀል፤ ተንኮል፤ ዘረኝነት እንዲወጡ ትልቅ አስተማሪ ነው፡፡
እስማኤል

4. ይህ የሰማዕታት መታሰቢያ ቂም በቀል ጥላቻ በሀገራችን መቼም እንዳይደገም እኛ ታዳጊዎች ሀላፍነት አለብን፡፡
እስጢፋኖስ እንየው
ሄኖክ ሰለሞን

5. ይህ ታሪክ ያለፈው ትውልድ የፈጸመው መጥፎ ድርጊት ነው፡፡ የዛሬው ትውልድ ደግሞ ከመሰል መጥፎ ድርጊት ተቆጥቦ ለሀገሪቱ አልሚ ተግባር እንዲፈጸም አደራ እላለሁ፡፡
ፍቅረስላሴ አድማሴ

14/1/2003

2. ለምን ሞቱ ይሆን? ማን ፈረደባቸው? ምን ዓይነት ዳኛ ነው የፈረደባቸው? ወይ ራዕይ የሌለው ጨካኝ ሰው በላ ነው፡፡ ደርግን እጠላዋለሁ፡፡

3. እግዚአብሔር ሀገራችንን ሰላም ያርጋት!!

4. በደማችሁ ጸዳች ኢትዮጲያ!!

5. ከዚህ አሳዛኝ ታሪክ ብዙ መማር እንችላለን!!

6. ይህ በእነሱ ይብቃ እኔም ላገሬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ተማርኩ!!

7. ይህንን በየመ/ቤቱ፤ በየት/ቤቱ እየሄዳችሁ ብትጋብዟቸው በጣም በቂ እውቀት ያገኛሉ ያላዩ ብዙ አሉና!!

8. ትናንት እናንተ በከፈላችሁት መስዋዕትነት ዛሬ ላለነው ትልቅ የአላማ ፅናት ተምረናል፡፡

9. እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነበር በየትኛው አለም ተደርጐ የማይታወቅ አሰቃቂ ድርጊት ነበር፡፡

10. ለሰማዕታት እግዚአብሔር ገነትን ያውርሳችሁ!!

11. God Bless you Jerry!!

5/1/2003

1. ከአምባ ገነን መዳፍ ያወጣችሁን በደምና አጥንታችሁ ነው፡፡
ደምሴ ብርሃኑ
ሞገስ ብርሃኑ
ተፈራ ብርሃኑ
ግርማ ብርሃኑ
እንዲሁም ለተስፋዬ መኰንን
ለሽፈራው ዘለቀ
ከፈለቀ ተፈራ ብርሃኑ

2. Behind History..... There is power & politics.

3. ይህ ታሪከ መንግስቱ ከፈጸማቸው ግፎች በጣም ጥቂት ይመስለኛል፡፡ አዲሱ ትውልድ ከዚህ የእልቂት ታሪክ በመማር እንዳይደገም መታገል አለበት፡፡ ለእድገትን ለስልጣኔ
ወደፊት መጓዝ አለበት፡፡

4. ያ ትውልድ? ክብርና ሞገስ ለሰማዕታት ይገባቸዋል፡፡ ለዛሬ ማንነታችን ናቸውና!!

5. ደርግ እንዲህ አይነት ታሪክ ያለው አይመስለኝም ነበር፡፡ ሙዚየሙ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚሁ ይብቃ! ሀገራችንን እናለማታለን፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

6. እግዚአብሔር ነፍሳችሁን ይማር!! ካለፉት እንማር፡፡
W.A


17/1/2003

1. "ዘይገርም ሀገር
ዘይገርም ነገር
ይህ ሁሉ አልፎበት
ያልጠፋች ይህች አገር”
ዘላለም

2. የሰማዕታት ደም አሁን እየበለጸገች ለምትገኘው ኢትዮጲያ ጉልህ የሆነ ድርሻ አለው!!
አበበ

3. ለአላማቸው የታገሉ ሁሉ ባይኖሩም ስራቸው ይኖራል፡፡
ወንድወሰን

4. Thank you for the eye opening display & wonderful explanation!!
Sara Stwewart

18/1/2003

1. ብንኖር እንጠቀማለን ሌላውንም እንጠቅማለን፡፡ እራስ ወዳድነት ላገርም ለራስም አይጠቅምምና!! ያለፈው እንዳይደገም በታደሰና በተማረ አእምሮ ለሰላምና ለልማት እንጂ
ለጥፋት መፍትሔ አንሁን፡፡
አበበ ታፍሰ

2. እንዳይደገምብን ለጥላቻ ሳይሆን ለልማትና ለመፈቃቀር እንትጋ!!
አማኑኤል ደሳለኝ

3. ለኢትዮጲያ ህዳሴ ያለፈውን ትተን በይቅርታ ወደ ፈጣሪ እንመለስ  

19/1/2003

1. ታሪክን የመያዝ ዝንባሌያችን ከዚህ በተሻለ እንዲሆን እየተመኘሁ ዘመዲቻቸው በዚህ አሰቃቂ ግድያ የሞተባቸውን መፅናናትን እመኛለሁለለ ይህንን ያየ ለራሱ ይጠንቀቅ!!

2. በመንፈሳዊ ህግም ሆነ ወይ በአለማዊ ህግ መተዳደር ጠቀሜታው የጐላ ነው!! እንዳለማው ሰይፉ ግራኝ
አልማዝ ይመር
አየሉ

3. ለኢትዮጲያ ሀገራቸው የተሰው ኢትዮጲያውያኖችን ለማስታወስ የተቀመጠው ሙዚየም የአሁኑ ትውልድ በፍቅርና በሰላም ለሀገሩ እንዲተጋ ያነሣሣዋል፡፡ ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!
N.A

4. I was really upset, when I see all things what the Derg regim was doing. I don’t want to happen again & see it our coming generation.
God Bless Ethiopia
Elias

5. It’s amazing! I can’t believe the happen to my country I wish them rest in Peace!!
Andy (Canada)

6. Freedom is not free
K.B

20/1/2003

1. የትላንትናው ገድል ለዛሬ ክብራችን ነው፡፡

2. ይህንን ነገር ሳይ አሁን ያለሁበትን መንግሥት አመሰገንኩ! በጣም ያሳዝናል፡፡
ኤልሳ

3. ባየሁት ነገር በጣም አዝኛለሁ!! ለቀጣዩም ትውልድ ይህ አይደገምም፡፡
ኪሩቤል ወልዴ

4. የኋላውን እየረሳን ወደፊት እንራመድ፡፡

5. በጣም ያሳዝናል የሰው ልድ እንደማይረባ ነገር የተወገረበት ስለሆነና ነገር ግን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ እንደዚህ አይነት ነገር ስለማይገም በምድራችን፡፡ እ/ር
ኢትዮጲያ ይባርክ፡፡
ህሊና ግርማ

22/1/2003

1. የደርግ ስርዓት በነበረው ጭካኔና በደል ብንጸጸትና እኛ ወጣቶች ደግሞ ሀገራችንና ህዝባችን በልማት እናሻሽላለን፡፡
A.A

2. አምላክ ኢትዮጲያን ይባርክ!!

