Content on this page requires a newer version of Adobe Flash Player.

Get Adobe Flash player

23/7/2002

1. እንዲህ አይነት የአገዛዝ ስርአት ዳግም በኢትዮጵያ እንደማይደገም ወጣቱና አዲሲቱን ኢትዮጵያ የሚረከቡ ሕፃናት አደራ ይላሉ፡፡

2. በሙዚየሙ ያሉት ነገሮች ከዘግናኝነታቸው ባሻገር በየትውልዱ በድጋሚ እንዳይከሰቱ ሊሰመርበት የሚገባ ቆራጥነትን የሚሻ እውነታ ነው፡፡
መሳይ

3. በእንደዚህ አይነት በመዘጋጀቱ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡

4. በሙዚየሙ ያየነው በወቅቱ ከተፈጸመው በጣም ጥቂቱ ነው እጅግ የሚያዘገንን ለመሆኑ እኔ ምስክር ነኝ፡፡
በድሉ

5. I never knew that this much happened & am really touched. Hope this Never happens again. Condolences to all who lost their love ones.

6. አብይና ውብሸት ታሪካችሁ ጎልቶ በመውጣቱ ኩራት ይሰማናል፡፡
Getahcew T.

7. ይህ ሁሉ እንዳይደገም ቃል እንግባ፡፡ ይቅር ለመባባል የወደፊቱን ኢትዮጵያ እንገንባ፡፡

8. እግዜ/ር ሆይ ከአሁን በኋላ ይህቺ ምድር ኢት/ያ ሰዎች ሳይሆኑ አንተ ግዛት፤ምራት በቃ! በላት ሕዝቧንም አሳርፍ፡፡ የአንተ መንግስት ምድርን ትገዛለችና!
Mehret

9. እኔ ምንም አልልም ብቻ ሁሉም ነገር በዚህ ይብቃ!! ፍቅር ያሸንፋል ፀብ፤ጥላቻ፤ ቂም በቀል ይቅር፡፡
ኮሎኔል

10. ለወደፊቱም እግአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቃት፡፡
Betty

11. ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዝርጋ እ/ር ይባርካት
H.T

24/7/2002

1. ሁላችንም ሰው ንነ ለዘመናችን መልካምን ነገር አድርገን እንለፍ እ/ር ሆይ መሪዎቻችንን እርዳ!!
Solo

2. ይሄ ስርአት ዳግመኛ እንዳይመጣ መታገል አለብን፡፡

3. ለምን??? ጌታ ሆይ ኦትዮጵያን ማራት፤ ባርካትም
Alemu

4. Time is change and we have to change. No more killing!!!

5. I don’t know whether the evidences (Photo) are original (true) or not if you Evidence put it near. Unless it is not fair to say that the killed people are Killed by derg or not!

6. ይህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ እንዲደገም አልፈልግም፡፡
ቢኒ

25/7/2002

7. እስከመቼ ይሆን ይህች ሀገር ልጆቿን የምትበላው? አጥፊዎቿ የሚነግሱት?

8. ከእነዚህ አውሬዎች የገላገለን ኢህአዴግ ክብር ምስጋና ይግባው!
መስፍን

9. ይህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ እንዲደገም አልፈልግም፡፡
ቢኒ

10. ከእነዚህ አውሬዎች የገላገለን ኢህአዴግ ክብር ምስጋና ይግባው!!
መስፍን

11. ይህንን ዘግናኝ ሁኔታ በማየቴ እጅግ ከልቤ አዝኛለሁ፤፤ ይህንን ስርአት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ላስወገደልን ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ የታሪክ ተመስጋኝ ነው፡፡ ይህን ሥርዓት
ለመጣል በዚ መስዋትነት እንደተከፈለ ስለሚገባኝ ነው፡፡ ክብር ሰተሰዉትና ነፃ ላወጡን ሱውአት፡፡
D.G

12. ይህ ድርጊት ላይደገም አልፏል፡፡ ቢሆንም ሁላችንም ያለፈውን ለመርሳት ለወደፊቱ
እንዴት ሀገራችን ማሳደግና መለወጥ እንዳለብን ማሰብ አለብን፡፡
ፋጂ

13. ክብር ምስጋና ነፃነት ለሰጡን ሰማእታት ይሁን፡፡
አድማሱ

14. የሞቱትን ሰማዕታት አላህ ነፍሳቸውን ይማርልን፡፡
ኢብራሒም

15. እንግዲህ ገዳዩም ተገዳዩም ኢትዮጵያውያን ሆንን ማን ላይ ቂም ይያዛል? ቁምነገር አድርገን መያዝ ያለብን አሁን በግራ እና በቀኝ የተሰለፍን የፖለቲካ ሀይሎች ይህ ነገር አሰቃቂ ታሪክ እንዳይታሰብ እና እንዳይደገም ምን ዋስትና እንያዝ? ምን ያህልስ ነው መተማመን ያለብን? በእውነት ምን እንማር?