3. አባቴ ሆይ አደራ አደራ ከፍታችን ያለው ዘመን የፍቅር ይሁን!!

4. There is always a better way doing towards.

5. ይህ ግፍ በደል ስቃይ መቼም አይደገምም!!

6. በእውነት ይህ ዜጋ ዜጋ ላይ ያደረሰው በደል ከኢትዮጲያውያን የሚጠበቅ አልነበረም! በየሰከንዱ የተነፈስናት አየር ትልቅ የህይወት መስዋዕትነት ተከፍሎባታል፡፡

7. የሰማዕታቱ ደም የትም አይቀርም ደርግ የማይረሳ አሳዛኝና መቼም ሊፈጸም የማይችል ለመናገርም የሚዘገንን ነገር ጥሎ አልፏል፡፡ በኢትዮጲያ የዚህ አይነት ድርጊት መፈጸሙ
አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ በዚሁ ይብቃ!!
ኤርሚያስ

8. Oh! It will never & ever happen again in our country!!

25/1/2003

1. አንዳይደገም አደራ!!

2. እኛ የተተኪው ኢትዮጲያውያን አቅኝ ትውልዶች ይህንን የማናውቀውን ታሪክ በማየታችን አዝነናል ይ ታሪክ መቼም ሊደግ አይገባም፡፡

3. የንፁህ ሰው ደም ፈሶ ላይቀር በከንቱ መልፋት የሟች ደም ሲዋቀስ አየሁ!!

4. ብዙው ነገር በተለያየ መንገድ ሲገለጽ ሰምቻለሁ የደርግን አስከፊነት ባውቅም ዛሬ ግን በአይኔ በማየቴ እንዳይደገም እየተመኘሁ የህዝብ ልጆች መውደቁ ግን የሰማዕታቱ
ህያውነትን ያሳያል፡፡

5. ይህ ሁሉ ነገር ግን እውነት ነው፡፡

6. ኢትዮጲያን በልጆቻቸው ላይ በእህት ወንዶሞቻቸው ላይ ይህን ድርጊት መፈጸማቸው አረመኔ ያስብላቸዋል፡፡ በአሁን ጊዜ ግን ፍቅርና፤ሰላም፤እድገት፤መስራት ይኖርብናል
መቼም አይደገም፡፡        

7. አባቴ በደርግ ተሰቦ ውትድርና ባይሄድና ትምህርቱን ቢጨርስ ሕይወታችን ይቀየር ነበር፡፡
ይበልጣል ጥላሁን
ሔኖክ ባያብል

27/1/2003

1. ከደርግ ጥይት ያመለጠችው እናቴ ይህን ብታይ ምን ትል ይሆን? ደርግ በግልፅ ሜዳ ላይ ይገድል ነበር፡፡ የዛሬው በድብቅ የሚደግለውን ማን ይየው ቀን ይምጣ ይሆን? ሁሉም
አልበጀንም፡፡ ፍቅር ለዘላለም ያሸንፋል!!

2. ክብር ለሰማዕታት!! የእኛ ትውልድ ከዚህ ሊማር ይገባል፡፡
A.S

3. ሰይጣን እንኳን ይህን ያህል የሚጨክን አይመስለኝም!!
ሉሲፈር

4. እኔ ሌጊዮን ነኝ እውነት እላችኋሁ የደርግን ያል መጨከን አልችልም፡፡
ከሌጊዮን

5. ደርግ በጣም ክፉ መንግሥት ነው የሲኦል መግቢያ መስፈርትን ከመቶ በላይ ያሟላ አሪዮስ!!

6. Whatever happens happens for reason but there was no reason in this!!

7. ደርግ ክፉ ነው!! ለዛን ግዜ ኖሬ ይህን ሁሉ ስቃይ ባለማየቴ የወገኔ ቁስል ሳያመኝ ቀረ ዛሬ ብን ህመማቸው አመመኝ፡፡ ለኔ ሲሉ የሞቱ ለእግዚአብሔር ያድርጋቸው፡፡
ጥሩአየር

8. ምስጋና ሰተሰውት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ልፋታችሁ መናአልቀረም እሽ!!
ቢዮር
ሀሚድ ሙለር

9. ብልሀትም ዕውቀትም የሌለው ሰው ሥልጣን ካገኘ እንዲህ ነው፡፡ ፈጣሪ በመለስ ክሶናል!!
ሄንዳስ    

28/1/2003

1. በዛሬው ይህንን ታሪክ በማየታችን ፤ ይህንንም ታሪካወዊ ቅርጽ ስላወቅን በጣም እናመሰግናለን፡፡

2. እዚህ ሙዚየም ላይ ያየሁት ነገር በጣም አስገራሚና የሚያስደንቅ ቦታ ነው፡፡
ሄሊ

3. Bless those who have paved the path for democracy and equality!!

4. በእውነት በጣም ያሳዝናል የደርግ ስርዓት ምን ያህል ጨካኝ እንደነበር ወጣቱ ከዚህ ሙዚየም ብዙ ትምህርት ወስደዋል ቀጥሉበት!!
ኋኋ

5. እውነታው ይህ ከሆነ ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የማይጠበቅ ነው!!

29/1/2003

1. በጣም ያሳዝናል ግን ብዙዎቹ ከአፈር ጋር ያሉ ነገሮችን አይቻለሁ፡፡ ለወደፊት እድሜ እንዲኖራቸውና ለታሪክ መረጃ እንዲሆኑ ከተፈለገ ከመሬት መውጣታቸውን በፅሑፍብትገልፁ መልካም ነው፡፡
ገዛኸኝ

2. ይህን ያህል ህዝብ ያለቀበት ኢሰብአዊ ድጊት መቼም እንዳይደገም
ሀይሌ

3. በጣም ያሳዝናል ለአሁኑ ትውልድ ትልቅ ትምህርት ነው፡፡ መንግሥትን እንመሰግናለን፡፡
የኋላሸት

1/2/2003

1. ኢትዮጵያ ትደግ ስሟ ከፍ ይበል ክብር ለሰማዕታት!!

2. ያለፈው አይደገም!! ኢትዮጵያ ብዙ ሚሊኒየሞችን በሀያልት በናንተ መስዋትነት ትቀጥላለች አላህ ከናንተ ይሁን!!

3. ክብር ለሰማዕታት ይሁንላችው ይህ ሙዚየም በጣም አስደሳች ነውና ይደግ ይበርታ እላለሁ፡፡
ከባሌ ጎባ

4. To God be the glory for our Nation-Ethiopia is moving forward never backward!!

5. የእግዚአብሔር ምህረት በኢትዮጵያ ይን ዳግም ከጥፋት ያድነን!!

2/2/2003

1. እግዚአብሔር መልካምን ዘመን አምጥቷልና እናመሰግነዋለን፡፡
ናቲ

2. ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች አሜን!!
ቢ.ቢ

3. This will never happen as long as we are alive!!
L.A.

3/2/2003

1. የሰማዕታ ተጋድሎ በልማት ይሄ ትው፤ድ ይግለፀው!!
አብነት አበራ

2. በጣም ደስ ያለኝ ግፈኞች ሁሉ የትም አለማምለጣቸው፡፡ እግዚአብሔር ፍርዱን
ይስጣቸው፡፡
ሀና ከአዋሳ

3. ሁሉም አልፏል ቀጣይ ስህተት እንዳይደገም!!
ቴዲ እና ማርታ

4. ለሞቱት ነፍሳቸውን ይማር!!

5. እገግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ አሜን፡፡ እየሱስ ያድናል፡፡
ናትናኤል

6. ሰላምና ደሞክራሲ ሁሌም ለአገራችን ይኑር!!
ሀብታሙ ጂሣ

7. እርስ በርስ አንገዳደል፡፡ ለመጪው ትውልድ ፍቅር እናሰተምር በዚህ ይብቃ!!
ኤኤ.ቢቢ

8. Let peace be with you, you are the missionary of eternal peace!!

4/2/2003

1. ጌታን የምለምነው ይህ ታሪክ ዳግም በኢትዮጲያ እንዳይመለስ ነው!!!

2. ሙትም ኃይል አለው፡፡ ለሚሰማው የሚነግረው፡፡
መላኩ

5/2/2003

1. ጌታ ሆይ እባክህ ምድራችን ባንተ ምህረት ትካስ/ካሣት!!

2. በአውነቱ ኮነ በጣም አሳዛኝ የሆነ ጭፍጨፋ ነው፡፡ እንደማይደገም ተስፋ አለን፡፡

3. ይህ ነገር እንደማይደገም አሁንስ ምን ተስፋ አለ?

4. ሰው ሁሉ ይህን በማየቱ በርግጥ ልቡ ከተሰበረ ይሔ ሙዚየም በራሱ ብዙ ተስፋና ብርሀን ይሆናል!! ምህረት

5. ያለፈውን ትተን በጐውን ብቻ በመውሰድ ትውልድን እንታደጋት!!

7/2/2003

1. ማን ያ!! ጊዜ እንደገና እዲመለስ አይፈልግም አይፈቅድምም!!

2. We don’t want anymore war!!

3. እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በገነት ያኑረው ይሄ ሁሉ ትግል ለኛ ነው፡፡ በለጠ ተሾመ

4. ቀጣዩም ትውልድ እንዳይደገም በመነጋገር ይመን፡፡

8/2/2003

1. አሁን ላይ ሆነን ኑሮን ስናማርር ያለፈው ትውልድ ምን ይበል? በኔ በኩል ፈጣሪ አምላካችን ያለፍንባት ታሪክ ዳግም ሳይሆን እስከመቼም እንዳይከሰት ይርዳን፡፡ ግን ለምን?
አዳነ

2. የኢትዮጲያ ህዝብ ሆይ ካለፈው እንማር!!
አስማረ

3. ለተጐጂ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛን!!

4. ፍቅር ይስጠንና የተሻለ ኢትዮጲያን እንፍጠር፡፡ ነፍስ ይማር!!!
ኪሩቤል

5. እግዚአብሔር መልካም ነው በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፡፡ ነፍሳችሁን በገነት ያኑራው!!
ሀና

6. እግዚአብሔር ነግሳችሁን በገነት ያኑረው!!
ዴቭ

7. የኢትዮጲያ የውድቀት ሚስጥር!!

8. ለዘላለም አያሳየኝ!!

9. Thanks be unto the Lord that this time has come!!

10. Lets learn from the past and try to make the future a better place!!

9/2/2003

1. ይህ አረመኔያዊ ተግባር ታሪክ ሆኖ ይለፍ!!
ዮሴፍ ክፍሌ

2. ይህ ታላቅ የታሪክ ስህተት እንዳይደገም የአሁኑ ትውልድ ትልቅ አደራ አለበት፡፡
ናቲ ታዬ

3. እነዚህ ሰዎች አረፉ እንጂ አልሞቱም፡፡ ዳግም በኛ ይወለዳሉ!!
ኬ.ቀና

4. ብትሞትም ለሀገርህ!!

5. ነፍሳችሁን በገነት ያኑረው!!

11/2/2003

1. የመተባበር ፍጥነት ለመሪዎች አሠራር ስንል እንተባበር፡፡ ስደተኛው

2. በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ በሰው ብልሃት የቀረ ሰቆቃ አይደለም፡፡
ታምሩ እንዳለ

3. ይህ እንዳይደገም ዜጐች ሁሉ ይጐበኙት ዘንድ ወይም ይታወቅ ዘንድ ጥረቱ ይቀጥል!!
መሐመድ ኡስማን

4. ይህ ትውልድ ያለቀበት ተግባር ሁለተኛ አይደገምም!! አሳፋሪ ስለሆነ፡፡ አገራችንን እ/ር ይጠብቃት!!

5. አይደገም! ግን ራሳችንን እንወቅ፡፡

ይኩኖአምላክ ካሣዬ

6. ሐሳቡን እደግፈዋለሁ በጣም ሊመሰገን ይገባዋል! ባለፈ ታሪክ እንኖርም እኛም የምኖረው አለም ታሪክ ነውና!!

7. ሙታንን ነፍስ ይማር!! እግዚአብሔርን መፍራት፤ ማስመሰል፤ ሆድ ብቻ መሙላት ይቅር፤ ግልፅነት በተዘዋዋሪ መናገር ይቅር፡ ባህላችን ይሁን ወሬ ብቻ አንሁን፡፡

8. ይህ ዘግናኝ ነገር እንዳይደገም ሁላችንም በርትተን እንስራ!!

9. በጣም አሳዛኝና አጸያሪ ስራ በአገራችን በመሰራቱ እጅግ በጣም አዝናለሁ፡፡ መንግስት ይህንን ስላደረገው ክብር ምስጋና ይድረሰው፡፡
ሶል

10. ሁኔታዎች እጅግ ያሳዝናሉ፡፡ ይህ ድርጊት ጌታ ተበቅሎታል ይህንን በልማትና በመዋደድ እጅ ለእጅ ተያይዞ ይህን የስኬት ስራ ይበቀለዋል!!