16. ለዚህች ሀገር መልካም ነገር ሰርተን ሳያልቅብን ለምን መተላለቅ እንደመረጥን እያን ዳንዳችን ልንጠያየቅ አና በጥልቅ ልንነጋገርበት ጊዜው አሁን ነው፡፡

17. እግዚአብሔር ዳግም የዚህ አይነት የጭካኔ ሀሳብ ያለውን መሪና ሕዝብ አይመልሰው፡፡

18. እግዚአብሔር ዳግመኛ ማንም ሰው የዚህን አይነት የጭካኔ ስራ እንዳይሰራ በዚህ ይብቃን ጌታ ያስበን፡፡

19. እጅግ በጣም አስተማሪ ነው ላይደገም ሁሉም ሊታገልና ከታሪክ ተወቃሽነትና ከዚሁ ተርታ ከመሰለፍ በቁርጠኝነት ሊንቀሳቀስ ይገባዋል፡፡ የነጭ ሽ    ብርም ሊታከልበት!

20. ይህንን አሳዛኝ ድርጊት ያስቀየረው የሕዝብ ልጆች ትግል እጅግ እጅግ የሚደነቅ ነው፡፡ It will never happen again.

21. እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው ሰቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ብቻ እመኛለሁ፡፡

22. አባቴ የደርግ ወታደር ነው፡፡ ግን እንዲህ አይነት ነገር ያፈርጋል ብዬ አልጠብቅም ያዛዝናል፡፡አፍሬባችኋለሁ፡፡

23. ስንት ንፁሀን አልቀዋል ነፍሳቸውን ይማር፡፡
ዮሴፍ

24. Men are not enemies that is some thing they learn. Let us stand together forever as a citizens of one nation. God Bless Ethiopia & may God Besom the souls of Martyrs in a heavenly.

27/7/2008

1. የተደረገው ነገር በእርግጥ ትልቅ አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ከማዘናችን ቀጥሎ ከስህ ተታችን እንማር ድጋሚ ላለማዘን ልባችንን በትህትና ፀበል እንጠበው!!
ካሱ ከድር

2. እግ/ር በመንግሥቱ ያስባችሁ፡፡
ቶማስ

3. በጣም ነው የሚያሳዝነው፡፡
ሲሳይ

4. እግ/ር ኢትዮጵያን ይርዳት፡፡
አማኑኤል መስፍን

5. ከእንግዲህ በምድሬ ላይ ጥፋት፤እረሀብ፤ ጦርነትና ቸነፈር አይኖርም፡፡
ሚሊዮን ዳዊት

6. ኢትዮጵያን ከእንግዲህ ከእንደዚህ ዓይነት ጥፋት እግ/ር ይጠብቃት፡፡
ፓስተር አመሉ ጌታ

7. ይሄ ታሪክ ይብቃ አይደገም ሁሉ በፍቅር ይሁን!!
G. Zola

8. Please God help my country to not see this thing again, please.
Eyuel Zwedu

9. We don’t want to see this type of thing again.
Darlec Mulip

10. ሰው ሆይ አስተውል፡፡

11. እናንተ ለኛ መንገድ ጠርጋችሁልናል ጨለማውን ብርሀን አድርጋችሁልናል እግ/ር ነፍሳ ችሁን በገነት ያኑረው ሕያውም ናችሁ፡፡
ዮርዳኖስ

12. ያለውን እውነት በማወቃችን በጣም ተደስቻለሁ ፍርዱን እ/ግር ይስጥ፡፡

13. ታሪክን ማወቅ ስህተትን ላለመድገም ወሳኝ ነው፡፡
ቀ.ድ.ካ.መ

14. የሰው ልጅ ስንት ዘመን ለመኖር እንዲህ አይነት ጭካኔ ይፈጽማል፡፡ ሁላችሁም ከዚህ ተማሩ መንግስተ ስላሴ ዘላለም ናት፡፡

29/7/2002

1. ፍቅረኛዬ ሶፍያ አየለ ደምሽ ደመ ከልብ ሆኖ አልቀረም ህያው ነሽ ለዘላለም፡፡
ፈ.ጥ (ዋሽንግተን)

2. We will never let you die.

3. We need to learn form the past! So please use it only to learn!

4. ታላትን ሳይ በእውነት ዛሬን አመሰገንኩት፡፡
አ.ብ

5. ተመስገን ይህም አለና!!

1/8/2002

1. ድጋሚ ማልቀስ ሰለማልፈልግ እስከመጨረሻው ቃል እገባለሁ፡፡

2. እናንተ የትውልድ ጀግኖች ነፍሳችሁ ገነት ይግባልና!!!
ፋሲል ጌታቸው

3. ከዚህ በኋላ ይህ አይደገምም፡፡
እናውጋው ሰማኸኝ

4. May all those life’s souls rest in heaven! እግኦአብሔር ይህንን በደል ለፈጸሙትና ላልፈጸሙት ሰዎች ተፀፃች ልቦናን ይስጣቸው፡፡ I promise, I swear, in my life will give such by anything to prevent what happened to occur again. God bless Ethiopia.