11. በእውነቱ ከሆነ እጅግ በጣም አሳዛኝና ህሊና ለነበሩት ብቻ ሳይሆን አልፎ ለተመለከትነውም ቢሆን የማይረሳ ጠባሳ ሰቶን አልፏል!!

12. ውድ ወንድሜ ዳኒ ዛሬ ላይህ ብጣ ከምትወዳች የትግል ጓደኞችህ ጋር መልዕክታችሁን አየሁ፡፡ እኔም ያላችሁኝን እንዲህ አልኩ እኛ አለፍን እናንተስ አገራችንን ለመገንባት ዛሬ ምን እየሰራችሁ ነው!! በመቻቻል ላይ ታገሉ በፍቅርና በሰላም ኑሩ፤ ጥሩ ነገር ሰርታችሁ ነብሳችንን ታደጉ፤ ያላችሁኝን አልኩ፡፡
ምናሴ

13. በእኔ ዘመን ግን በኢትዮጲያ ላይ መልካሙን አያለሁ!! እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይባርክ!!

14. ስናደርግ ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔርም ይሁን!!

15. ይህንን መአት እግዚአብሔር ደግሞ አያሳየን!!

16. በእናታችሁ አሁን ያለንበትን ዘመን እናመስግን፡፡
ማህሌት

12/1/2003

1. በርግጥም ይህ ይብቃን እንተሳሰብ፤ እንከባበር፤ እንዋደድ፤ ምድራችን የብዙናታና!! እግዚአብሔር ይጠብቀን ምድራችንንም ይባርክ፡፡ አሜን!!
ሀና ሞገስ

2. በሞኝታችን ጊዜ ይህንን ሁሉ ሰው አጣን፤ በብልጥነታችን ጊዜ ደግሞ ጊዜው ይቁጠረው!! መቼ ይሆን የሚነጋልን!!
አድማሱ ( ከድሬደዋ)

3. ያሳዝናል በጣም ነፃ ነኝ እግዚአብሔር ምድራችንን ይባርክ!! ሰላም ለኢትዮጲያ!!
ፍሬሰንበት ደበበ

4. ሰው እንደመሆኔ መጠን የአንድ ሰው መከራን ማየት አልፈልግም፡፡ በፖለቲካ ምክኒያት የዚህን ሁሉ ህዝብ መቀጠፉን ሳስታውስ በጣም ያሳዝናል፡፡ ነገር ግን ይህ የትላንትናው
ያሰቃቂ ክስተት ነው፡፡ አሁን ያየነውን እና እያየን ያለውን ተመሳሳይ እልቂት መቼ እንዘግበው፡፡

5. በሰላም ይረፉ!! May they rest in peace!!!
Mehret Equbaye

14/2/2003

1. የድንቁርና ውጤት ነው የአሁኑ ትውልድ ይህን ታሪክ ለማደስ የበኩላችንን እንወጣ፡፡

2. አምላክ ነብሳቸውን ይማረው!!

3. ሁሉም እንደሚያልፍ ከእናንተ አየሁ!!!

4. አይ ኢትዮጲያ ሀገሬ ይህ ነው ታሪክሽ?

15/2/2003

1. በዛሬ ውስጥ ትናንትን አይተናል፡፡ እባካችሁ እንዳይደገም!!

2. በጣም ጥሩ ሙዚየም ነው በዚህ ቀጥሉበት፡፡ አስተማሪም ነው፡፡

3. Rest in peace, Never Again!!

4. በጣም ያሳዝናል ግን አደራ እንዳይደገም!!

5. ታሪክ ተሰብስቦ በአንድነት አይተናል፡፡
ደበሽ ጋዲሳ

6. ይህንን የደርግ ጭፍጨፋ ያካሄዱ የቀድሞ ባለስልጣናትን የፍርድ ሂድት አይቼ ነበር፡፡
በቁም የሞተ ሰው ነው የሚመስሉት ፀፀቱ፡፡
ወርቅነህ ደበበ

7. ከታሪክ የማይማር ታሪክን ይደግማል፡፡ እንዳይደገምብን አደራ፡፡
ማሞ ጴጥሮስ

19/2/2003

1. አምላክ የሞቱትን ነፍስ ይማርልን!! በናንተው ይብቃ!!

2. ለዚ ነፃነታችን ያለቁትን ወንድም እህቶቻችን ሰማዕታት እግዚአብሔር በገነት እንዲያኖሩልን እንጸልያለን፡፡

3. የማያልፍ የለም!!

20/2/2003

1. እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በገነት ያኑረው!!!
ዳዮታ

2. እነሱ ለእኛ እንደሞቱ እኛ ለሀገራችን መሞት ይኖርብናል፡፡
እዩኤል

3. This is a nice heritage in Ethiopia!!
Selome

4. We are sorry about those killing!!

5. Never! Again!! In any mat of the world!!

21/2/2003

1. It won’t happen again!! That’s really immoral!!

2. This is an eye opener
RIP
They didn’t die for nothing!!

3. New ERA in Ethiopia is due to them.

4. Its hard for me to believe for me to believe this happened for real, God has The best!! They are the HEROS!!

5. ቢቻል ቢቻል ይህንን ታሪክ ትውልድ ማስተማሪያ ማድረጋቸው ጥሩ ነው ይሁንና የደርግ በደል ይህንን ያህል አስከፊ መሆኑን አይቻለሁ!!
ምህረቱ ረጋሣ

22/2/2003

1. በጀግኖቻችን እንደገና ተወልደናል!!
አለማየሁ

2. በጀግኖቻችን ኮራን!!
አህመዲን

3. ወንድሞቻችንን አንረሳም!!
ሲሳይ

4. ለዛሬው ማንነታችን ለከፈላችሁት መስዋትነት እናመሰግናለን!!
ሃቢ

5. ብቻ ለኢትዮጲያ እግዚአብሔር ሰላምን ይስጣት!! ነፍሳችሁን ይማር! “ በእናንተ ትግል
እኛ ተርፈናልና”

6. ነገር ሁሉ ለበጐ ሆነ በእናንተ ደም እና እንባ እኛ ሰዚህ በቅተናልና እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በገነት ያኑረው፡፡
በሰላም ግዛቸው

7. ጌታ ሆይ እባክህን ኢትዮጲያን ባርካት (ማራት) ይህ ነው ናፍቆቴ፡፡

23/2/2003

1. ጌታ በሰማይ ነፍሳቸውን ተቀበላት ለወደፊት ትውልድ ትልቅ ትምህርት የሚሆን ቤተመዘክር ሠርታችሁልናል!!
ራህዋ

2. እ/ር አምላክ ነፍሳችሁን ከቅዱሳን ሰማዕታት ማለትም ከነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ቅዱስ ስቲፋኖስ ቅድስት አርሴማና ከሌሎች ቅዱሳን ሰማዕታት ጋር ይደምርላችሁ፡፡ እንዲሁምነፍሳችሁንበአብርሃም፤ በይሳቅ፤ በያዕቆብ አጠገብ ያሳርፍላችሁ፡፡ ጨሩ እ/ር ሀገራችንን ቅድስት ኢት ዮጲያን፤ አፍሪካ መላው ዓለምን ሰላም ያድርግልን፡፡
አክሊለ ጊዮርጊስ

3. በእናንተ መስታዋት እኛ ኖረናል ታላቅ ክብርና ምስጋና፡፡

4. በእርግጠኝነት ሀገሬ ብዙ ችግር አሳልፋለች ካሁን ወዲህ ግን አትቸገርም፡፡
አላዛር መኮንን

5. ያሳዝናል ለሚቀጥለው ትውልድም ጥሩ ትምህርት ያሰጣል፡፡

6. ደ - ደብድበህ
ር - ርግጥ አርገህ
ግ - ግዛቸው ደደብ ነው አይደል?

7. በእርግጠኝነት በደርግ ዘመን ከክቡር የሰው ነፍስ ይልቅ ጥፋት ይከበር እንደነበር ተገነዘብኩ፡፡ ግን ታጋዩ ሞተ እንጂ አላማው አልሞተም፡፡
እዮብ ካሣ

25/2/2003

1. ሰው ያልፋል ታሪክ ግን ከተጠበቀ ለዘላለም ይኖራል፡፡
ምንተስኖት ደገፉ

2. ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቶኛል፡፡ ዳግም እንደዚህ ዓይነት የዘር ያማጥፋት ወንጀል እንዳይደገም ባገኘሁት አጋጣሚ ወገኖቼን አስተምራለሁ፡፡
ደምሴ

3. እነሆ ጥቁር ጠባሳ ራሱን እንዳይደግም ለሰማዕታት ክብር ለዘላለም፡፡
አብርሀም

26/2/2003

4. በእርግጥ ይህ ነገር በሀገራችን ተፈጽሟል! ከዚህ በኋላ ለሚፈሰው ክብር ደም ተጠያቂ ላለመሆን እውነትንና ነፃነትን ይዘን ልንጓዝ ይገባናል፡፡
ዘካሪያስ ሀ/ሚካኤል

5. በጣም አሳዛኝ ! እግዚአብሔር ምህረት ያድርግ፡፡
ዳዊት ንጉሱ

6. ወንድሜ አምሳሉ ማሞ ምንግዜም አልረሳህም፡፡
አጥናፉ ማሞ

28/2/2003

1. የሰማዕታት ዓላማ ዘላለማዊ ነው፡፡ ክብር ለነሱ ይሁን፡፡
ደበሽ ጋዲሳ

2. ባየሁት ነገር በጣም ነው ያዘንኩት እንዲህ አይነት ክስተት መፈጠር የለበትም፡፡
ሔኖክ ይትባረክ

3. የምወድህ ወንድሜ ምንግዜም አስታውስሀለሁ፡፡
ዮሀንስ ተረፈ

29/2/2003

1. በዚህ ሁሉ ግፍና መከራ ያ ትውልድ አልፏል!! ያሁን ትውልድስ ምን ማድረግ እንዳለበር ያውቅ ይሆን?

2. አለቀስኩ የወገኖቼን አፅም አይቼ፡፡

30/2/2003

1. እንዳይደገም እንታገላለን፡፡

2. ለምን?
ከሀረር

3. እኛ የአሁን ዘመን ትውልዶች ከቀድሞው ትምህርት ካልወሰድን ትርጉም የለውም፡፡
ታጠቅ

4/3/2003

1. መቼም እንዴትም እንዳይደገም፡፡ ያለፈው በቃን፡፡
እስክንድር ደስታ

2. You will always be remembered!!

3. The world needs to remember your sacrifices!!

5/3/2003

1. Let us pray to God! So that such story may not be repeated anywhere in the world!!

2. ለሁሉም ዕድሜ አለው፡፡
አየነው

3. ዕድሜ ለዚህ መንግሥት!!
ዳዊት

6/3/2003

1. ክርስቶስ ነፍሳችሁን በእግዚአብሔር በቀኝ በኩል ካሉት በአብርሀምና በይስሐቅ ያስቀምጣችሁ፡፡

2. እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በሰላም ወደ ገነት በር ያስገባላችሁ፡፡

3. አግዚአብሔር ይመስገን ለዚህ አድርሶናል፡፡

8/3/2003

1. ይሄ መንግሥት ዕድሜውን ለማራዘም ስለሚጠቅመው ይህ ሙዚየም እንዳይዘጋ፡፡

2. ይህ ሙዚየም ያለፈ ጥቁር ታሪካችንን ግም እንዳይደገም አስተምሮናል፡፡

3. እንደዚህ አረመኔያዊ ድርጊት ፈጣሪ ይክፈለው፡፡

4. ጥሩ ታሪክ ለመፍጠር እንነሳ፡፡

5. ይህ ታሪክ የትም እንዳይደገም አባወራ ወጣት የጦርነትና የስደት ሰለባ አይሁን፡፡

9/3/2003

1. መገደል ያለበት ሌባ ብቻ ነው፡፡ ማንኛውም መንግስት አይገደል፡፡

2. ልዩነትን በውይይት እንጂ በጥይትና በማሰር ለመፍታት መሞከር ይቅር፡፡

3. አረመኔያዊ አገዛዝ!!!

4. እንኳንም አልተወለድኩ!!

11/3/2003

1. መችስ ያለፈው አልፏል ደግሞ እንዳይደገም ምኞቴ ነው፡፡
ጳውሎስ ሲሳይ

2. በጊዜው አልነበርኩም በምሰማውና በማያቸው የፎቶና የቪዲዮ ማስረጃ ግን በጣም አዝኛለሁ ማየቱና መስማቱ እራሱ አሰቃቂ ነው እንኳን በራስና በቤተሰብ ላይ መፈፀም፡፡
እባካችሁ መንግስት መሆን የምትፈልጉ እንዲሁም አሁነ እሱ ውስጥ ያላችሁ በአይምሮ ዋችሁ አስቡ አደራ እንዳይደገም፡፡
ሔኖክ ጥሩሰው

3. ድጋሚ እንደዚህ አይነት ላለማድረግ ቃል እንግባ!!