5. ነፃነት ማለት እየደሙ መሞት፤ ጀግና ሆኖ ሀገርን ለሰላም ማብቃት መሆኑን ከእናንተ አሰቃቂ ግፍ ከተበደላችሁ ያገሬ ጀግኖች ተምሬአለሁ፤፤ መቸም አልረሳችሁም፡፡
ዋልተንጉስ

6. እኔ ከምስጋና በስተቀር ምን ማለት እችላለሁ፡፡ ለአሁን ይብቃን፡፡
ሚሊዮን ሀይሌ

7. እናንተ ህይወታችሁን ሰውታችሁ ለኛ ሕይወት የሰጣችሁን ሰማዕታት እናመሰግናችኋለን፡፡
ሮቤል እና ፍሬሕይወት

8. እናንተ ስለኛ ሕይወታችሁን የሰዋችሁ ከዘላለም እስከ ዘላለም እንወዳችኋለን!!! አምላክ ነፍሳችሁን በገነት ያኑራ፡፡
ጆኒ በሪሁ

3/8/2002

1. ለካ መስዕዋትነት ማለት በሞት የተገኘ ሒይወት ነው!! ክብር ለሰማዕታት!!
Rezene G/S

2. Ethiopia is a beautiful country may such in sane maniacs never even touch the grounds of this nation ever.
Manav

3. This is absolutely in human hope Ethiopia never sells such time ever again.
Paul

4. This is a good lesion for the coming generation not to be happened again.

5. ገብረአብ ፍረህ የምንወድህ ወንድማችን ምንግዜም እናስታውስሀለን እንወድሀለን፡፡
ሀና፣እዮብ፣ግርማ እና ከበደ

6. ውስጤን አመመኝ፡፡
ዮናስ

7. መዘክራችን ለበቀል ሳይሆን ሰፍቅር ይሁን! ተተኪውም ይህን አውቆ ይንከባከበው፡፡
አብርሀም

8. እግዝአብሔር አምላክ በምህረቱ ያስባችሁ፡፡
ታደሰ ፀጋዮ

9. መሆን ያልለበረበት ነገር ሆነ ነገር ግን ፍቅር ነው!!
Rezene G/s

10. የዚያን ጊዜ የነበረውን ጭካኔ እና ድባብ ያስታውሳል፡፡ ፍቅር ወጋ አለው፡፡ መስዋዕቶቹ ተሰውተው እንኳን ወኔያቸው እና አላማቸው ከፊታቸው ላይ ይነበባል፡፡ አከብራቸዋለሁ፡፡
ኤፍሬም

11. ክብር ለተሰው ሰማዕታት ይህ ግፍ በኢትዮጵያ ምድር መቼም ቢሆን አይደገምም ፍቅር መውደድ መተሳሰብና ሀገራዊ ሕዝቦች ነንና፡፡
Yacob

12. ከሙዚየሙ ካየሁትና ከታዘብኩት የተከፈለ መስዋዕት ለኛ መሆኑ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በመነሳት አሁን ያለው ትውልድ ከመጪው ትውልድ ትምህርት መውሰድ መቻልአለበት ይህ ካልሆነ በእጃችን ያለው ወርቅ ወደ መዳብ ይቀየራል ዘላለማዊ ክብር ለሰማዕታት፡፡

13. ለምን አይናገር? ይናገራል ታሪክ፡፡

14. ቃላት በጥም ያጥረኛል ለዚህች ሀገር ስንቱ ዋጋ ከፍሏል፡፡ እነሱ ማየት ያልቻሉትን እኛ
ማየት ችለናል፡፡

15. እኔ የተሰማኝን ስሜት በጣም ዘግናኘነና አስከፊ ችግሮችን በተወሰነ መልኩ ቢሳተፍበትም ሳየው ግን በጣም የባሰ አሳዛኝ አስለቃሽ  ሁኔታ ሰትውልድ መተላለፍ የሚገባው ወጣቱናትልቁ ማየትአለበት እላለሁ፡፡ ክብርና ሞገስ በግፍ ለተጨፈጨፉ
ገ/ዮሐንስ አባይ

16. በውኑ ቀደም ብሎ ደርግ ሲያረገው የነበረው ተግባር ይህ ከሆነ በጣም አሰቃቂና አሳዛኝ ነው፡፡ ይህን በማየቴና ይህን በመረዳቴ እጅግ እንደጠላውና አሁን ላይ ሆኖ ባገኘው ምን ላረግ እንደምችል አላውቅም፡፡ አስጎብኚው ሲያሳዩንና ሲያስረዱን እንባዬን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ ድረስ ነው ያነባሁት፡፡ በርግጥ ወንድም ወይ ዘመድ አልነበረኝም ሆኖም የኢትዮጵያ ሕዝቦች እንዲ ያለ አግባብ መጨፍጨፋቸው ውስጤ አዝኖ ይህን ነገር እንባ ይፋረዳቸው ሳይሆን መንግስት ይፋረዳቸው፡፡ ታዲያ አሁን ካለው መንግስት ጋርማ ሊወዳደር ይችላል፡፡ ክብር መታሰቢያ ለሰማዕታት፡፡
ገነት መገርሳ