12/3/2003

1. ለውድ አያቴ ላቀው
ሄርሜላ

2. ታሪክ ል እንደሆን ቢቀር እመኛለሁ፡፡
ሀትዊት ወርቁ

3. በ1983 ልጅ ተወለደ እሱም አማኑኤል ባላቸው ይባላል፡፡

14/3/2003

1. ይህ እልቂት በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ በእነዚህ ወገኖቻችን መስዋትነት ይህ ቀን መጥቷ ወገኔ የቱ ይሻላል? እኔ ይህንን ቀን ወደኋላ እንዳይመለስ እጠብቃለሁ ለምን ቢባል
ተምሬበታለሁ፤ ሠርቼበታለሁ፤ ለወግ ለማዕረግ በቅቼበታለሁና እኔ እጠብቀዋለሁ፡፡ ስርዓቱ እንዲጐለብት ሰላማችን በጋራ የመጠበቅ የዜግነት እና የነዚህ ሰማዕታት አደራ
ስላለብን፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይባርክ፡፡
ቶማስ

2. ይህ እልቂት አይደገም ለዘላለም እንዳለፈ ይቆጠር፡፡ ስለዚህ ከእንግዲህ የአንድም ሰው ነፃ ሀሳብን መብት የሁላችንም ይሁን፡፡

3. ሁሴን መሐመድ ሁሴን (አርሲ አሰላ) “የተባለው የፋሺሰቶች መጋዝ በኛ ደም ይዶሎድማል፡፡ አንድ ቀን ጭቁን የኢትዮጲያ ህዝቦች ያቸንፋሉ!!” ብለህ የተናገርከው
የመጨረሻ ቃልህ እውን ሆኖ ያለነው አይተናል፡፡
ታደሰ

4. ሰው ለአንድም ለሌላም ይሞታል፡፡ ለአላማ ሞት ደግሞ ተላቅነት ነው፡፡

5. በእናንተ ደም ዛሬ እየኖርን ነው፡፡ እግዚአብሔር ነፍሳችሁን በገነት ያኑር!! ቅርሶቻችንን እንጠብቅ፡፡

15/3/2003

1. ትናንት ያለፈው እውነታ አልፎ ዛሬ ይህን ማየቴ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡

2. እግዚአብሔር የሞቱትን ነፍስ ይማር!!

3. ህፃናቱስ ለምን?

4. ደርሼበት ባላየውም በጊዜው እግዚብሽኑ ልብ ይነካል! በዚሁ ይብቃ እግዚአብሔር ነብሳቸው በገነት ያኑራት!!

16/3/2003

1. እውን ወገን ለወገኑ እንዲህ ይጨክናል!! እግዚኦ!! በዚሁ ይብቃ በገነት ያሳርፍልን!!
ረድኤት በረከት

2. እንዲህ ያለ አሳፋሪ ታሪክ በኢትዮጲያ በመፈጸሙ በጣም አዝናለሁ፡፡
አንዱዓለም

3. ይህንን ታላቅነቀ መራረራ ሂደት አልፋችሁ ለዛሬው ሰላምና ዴምክራሲ ስላበቃችሁን እናመሰግናለን፡፡
ማሜ

4. በጣም ጥሩ ትምህርት አግኝተናል፤ መቼም አይደገምም ከዚህ የተለየ ሁኔታ መቅረብ አለበት አሁንም ህዝቡ እንዲያውቀው፡፡
ሳሙኤል ወልዴ

5. ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር፡፡ ይህ ታሪክ እንዳይደገም የዘወትር ምኞቴ ነው፡፡
ኑርሰፋ፤ ዘኩና ኢክራም

6. ጠመንጃ መፍትሄ ሆኖ አያውቅም ወደፊትም አይሆንም፡፡ ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!
ደመላሽ አማረ

7. ሁሉም ያልፋል፤ ይህም አልፎአል፡፡ ነገር ግን ምን እንደሚያጋጥመን ስሰማናውቅ ለዘላለሙ ህይወት የምናገኝበትን መንገድ ለይተን እንወቅ!!!
አሀዱ ገብሩ

18/3/2003

1. ማየት ማመን ነው፤ ታሪክ ምስክት ነው!!

2. የቅንነት መንፈስ በውስጣችሁ ይዘራ፤ እንዋደድ፤ አንጠላላ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

3. በዚህ ዘመን ኖሮ ይህንን ታሪከ ማየት እድለኛ መሆን ነው፡፡ ታድያ ይህን እድል ልማታዊ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ግዴታም ነው፡፡

4. መቼም አይደገምም!!

5. በጣም አዝኛለሁ እንዳይደገም!!!
ሜሮን

6. ይሄ እዚህ ያየነው በውነቱ ጥሩ ነው ምክንያቱም በዚ አጋጣሚ አባቱም በፎቶ ስላየሁ ደስ ብሎኛል፡፡ የአባቴ ስም ጌታቸው ገ/ጊዮርጊስ ነበር፤ እግዚአብሔር ነብሱን ይባርክ፡፡
ሚኪያስ ጌታቸው

7. ዳግም አይምጣ ነፍሳችሁን በገነት ያኑረው፡፡

8. በእናንተ ትግል የተነሳ እና ለዚህ በቅተናልና በጣም እናመሰግናልን፡፡ ነብሳችሁን በመንግሥተ ሰማያት ያቆይልን፡፡
ዮሐንስ፤ ስለሺ፤ ቢኒያም እና ሻፊ

9. እ/ር ከዚህ በኋላ ለእንደዚህ ነገር አያሳልፈንም፡፡
ዳግም ተስፋዬ

10. እ/ት መጪውን ግዜ ከዚህ እንድንማርበት ያደርግልን፤ እዕምሮ ይስጠን፡፡

22/3/2003

1. በጣም ባየሁት ነገር ተገርሜያለሁ ብዙም ነገር ተምሬያለሁ፡፡

2. ይህንን ሁሉ የተቀበላችሁ ሰማዕታት ፈጣሪ ነፍሳችሁን በገነት ያኑራት፡፡ የአሁኑ ዘመን ትውልድ ዘወትር ያስባችሁ ዘንድ ይሁን፡፡

3. Father God may we never forget those who gave life for Justice and freedom, bring peace to this land always. Thank you God!!

24/3/2003

1. ይህን ሁሉ በማየቴ በጣም ተደስቻለሁኝ ግን በጣም አሰቃቁ ሰይጣን ድርጊት ነው ከአሁኑ ጋር ሊገናኝ አይችልም፡፡ እግዚአብሑር አምላክ ኢትዮጲያን ለወደፊት ይጠብቅ!!

2. በጊዜው መሆን ያለበት ሆነ፤ ግን አሁን ዳግም እንዳይደገም እግዚአብሔር ይጠብቀን አሜን!!

3. ያየሁት ሁሉ በጣም አሰቃቂና አሳዛኝ ነው ይህ ታሪክ መቸም ተመልሶ አይደገምም!!

4. እኔ በኢትዮጲያዊነቴ ኮርቻለሁ ይህ ቅርፅ ለትውልድ እንዲተላለፍ በአክብሮት እጠየቃለሁ፡፡

ፍፁም አለማየሁ

5. ጎኑ ካለው አ.አ ሙዚየም ጋር የማይገናኝ የጥራት ደረጃ አስተውያለሁ (ምናልባት አዲስ ፎቅ ስለሆነ ይሆን)

6. ይህ ነገር በዚህ ይብቃ እግዚአብሔር አገራችንን ከዚህ እልቂት እግዚአብሔር አገራችንን ይባርክ!!

27/3/2003

1. ታሪክን የማያውቅ የታሪከን መጥፎ ተግባር ወይም በታሪክ የተሠራውን ስህተት ይደግማል እንደሚባለው ለታሪክ ይህንን ማቅረቡ መንግስትን አመሰግናለሁ፡፡ ከታሪክ እንማር!!
ባልላቸው አባትነህ

2. ለመናገር በጣም ይከብዳል በእውነት በፊ የነበረውን ትክክለኛ ሁኔታ በአሳማኝ መረጃ አስደግፎ ማቅረብም በጣም ጥሩ ነው፡፡
ልዑል ቢራራ እና ሚካዜል ግደይ

3. ዳግም እንዳይደገም እፈራለሁ!!
ሰይድ

4. ኢትዮጲያዬ እውነት ነውን?
ኤሉል

5. ይህ ታሪክ በውነት መደገም ያለበትም፡፡
ማርታ በርሄ

6. እምባዬን ተቆጣጠሬ እንደምንም ጨረስኩት፤ አቤት በኢትዮጲያችን ያለፈው ግፍ ይህ ታሪክን ያሁኑ ትውልድ መልካም ነው፡፡ በቃ በቃ፡፡
መላኩ ተኮላ

28/3/2003

1. የናንተ ሞት ለኛ ህይወት!!

2. በእውነት አንድ ትውልድ ጠፍቷል ይህም የታሪከ ክፍተትን ፈጥሯል፡፡

3. እግዚአብሔር ሆይ ይህንን ስርዓት ስላሳየኸን ከልብ እናመሰግንሀለን፡፡ የሞቱትንም ወንድሞች እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር፡፡ ከዚህም በላይ ብዙ ያልተገኘ መረጃ እንጂ
እንኳን እንባ ደም ያስለቅሳል፡፡ ይህንን በሙዚየም መልክ ስላሳያችሁን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ኢትዮጲያ ታላቅ ነች!!!
አብርሀም ወልዴ

4. ፈጣሪ ሆይ! በዚያ ዘመን ስላልተወለድኩኝ ዕድሜ ልኬን አመሰግንሃለሁ፡፡
ምህረት ያረጋል

30/3/2003

1. አምላኬ ሆይ አይነቱን ሰይጣናዊ ስራ ሚቀጥለው ትውልድ እንዳያይ ጠብቀው!!!

2. በጣም ያስጨንቃል፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ኢትዮጲያን ጨክንበት ሆይ ምህረትህን
አትንፈጋት!!!

3. በናንተ መስዋዕትነት ለዚህ በቃን!!

4. የተታገሉት ትግል ለፍሬ በቃ!!

5. ፍሬአችሁን አየነው የትግላችሁም ውጤት አጣጣምነው፡፡
አደሰች ተወልደ

6. ይህን ማፈሪያ ታሪካችንን የውጭ ዜጎች ባያዩት እመርጣለሁ፡፡

7. Never again!!
Mulugeta

8. The one who kill one without Justice is considered as the one kill humanity

1/4/2003

1. ሰው ሰውን ሀሳቡን ስለቃወመው ይገለዋል፡፡ እባካችሁ ሁላችንም ቅን እነሁን!!

2. አሁንም እንዳይደገም አደራ!!

3. I wish I was there!!

4. ሁሌም ስህተት ይፈጸማል! ግን አይደገም!!

5. This is the proof!!

6. We lost our brother, sisters, moms and dad, look at them..... I hate Mengistu!!

7. I wanted to be like them, never succeeded.

8. Now, I am so pleased, because I know them past stupidity will never come Back again” Mengistu was really stupid!!!

4/4/2003

1. ደርግ በጣም ክፉ ነው ውዳቂ ነገር ነው ያደረገው፡፡ ባየነው ነገር በጣም አዝነናል፡፡

2. ደርግ በጣም ክፉ ነው በጣም ነው ያዘንኩት፡፡

3. ባየኋቸው ፎቶዎች ደርግ ምን ያህን ጨካኝ እንደነበረ ማረጋገጫ ሆኖኛል፡፡
ተስፋዬ

4. ይህን ያህል ጭካኔ አይቼ አላውቅም፡፡

5. የደርግን ያህል ጨካኝ ምንግዜም አይኖርም፡፡ በእሱ እጅ ለሞቱት ዜጎቻችን ከልቤ አዝኛለሁ፡፡
ሰለሞን እሸቴ

6. እውነት ትውልድ የማይረሳው! እጅግ አልረሳውም!!

7. በወቅቱ ባልኖርም ግን ውስጥን የሚነካ ተግባር አረመኔያዊ ድርጊት ቢሆን የአሁኑ ትውልድ ይማርበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ሚካኤል

8. የአሁን ዘመን ትውልድ እንደመሆኔ በማንበብና በመስማት የቀይ ሽብር እልቂት ምን ያህል ዘግናኝ መሆኑን የተገነዘብኩት፡፡

9. አባት፣እናቶች.እህት፣ ወንድሞች፣ እህቶች በጣም አዝነናል፡፡ የአሁኑ ትውልድ ከናንት ተምረናል፡፡
ኤልያስ ብርሀኔ

5/4/2003

1. በየሱስ ስም ዳግም አይመጣም እግዚአብሔር አይቶናል!!

2. ዳግመኛ ለዘላለም እንዳይደገም እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይጠብቃት!!

3. ምነው ይሄ ሁሉ ጭካኔ!!
ውብሸት

4. ያሁኑ ትውልድ በጣም እድለኞች ነን ስለዚህ ሁላችንም ያለፈውን ትውልድ ችግር ከግምት ለማስገባት ላገራችን እድገት ለተገኘው ሰላም በርትተን መስራት የጠበቅብናል፡፡
ተስፋዬ በርሄ

5. ባሁት ነገር በጣም አዝኛለሁ፡፡ ያለፈው ትውልድ ዲሞክራሲን ለመገንባት ያደረገው መሪር ትግል ዛሬም ሀገርን ለመገንባት ይደገም!!

6/4/2003

1. በጣም ኢሰብዓዊ ተግባር ነው የተፈጸምወ፡፡ በጣም ያሳዝናል አምላክ ኢትየጶያን ከዚህ ዓይነቱ ኢሰብአዊ ድርጊት ይጠብቃት፡፡

2. እነዚህማ ኢትዮጲያውያን መሆናቸውን እጠራጠራለሁ፡፡

3. በጣም አዝኛለሁ! እምላከ እስራኤል ያንን ዘመን አይመልስ፡፡
ወንድወሰን

4. ይህን ሁሉ ያደረጉት የሰው ዘሮ መሆናቸውን ማመን ያስቸግራል!!

5. ደርግ ግን ነፍሱ አይማርም! ኢትየጲያ ለዘላለም ትኑር!!

6. እንደመጥፎ ህልም ሁሌም የሚያስቃዥ፣ ሁሌም የሚዘገንን ዘመን! ላለፈውና ለተደረገው ግፍ እያዘንን በማለፉ እንደሰታለን፡፡

7/4/2003

1. በጣም ያሳዝናል!!
ስህን ሐይሉ

2. እንዳይደገም ፈጣሪ ይጠብቀን!!
ኤርሚያስና ኡመር

3. ይህ ታሪክ እንዳይደገም!!
ፍፁም ፍስሐ

4. ከአሁን በኋላ ኢትዮጵያ ይህ አሰቃቂ ታሪክ እንዳይገጥማት ተግተን እንስራ እንጸልይ፡፡

5. አባይንህ ውድ አጎቴ ምንም በህጻንነቴ ብትሞትም ዛሬ አስታውሼሀለሁ፡፡
ለአለም

6. ስለውነት ለመናገር ደርግ እጅግ በጣም ያሳዝናል፡፡ አረመኔና ግፈኛ መንግሥት መሆኑን ባየሁት ነገር አረጋግጫለሁ፡፡
ሙሉአለምና ቴዎድሮስ

7. ደርግ አርመኔ እ ጨካኝ እንደሆነ አይቻለሁ በውነት ከእንግዲህ እንደዚህ ነገር እንዳይደገም ሁላችንም መተባበር አለብን፡፡

8. ያሳዝናል በጣም ግን እስካሁን ተጠብቆ ለኛ መቅረቡ ደስ ይላል፡፡

9. በዚህ ደም ተጨማሪ ይቅርታ መጠየቅ ያሳፍራል፡፡

10. ኢትዮጲያ ሀገሬ
መኖሪያ ክብሬ
ልጆችሽ አኮሩሽ
ደማቸውን ሰጡሽ
ቢኒያም ተስፋዬ

11. I will never let to be done! Again “ The Red Terror’ Never, Never, Never…!!
Yedidiiya

8/4/2003

1. ኢትዮጲያን እግዚአብሔር ይጠብቃት ከመለያየት፤ ከመከራ፤ ከጦርነት ይጠብቃት!!

11/4/2003

1. ያለፈ አልፏል እንደገና ይህ ታሪክ እንዳይደገም እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡
ሄኖክ

2. በጣም አዝኛለሁ መቸም አይደገምም፡፡
ኤልሳ

3. ከዚህ ስርዓት በመትረፌ ደስተኛ ነኝ፡፡

4. እነኚህን ሁሉ የቀይ ሽብር ሰማዕታትን ለጨፈጨፈና በአሁኑ ሰዓት እስር ቤት ለሚገኙ ባለስልጣናት ምህረት እንዲደረግ ለሚሯሯጡት የሐይማኖት አባቶች እናዝንላቸዋለን፡፡

5. በዚህ ይብቃ!!
ሚኪ

6. ለሰማዕታት ስንቴ እንዳነባሁ ባላስታውሰውም እነሆ ዛሬም አነባሁኝ፡፡ እነሱ ጎድለውብኝ እኔ ሙሉ ሆንኩኝ፡፡
ሙኒር አልሀሚድ

7. በሕይወት ዘመኔ ተደግሞ ማየት አልፈልግም!!
ራሄል

8. ይህንን በደል ለሰሩት ይቅርታ አያስፈልግም፡፡

9. ሞት አይቀርም፣ ስም አይቀበርም እንደተባለ ሁሉ ለስማችን መስራት አለብን!!

10. በኢትዮጲያ ውስጥ ቂም በቀል ያብቃ! እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ይባርክ!

12/4/2003

1. እጅግ ውስጤ ደማ ለካንስ ይህም ነበር?

2. ወገንህ ወገን ካልሆነ ምን ይጠቅምሃል?

3. ምን ያህል አስጨናቂ ግዜ ነበር?

4. ከአሁን በኋላ እንዳይደገም የበኩሌን እጥራለሁ፡፡

5. I appreciate the solidarities who lost their life for their country.be like those!!

13/4/2003

1. I just understand the value of peace!!

2. እንኳንም በዛ ዘመን አልተወለድኩ!!

3. በዛ ዘመን ባለመፈጠሬ እግዚአብሔርን ከልብ አመሰግናለሁ!! መንግሥቱ የሰይጣን ታናሽ ወንድም ነው፡፡
ቅድስት ፍቅረልዑል

4. It was the most horable time!!

5. እንኳን ግዜ አለፈ! መልካሙን ዘመን ያምጣልን፡፡

6. በግፍ ለተገደላችሁ እግዚአብሔር መንግስተ ሰማያትን ያውርሳችሁ!!

7. Medon Robert for more information- 0913-171960

8. I am really amazed about it and it very unmisirable thing what mengestu did this law was very difficult for life or for everything when I see this. I told for God not to born on this time really I thank god forever.

9. ያየሁት ነገር በጣም አስደንግጦኛል፣ ለአሁን እኔነቴ የነሱ መስዋትነት ትልቅ ነገር ነው፡፡

10. ለምን ማሳየቱ አስፈለገ?

12. አሁን ለምተነፍሰው የሰላም አየር የናንተ መሰዋዕት ትልቅ ድርሻ ነበረው፡፡
ኤርሚያስ ጌታቸው

13. ሕይወታቸው በአረመኔዎች ጨካኞች እጅ ብታልፍም ያማያልፍ ታሪክ በመሥራት የብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች እኩልነት በማስፈን ያፉ ታጋዮች ለዘላለም ይታሰባሉ፡፡

14. የገዛ ወንድምህ፣እህትህ፣እናትና አባትህን ገድለህ የሚፎከርበር ግዜ በማብቃቱ መድሐኒአለም የተመሰገነ ይሁን!!

15. እኝም መኖርን ጠላን እግዚአብሔር ክፉን ቀን አሳለፈ ክብር ለሰማዕታት ይሁን!!